በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አሞጽ የባሉጥ ፍሬ ለቃሚ ወይስ ወጊ?

አሞጽ የባሉጥ ፍሬ ለቃሚ ወይስ ወጊ?

አሞጽ የባሉጥ ፍሬ ለቃሚ ወይስ ወጊ?

በዘጠነኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት የጥጃ አምልኮ ካህን የነበረው ክፉው አሜስያስ ነቢዩ አሞጽን በእስራኤል ትንቢት እንዳይናገር አስጠንቅቆት ነበር። አሞጽ ግን እንዲህ በማለት ተቃውሞውን ገለጸ:- “እኔ እረኛና የባሉጥ ፍሬ ለቃሚ [“ወጊ፣” NW] ነኝ . . . እግዚአብሔር ግን የበግ መንጋ ከምጠብቅበት ቦታ ወስዶ፣ ‘ሂድና ለሕዝቤ ለእስራኤል ትንቢት ተናገር’ አለኝ።” (አሞጽ 7:14, 15) አዎን፣ አሞጽ ነቢይ የሆነው ራሱን ሾሞ ሳይሆን ይሖዋ ነቢይ አድርጎ ስለ ላከው ነበር። ሆኖም አሞጽ የባሉጥ ፍሬ “ወጊ” እንደሆነ ሲናገር ምን ማለቱ ነበር?

ወጊ ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል በአዲስ ዓለም ትርጉም ውስጥ የሚገኘው በዚህ ጥቅስ ላይ ብቻ ነው። ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የባሉጥ ፍሬ “ወጊ” ከማለት ይልቅ “ለቃሚ፣” “አራሽ” ወይም “አምራች” የሚሉትን ቃላት ተጠቅመዋል። ይሁን እንጂ ኢኮኖሚክ ቦታኒ የተባለው መጽሔት እንደሚገልጸው የዕብራይስጡ ቃል የባሉጥን ፍሬ የሚያመርት ሰው የሚያከናውነውን ለየት ያለ ሥራ ስለሚያመለክት ትክክለኛው ትርጉም ‘መብሳት’ ነው።

በግብጽና በቆጵሮስ የባሉጥን ፍሬ በመውጋትም ሆነ በመብሳት ፍሬውን በትንሹ መሰንጠቅ ከጥንትም ጀምሮ የታወቀ ነበር። በአሁኗ እስራኤል ሌሎች የባሉጥ ዝርያዎች በመኖራቸው የባሉጥን ፍሬ መውጋትም ሆነ መብሳት የተለመደ አይደለም። ሆኖም በአሞጽ ዘመን በእስራኤል የነበሩት የባሉጥ ዝርያዎች ከግብጽ የመጡ በመሆናቸው ይህን ፍሬ መውጋት የተለመደ ነበር።

የባሉጥን ፍሬ መውጋት፣ ፍሬው ውኃ እንዲመጥና ፈሳሽ ያለው እንዲሆን ሳያደርገው አይቀርም። በተጨማሪም ፍሬው ቶሎ እንዲበስል የሚረዳው ኤትሊን የተባለ ጋዝ እንዲፈጠር ስለሚረዳ ፍሬው ትልቅና ጣፋጭ እንዲሆን ያደርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ ፍሬው ቶሎ ስለሚበስል በትል እንዳይጠቃ ይረዳዋል።

አሞጽ፣ እረኛና የባሉጥ ፍሬ ወጊ እንዲሁም ዝቅተኛ ገቢ ካለው ቤተሰብ የመጣ ሰው ቢሆንም ጠላቶቹ በሰነዘሩት ዛቻ አልተሸበረም። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ በእስራኤል ላይ ስለሚያመጣው የቅጣት ፍርድ የሚናገረውን መልእክት በድፍረት አውጇል። በዛሬው ጊዜም በሰዎች ዘንድ የማይወደድ መልእክት ለሚናገሩት የአምላክ አገልጋዮች አሞጽ እንዴት ያለ ጥሩ ምሳሌ ነው!—ማቴዎስ 5:11, 12፤ 10:22