በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘በግድ አለችን’

‘በግድ አለችን’

‘በግድ አለችን’

በምሥራቁ ዓለም እንግዳን መቀበል የተለመደ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ በሕንድ፣ አንዳንድ ቤተሰቦች በድንገት ለመጣባቸው እንግዳ ምግባቸውን አሟጥጠው በመስጠት ጦማቸውን ሊያድሩ ይችላሉ። በኢራን የምትኖር አንዲት እናት ደግሞ እንግዳ በማንኛውም ሰዓት ቢመጣ የምታቀርበው እንዳታጣ ሁልጊዜ ማቀዝቀዣውን በምግብ ትሞላዋለች።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ብዙ ሰዎችም እንዲህ የመሰለውን የልግስና መንፈስ አሳይተዋል። በዚህ ረገድ የመቄዶንያ ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው በፊልጵስዩስ ትኖር የነበረችው ልድያ ግሩም ምሳሌ ትሆናለች። ልድያ ወደ ይሁዲነት ከተለወጡት ሰዎች መካከል ሳትሆን አትቀርም። በአንድ የሰንበት ቀን ሐዋርያው ጳውሎስና የጉዞ ጓደኞቹ፣ ልድያን ጨምሮ አንዳንድ ሴቶች ፊልጵስዩስ አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ወንዝ አጠገብ ተሰብስበው አገኟቸው። ጳውሎስ የሚናገረውን ትሰማ ዘንድ ይሖዋ የልድያን ልብ ከፈተላት። በዚህም ምክንያት እርሷና ቤተሰቦቿ ተጠመቁ። ከዚያም ልድያ እንግዶቹን “በጌታ ማመኔን በርግጥ ከተረዳችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ጥቂት ተቀመጡ” በማለት ለመነቻቸው። የጳውሎስ የጉዞ ባልደረባ የነበረው ሉቃስ ሁኔታውን ሲገልጽ “አጥብቃ ለመነችን [“በግድም አለችን፣” የ1954 ትርጉም]” በማለት ጽፏል።—የሐዋርያት ሥራ 16:11-15

እንደ ልድያ ሁሉ በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖችም ተጓዥ የበላይ ተመልካቾችንና ሚስቶቻቸውን ጨምሮ ለእምነት ባልንጀሮቻቸው የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ያሳያሉ። ጋባዦቹ ወንድሞቻቸውን ወደ ቤታቸው እንዲመጡ ‘ግድ ይሏቸዋል።’ እንግዶችን መቀበላቸው የሚያንጹ ጭውውቶችን ለማድረግና መንፈሳዊ የሆኑ ወዳጆች ለማፍራት ያስችላቸዋል። አብዛኞቹ የይሖዋ ምሥክሮች አነስተኛ የገቢ ምንጭ ያላቸው ቢሆኑም ‘እንግዶችን ይቀበላሉ።’ (ሮሜ 12:13፤ ዕብራውያን 13:2) የለጋስነት መንፈስ ማሳየታቸው ደስታ ይሰጣቸዋል። በእርግጥም ኢየሱስ “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው” ማለቱ ትክክል ነው።—የሐዋርያት ሥራ 20:35