በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?

በመናፈሻ አካባቢ ወይም መልካም መዓዛ ባላቸው አበቦች መካከል መንሸራሸር የሚያስደስትህ ለምንድን ነው? ውብ የሆነ ሐይቅ አሊያም በደመና የተሸፈኑ ትላልቅ ተራራዎችን ስትመለከት መንፈስህ የሚነቃቃው ለምንድን ነው? ወፎች በዛፎች ላይ ሆነው የሚያሰሙትን አስደሳች ዝማሬ ቆም ብለህ የምታደምጠው ለምን ይሆን? ግልገሎች ሲፈነጩ ወይም በጎች በለመለመ መስክ ላይ ሲግጡ መመልከት አስደሳች የሆነውስ ለምንድን ነው?

የሁሉም ጥያቄዎች መልስ አንድ ነው። የተፈጠርነው በገነት ውስጥ እንድንኖር ስለሆነ ነው! የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን የሆኑት አዳምና ሔዋን በሕይወት መኖር የጀመሩት በገነት ውስጥ ነበር። በገነት ውስጥ የመኖር ፍላጎት የወረስነው ከእነርሱ ሲሆን እነርሱ ደግሞ ይህን ፍላጎት ያገኙት ከፈጣሪያቸው ከይሖዋ አምላክ ነው። አምላክ ግሩም በሆነው ምድራዊ መኖሪያ እንድንደሰት አድርጎ ስለፈጠረን በገነት መኖራችን እንደሚያስደስተን ያውቃል።

ይሖዋ ምድርን የፈጠራት ለምንድን ነው? እርሱ “ምድርን ያበጃት . . . የሰው መኖሪያ” እንድትሆን ነው። (ኢሳይያስ 45:18) ‘የምድር ፈጣሪ’ ለአዳምና ለሔዋን ውብ መኖሪያ የሆነችውን ኤደን ገነትን ሰጥቷቸው ነበር። (ኤርምያስ 10:12፤ ዘፍጥረት 2:7-9, 15, 21, 22) በገነት የነበሩትን ወንዞች፣ አበቦችና ዛፎች ሲመለከቱ ምን ያህል ተደስተው ይሆን? እጅግ ማራኪ የሆኑ አእዋፍ በሰማይ ላይ ሲበሩ ይታያሉ፤ በምድር ላይም ቢሆን የተለያዩ እንስሳት ይርመሰመሱ የነበሩ ሲሆን አንዳቸውም ለሕይወት አስጊ አልነበሩም። ዓሦችና ሌሎች ፍጥረታት ኩልል ባሉት ውኆች ውስጥ ከወዲያ ወዲህ ይዋኛሉ። ከሁሉም በላይ ደግሞ አዳምና ሔዋን አብረው የነበሩ ሲሆን ልጆችን መውለድና እየጨመረ ከሚሄደው ቤተሰባቸው ጋር በደስታ የሚኖሩበትን ገነት ማስፋት ነበረባቸው።

በአሁኑ ጊዜ ምድራችን ገነት ባትሆንም እንኳ ከአንድ ደስተኛ ቤተሰብ ግሩም መኖሪያ ጋር ልትመሳሰል ትችላለች። አምላካችን ይህቺ ዓለም አቀፍ መኖሪያ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ማለትም ብርሃንን፣ ሙቀትን፣ ውኃንና ምግብን አሟልታ እንድትይዝ አድርጓል። የፀሐይ ብርሃንና ሙቀት በማግኘታችን እንዲሁም በምሽት ደብዘዝ ያለ የጨረቃ ብርሃን በመመልከታችን ምንኛ አመስጋኞች ነን! (ዘፍጥረት 1:14-18) በከርሰ ምድር ውስጥ የድንጋይ ከሰልና ነዳጅ ዘይት የመሳሰሉ ሙቀት ሰጪ የኃይል ምንጮች አሉልን። በውኃ ዑደትና ምድር ላይ ባሉት ወንዞች፣ ሐይቆችና ባሕሮች አማካኝነት ውኃ እናገኛለን። በተጨማሪም ምድር ለምለም በሆነ የሣር ምንጣፍ ተሸፍናለች።

በቤት ውስጥ ምግብ እንደሚቀመጥ ሁሉ ምድርም የተከማቸ ምግብ አላት። በእርሻው ላይ የተትረፈረፈ ሰብልና ፍራፍሬ ይኖራል። ይሖዋም ‘ከሰማይ ዝናብና ፍሬያማ ወቅቶችን በመስጠት ልባችንን በመብልና በደስታ ሲያረካው’ ቆይቷል። (የሐዋርያት ሥራ 14:16, 17) ምድር በአሁኑ ጊዜም እንኳ ግሩም መኖሪያ በመሆኗ “ደስተኛ አምላክ” የሆነው ይሖዋ ወደ ገነትነት ሲለውጣት ደግሞ ምን ልትመስል እንደምትችል ገምት!—1 ጢሞቴዎስ 1:11 NW

[በገጽ 2 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች ምንጭ]

COVER: Earth: NASA photo; Stars: NASA, ESA and AURA/​Caltech