በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የገና በዓል ወዴት እያመራ ነው?

የገና በዓል ወዴት እያመራ ነው?

የገና በዓል ወዴት እያመራ ነው?

ኤስ ኒውስ ኤንድ ዎርልድ ሪፖርት  የተባለው መጽሔት፣ የዛሬ አሥር ዓመት በታኅሣሥ ወር እትሙ ላይ “የገና በዓልን ፍለጋ” የሚል የሽፋን ርዕስ ይዞ ወጥቶ ነበር። ጽሑፉ የገና በዓል “እየጠራና ከንግድ እየራቀ” መሆን አለመሆኑን በተመለከተ ያሰፈረው ሐሳብ ነበር። ታዲያ የገና በዓል እየጠራና ከንግድ እየራቀ ነው?

መጽሔቱ፣ እንዲህ ይሆናል ብለን መጠበቅ የሌለብን ለምን እንደሆነ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል:- “ቆስጠንጢኖስ . . . የሮም ንጉሠ ነገሥት እስከሆነበት እስከ አራተኛው መቶ ዘመን ድረስ የክርስቶስ ልደት መከበሩን የሚገልጽ ምንም ማስረጃ አናገኝም።” ይህም “ኢየሱስ የተወለደበትን ቀን ማንም ሰው በእርግጠኝነት እንደማያውቀው በተወሰነ መልኩም ቢሆን” ያሳያል። ይህ መጽሔት በመቀጠል “የወንጌል ዘገባዎች ወሩንና ቀኑን ሊጠቅሱ ይቅርና ዓመቱን እንኳ አልተናገሩም” ብሏል። የቴክሳስ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ ጸሐፊ እንደተናገሩት ደግሞ “የጥንቶቹ ክርስቲያኖች ልደቱን የማክበር ፍላጎት አልነበራቸውም።”

መጽሔቱ “ግምታዊ ሐሳብ” በሚለው ንዑስ ርዕስ ሥር “ቤተ ክርስቲያኒቷ ታኅሣሥ 25ን እንዴት እንደመረጠች” አብራርቷል። “በዓሉ [የተጀመረው] ሳተርናሊያን እና ሌሎች አረማዊ በዓላትን ወደ ‘ክርስቲያናዊ በዓልነት’ ለመለወጥ ታስቦ ነው የሚለው አመለካከት በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት አግኝቷል” ብሏል። “የቤተ ክርስቲያን መሪዎች፣ ገናን ሰዎች ቀድሞዉንም በዓል በሚያከብሩበት በታኅሣሥ ወር መጨረሻ ላይ እንዲውል በመወሰን የመድኃኒታችን ልደት በሰፊው እንዲከበር አድርገዋል።” በ19ኛው መቶ ዘመን አጋማሽ ላይ ሰዎች ስጦታ በመግዛትና በመስጠት ላይ ትኩረት ማድረግ ጀመሩ። “አዲስ የመጣው በገና በዓል ላይ ስጦታ የመለዋወጥ ልማድ የሀብት ማካበቻ ምንጭ በመሆኑ ብዙም ሳይቆይ ነጋዴዎችና የማስታወቂያ ሠራተኞች ወቅቱን ማስተዋወቅ ጀመሩ።”

በመሆኑም የገና በዓል ከጠራው ክርስትና እየራቀ ይሄዳል እንጂ ሌላ የተሻለ አቅጣጫ ይከተላል ብሎ ለመጠበቅ የሚያበቃ ምንም ምክንያት የለም። ዘመናዊው የገና በዓል “በተጧጧፈ የንግድ እንቅስቃሴ” የተሞላ ቢሆንም እውነተኛ ክርስቲያኖች የኢየሱስን ልደት ለማክበር ፈጽሞ አስበው አያውቁም። ከዚህ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስ ትኩረት የሚያደርገው ክርስቶስ በመሞትና ትንሣኤ አግኝቶ ወደ ሰማይ በማረግ ባቀረበው ቤዛ ላይ ነው። (ማቴዎስ 20:28) ይህ ደግሞ አሁንም ሆነ ወደፊት ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነገር ነው።