በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አምላክ በአሁኑ ጊዜም ምድርን እየተቆጣጠረ ነው?

አምላክ በአሁኑ ጊዜም ምድርን እየተቆጣጠረ ነው?

አምላክ በአሁኑ ጊዜም ምድርን እየተቆጣጠረ ነው?

የተፈጥሮ አደጋዎች፣ ቀሳፊ በሽታዎች፣ ባለ ሥልጣናት ዘንድ የሚታየው ሙስና፣ የሽብርተኞች ጥቃት፣ ጦርነት፣ ወንጀል። እንደነዚህ ያሉ ዜናዎችን ሳንሰማ የምናድርበት ቀን ይኖራል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው። እነዚህ ነገሮች በግለሰብ ደረጃ በእርስዎ ላይ ቢደርሱም ባይደርሱም “ይህ ዓለም ወዴት እያመራ ነው? ነገሮች የሚስተካከሉበት ጊዜስ ይመጣ ይሆን?” ብለው ጠይቀው መሆን አለበት።

ከ200 በሚበልጡ አገሮች የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች እነዚህን ጉዳዮች የሚዳስስ “አምላክ በአሁኑ ጊዜም ምድርን እየተቆጣጠረ ነው?” የሚል ርዕስ ያለው ወቅታዊ የሕዝብ ንግግር ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል። የሕዝብ ንግግሩ አምላክ ቀጥሎ ያሉትን ወሳኝ ጥያቄዎች በተመለከተ አስተማማኝ በሆነው በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተናገራቸውንም ሆነ ቃል የገባቸውን ነገሮች ያብራራል:-

አምላክ ምድር ላይ ስለሚከናወኑት ነገሮች ግድ ይሰጠዋል?

ስለ ሰው ልጆች ምን ይሰማዋል?

ስለ አንተስ ደኅንነት ያስባል?

የሕዝብ ንግግሩ በብዙ ቦታዎች የሚቀርበው እሁድ ሚያዝያ 22, 1998 (ሚያዝያ 30, 2006) በይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ ነው። በአካባቢዎ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች የሕዝብ ንግግሩ የሚደረግበትን ቦታና ሰዓት ሊነግሩዎት መልካም ፈቃዳቸው ነው።

አምላክ በአሁኑ ጊዜም ምድርን እየተቆጣጠረ ነው? ለሚለው ጥያቄ አጥጋቢ መልስ በሚሰጠውና አበረታች በሆነው ነጻ የመጽሐፍ ቅዱስ ንግግር ላይ እንዲገኙ ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልዎታለን።