በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከፍተኛ ዋጋ ያለው ‘ተሰባሪ ዕቃ’

ከፍተኛ ዋጋ ያለው ‘ተሰባሪ ዕቃ’

ከፍተኛ ዋጋ ያለው ‘ተሰባሪ ዕቃ’

ሐዋርያው ጴጥሮስ “እናንተ ባሎች ሆይ፣ [ሚስቶቻችሁን] በቀላሉ እንደምትሰበር ዕቃ በክብር በመያዝ በእውቀት አብራችሁ ኑሩ” በማለት ጽፏል። (1 ጴጥሮስ 3:7 NW) በዚህ ጥቅስ ላይ ሴቶች ‘በቀላሉ ከምትሰበር ዕቃ’ ጋር መመሳሰላቸው ዝቅ ያደርጋቸዋል? እስቲ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊው ሊናገር የፈለገውን እንመልከት።

“በክብር” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል “ዋጋ፣ . . . አክብሮት” የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል። ስለዚህ አንድ ክርስቲያን ባል ሚስቱን ልክ እንደ ተሰባሪና ውድ ዕቃ በአሳቢነት እንዲሁም በእንክብካቤ መያዝ አለበት። ይህ ደግሞ ፈጽሞ ዝቅ የሚያደርግ አይደለም። ቴፈኒ የሚባለውን የራስጌ መብራት እንደ ምሳሌ አድርገን እንውሰድ። በዚህ ገጽ ላይ የሚታየው ይህ ውብ የራስጌ መብራት በቀላሉ ሊሰበር ስለሚችል ጥንቃቄ የሚፈልግ ዕቃ ነው። ታዲያ መብራቱ በቀላሉ የሚሰበር መሆኑ ዋጋውን ይቀንሰዋል? በፍጹም! ኦሪጂናሉ ቴፈኒ የራስጌ መብራት በ1997 በወጣ ጨረታ ላይ 2.8 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተሽጧል! በቀላሉ ስለሚሰበር ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ መሆኑ ዋጋውን ጨመረለት እንጂ አልቀነሰበትም።

በተመሳሳይም ሴቶች በቀላሉ እንደሚሰበር ዕቃ በክብር መያዛቸው ዝቅ አያደርጋቸውም ወይም አያቃልላቸውም። “በእውቀት አብራችሁ ኑሩ” የሚለው አገላለጽ አንድ ባል የሚስቱን ጠንካራም ሆነ ደካማ ጎን፣ የምትወደውንና የምትጠላውን ነገር እንዲሁም አመለካከቷንና ስሜቷን ግምት ውስጥ ያስገባል ማለት ነው። አሳቢ ባል እሱና ሚስቱ የባሕርይ ልዩነት እንዳላቸው ይገነዘባል። ‘ጸሎቱ እንዳይደናቀፍ’ ተገቢውን አሳቢነት ያሳያታል። (1 ጴጥሮስ 3:7) አንድ ባል ለሚስቱ በሴትነቷ የሚገባትን አክብሮት ሳይሰጣት ቢቀር ከአምላክ ጋር ያለውን ዝምድና አደጋ ላይ ይጥላል። በግልጽ ማየት እንደሚቻለው የአምላክ ቃል ሴቶችን ዝቅ አያደርግም። ከዚህ ይልቅ ያከብራቸዋል።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

© Christie’s Images Limited 1997