በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የክርስቶስን ተቃዋሚ ለይቶ ማወቅ ያስፈለገው ለምንድን ነው?

የክርስቶስን ተቃዋሚ ለይቶ ማወቅ ያስፈለገው ለምንድን ነው?

የክርስቶስን ተቃዋሚ ለይቶ ማወቅ ያስፈለገው ለምንድን ነው?

ከረጅም ዓመታት በፊት አንድ ሐዋርያ “እንደሰማችሁትም የክርስቶስ ተቃዋሚ ይመጣል” በማለት በመንፈስ ተገፋፍቶ ጽፎ ነበር። (1 ዮሐንስ 2:18) እነዚህ ቃላት ምንኛ ትኩረት የሚስቡ ናቸው! ለበርካታ ዓመታት ሰዎች የዚህን ጥቅስ ትርጉም ለማወቅ ጥረት አድርገዋል። የክርስቶስ ተቃዋሚ ማን ነው? የሚመጣውስ መቼ ነው? በሚመጣበት ጊዜስ ምን ያደርጋል?

ለፉት ዘመናት የክርስቶስ ተቃዋሚ ተብለው የተወነጀሉ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ቀደም ባሉት ጊዜያት “የክርስቶስ ተቃዋሚ” የሚለው ስም ለአይሁዳውያን፣ ለካቶሊክ ጳጳሳት እንዲሁም ለሮም ንጉሠ ነገሥታት ተሰጥቷል። ለምሳሌ ያህል ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ፍሬደሪክ (1194-1250) ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጎን ሆነው በመስቀል ጦርነት እንደማይካፈሉ ሲናገሩ ሊቀ ጳጳስ ግሪጎሪ ዘጠነኛ፣ ንጉሡን የክርስቶስ ተቃዋሚ ብለው ከመጥራታቸውም በላይ አውግዘዋቸዋል። የግሪጎሪ ተተኪ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ኢኖሰንት አራተኛም፣ ዳግማዊ ፍሬደሪክን በድጋሚ አውግዘዋቸዋል። ንጉሠ ነገሥት ፍሬደሪክም ቢሆኑ ሊቀ ጳጳስ ኢኖሰንትን የክርስቶስ ተቃዋሚ ብለዋቸዋል።

“የክርስቶስ ተቃዋሚ” የሚለውን ሐረግ የተጠቀመ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ ሐዋርያው ዮሐንስ ብቻ ነው። በስሙ በተጠሩት ሁለት ደብዳቤዎች ላይ፣ ቃሉ በነጠላም ሆነ በብዙ ቁጥር አምስት ጊዜ ተጠቅሶ ይገኛል። እነዚህ ቃላት የሚገኙባቸው ጥቅሶች በሚቀጥለው ገጽ ላይ ባለው ሣጥን ውስጥ ተዘርዝረዋል። ከእነዚህ ጥቅሶች በመነሳት የክርስቶስ ተቃዋሚ፣ ሰዎች ከክርስቶስና ከአምላክ ጋር ያላቸውን ዝምድና ለማበላሸት ቆርጦ የተነሳ ሐሰተኛና አታላይ ነው ብሎ መደምደም ይቻላል። በመሆኑም ሐዋርያው፣ ክርስቲያን ወንድሞቹን እንዲህ በማለት አስጠንቅቋቸዋል:- “ወዳጆች ሆይ፤ መንፈስን ሁሉ አትመኑ፤ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፤ ምክንያቱም ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት ወደ ዓለም ወጥተዋልና።”—1 ዮሐንስ 4:1

ኢየሱስም ቢሆን አታላዮች ወይም ሐሰተኛ ነቢያት እንደሚመጡ ሲያስጠነቅቅ እንዲህ በማለት ተናግሯል:- “በውስጣቸው ነጣቂ ተኲሎች ሆነው ሳሉ የበግ ለምድ ለብሰው መካከላችሁ [ይገባሉ]። . . . ከፍሬያቸው [ወይም፣ ከሥራቸው] ታውቋቸዋላችሁ።” (ማቴዎስ 7:15, 16) ኢየሱስም ተከታዮቹን ስለ ክርስቶስ ተቃዋሚ እያስጠነቀቃቸው ነበር? ይህን ክፉ የሆነ አታላይ እንዴት ለይቶ ማወቅ እንደሚቻል ቀጥለን እንመልከት።