በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘በዘጠኝ ዓመቱ ልጅ ምክንያት’

‘በዘጠኝ ዓመቱ ልጅ ምክንያት’

‘በዘጠኝ ዓመቱ ልጅ ምክንያት’

ቪየስዋቫ የምትባል በደቡብ ፖላንድ የምትኖር ሴት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቷ በመጡ ቁጥር መስማት እንደማትፈልግ በትሕትና በመግለጽ ትሸኛቸው ነበር። አንድ ቀን የዘጠኝ ዓመቱ ሳሙኤል ከእናቱ ጋር ሆኖ ወደ ቤቷ መጣ። በዚህ ጊዜ ግን መልእክቱን ለመስማት ወሰነች፤ ከዚያም በምድር ላይ ስለምትቋቋመው ገነት የሚገልጽ መጽሔት ወሰደች።

የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት መታሰቢያ ቀርቦ ስለነበር ሳሙኤል፣ ቪየስዋቫን በዚህ ልዩ በዓል ላይ እንድትገኝ ሊጋብዛት ፈለገ። ስለዚህ ከእናቱ ጋር ሆኖ ተመልሶ በመሄድ የመጋበዣ ወረቀት ሰጣት። ቪየስዋቫ ልጁ ጥሩ አለባበስ እንዳለው ስትመለከት፣ ትንሽ እንዲጠብቋት ጠየቀቻቸውና ወደ ውስጥ ገብታ ልብሷን ቀይራ ተመለሰች። ከዚያም ሳሙኤልን በደንብ አዳመጠችው፤ በመታሰቢያው ላይ እንድትገኝ ያቀረበላትን ግብዣ የተቀበለች ሲሆን “ብቻዬን ልምጣ ወይስ ከባለቤቴ ጋር?” ብላ ጠየቀችው። አክላም “ባለቤቴ ባይመጣ እንኳ እኔ እመጣለሁ። ሳሙኤል፣ ለአንተ ስል እመጣለሁ” አለችው። ቃሏን ጠብቃ በመታሰቢያው በዓል ላይ በመገኘቷ ሳሙኤል በጣም ተደሰተ።

የመታሰቢያው ንግግር ሲቀርብ ሳሙኤል ከቪየስዋቫ አጠገብ ተቀምጦ ውይይት የሚደረግባቸውን ጥቅሶች እያወጣ ያሳያት ነበር። ይህም በጣም አስገረማት። በመታሰቢያው በዓል የተደሰተች ሲሆን ጥልቅ መንፈሳዊ ነገሮች በቀላል አገላለጽ ሲብራሩ በመስማቷ አመስጋኝነቷን ገለጸች። ጉባኤው ባደረገላት የሞቀ አቀባበልና ባሳያት ደግነት ልቧ ተነካ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቪየስዋቫ ለመንፈሳዊ ነገሮች ያላት አድናቆት እያደገ ከመሆኑም በላይ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር አዘውትራ መሰብሰብ ጀምራለች። በቅርቡ እንዲህ ስትል ተናግራለች:- “ከዚህ ቀደም ቤቴ ስትመጡ ሳላዳምጣችሁ መቅረቴ ያሳፍረኛል። አሁንም ቢሆን መልእክታችሁን ያዳመጥኩት በዚህ የዘጠኝ ዓመት ልጅ ማለትም በሳሙኤል ምክንያት እንደሆነ አልሸሽግም።”

በፖላንድ እንደሚኖረው እንደ ሳሙኤል ሁሉ ሌሎች ብዙ ወጣት የይሖዋ ምሥክሮችም በንግግራቸውና በመልካም ጠባያቸው አምላክን እያወደሱት ነው። አንተም ወጣት ከሆንክ ቅን ሰዎች ለመንፈሳዊ ነገሮች ጉጉት እንዲያድርባቸው ልትረዳቸው ትችላለህ።