በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለማንበብ ቀላል ነው፤ ትርጉሙ ግን ትክክለኛ ነው?

ለማንበብ ቀላል ነው፤ ትርጉሙ ግን ትክክለኛ ነው?

ለማንበብ ቀላል ነው፤ ትርጉሙ ግን ትክክለኛ ነው?

በመስከረም 2005 የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን የ100 ደቂቃ መጽሐፍ ቅዱስ የተባለውን እትም መውጣት በሙሉ ድጋፍ አጽድቋል። በ100 ደቂቃ እንዲነበብ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍትን እያንዳንዳቸው አንድ ገጽ ባላቸው 17 ክፍሎች ሲያጠናቅራቸው የግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍትን ደግሞ እንዲሁ አንድ ገጽ ባላቸው 33 ክፍሎች አጠቃሏቸዋል፤ ይህን እትም የገመገሙ አንድ ሰው “አሰልቺ” ብለው የጠሯቸው ሌሎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከዚህ መጽሐፍ ወጥተዋል። አዎን፣ ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ ቀላል ነው፤ ትርጉሙ ግን ትክክለኛ ነው?

ከዚህ እትም ውስጥ ይሖዋ የሚለው መለኮታዊ ስም ከመውጣቱም በተጨማሪ ሌሎች ስህተቶችም እንዳሉ ጠንቃቃ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ልብ ማለት ይችላሉ። (ዘፀአት 6:3 የ1879 ትርጉም) ለምሳሌ ክፍል 1፣ አምላክ “ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ ፈጠረ” ይላል። ይሁን እንጂ ዘፍጥረት 1:1 “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን ፈጠረ” በማለት ሐሳቡን ያስቀምጠዋል። ከዚያም ጥንታዊው ቅጂ የተለያዩ የፍጥረት ሥራዎች በምድር ላይ እንደተከናወኑና እነዚህም በስድስት “ቀናት” ወይም በተወሰነ ጊዜ ውስጥ እንደተጠናቀቁ ይገልጻል። በኋላም ዘፍጥረት 2:4 (የ1954 ትርጉም) “እግዚአብሔር አምላክ ሰማይንና ምድርን ባደረገ ቀን” በማለት ጠቅላላ የፍጥረት ሥራ የተከናወነበትን ጊዜ ጠቅለል አድርጎ ገልጾታል።

ይህ የ100 ደቂቃ መጽሐፍ ቅዱስ፣ “[ከአምላክ] አገልጋዮች አንዱ የሆነውና . . . የሰው ዘሮችን የመክሰስ ኃላፊነት የተሰጠው ሰይጣን” ታማኝ በነበረው ኢዮብ ላይ ጥቃት እንዳደረሰበት ይገልጻል። እዚህ ላይ ያለውን ስህተት ልብ ብለሃል? “ሰይጣን” የሚለው ቃል “ተቃዋሚ” የሚል ትርጉም አለው። በመሆኑም ሰይጣን የአምላክ አገልጋይ ሳይሆን የአምላክ ዋነኛ ጠላት እንዲሁም ራሱን የሰው ልጆች ከሳሽ ያደረገ አካል ነው።—ራእይ 12:7-10

በዚህ የ100 ደቂቃ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኘው የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ክፍልስ ምን ለማለት ይቻላል? ኢየሱስ ስለ በጎችና ፍየሎች በሰጠው ምሳሌ ላይ “ምንም ያህል ዝቅተኛ ቢሆን ማንኛውንም ሰው” ለሚረዱ ግለሰቦች ክርስቶስ ሞገሱን እንደሚያሳያቸው ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፤ ሆኖም ኢየሱስ እዚህ ላይ የተናገረው የእርሱን ፈለግ ተከትለው ለሚሄዱ ታማኝ ተከታዮቹ ማለትም ‘ለወንድሞቹ’ መልካም የሚያደርጉትን እንደሚባርካቸው ነው። (ማቴዎስ 25:40) ይኸው መጽሐፍ ቅዱስ የራእይ መጽሐፍን ጠቅለል አድርጎ ባስቀመጠበት ክፍል ላይ “ታላቂቱ ባቢሎን ማለትም ሮም ሙሉ በሙሉ ትጠፋለች” ይላል። ይሁን እንጂ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የመጀመሪያው ቅጂ ስለ “ታላቂቱ ባቢሎን” ማንነት የሚሰጠው ሐሳብ እንዲህ ዓይነቱን መግለጫ እንደማይደግፍ ያውቃሉ።—ራእይ 17:15 እስከ 18:24

ፈጣሪያችንን ለማወቅም ሆነ ዓላማውን ለመረዳት ለሚፈልጉ ሰዎች ሙሉውን መጽሐፍ ቅዱስ ከማንበብ የተሻለ ነገር የለም። እርግጥ ነው፣ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ከ100 ደቂቃ በላይ ይፈጃል፤ ይሁን እንጂ እንዲህ ማድረጉ በዋጋ የማይተመን በረከት ያስገኛል። (ዮሐንስ 17:3) መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ የሚጠይቀውን ጥረት በማድረግ በረከት ለማጨድ ያብቃህ።—2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17