በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በመከራ በተሞላው በዚህ ዓለም ውስጥ ያለ ስጋት መኖር ትችላላችሁ!

በመከራ በተሞላው በዚህ ዓለም ውስጥ ያለ ስጋት መኖር ትችላላችሁ!

በልዩ የሕዝብ ንግግር ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል

በመከራ በተሞላው በዚህ ዓለም ውስጥ ያለ ስጋት መኖር ትችላላችሁ!

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተው ይህ ንግግር በዓለም ዙሪያ ከ230 በሚበልጡ አገሮች ይቀርባል። በብዙ ቦታዎች ንግግሩ የሚቀርበው እሁድ ሚያዝያ 7, 1999 (ሚያዝያ 15, 2007) ነው። እርስዎስ ከዚህ ንግግር ምን ትምህርት ማግኘት ይችላሉ? በንግግሩ ላይ ከሚቀርቡት ትምህርቶች መካከል ጥቂቶቹን እንመልከት:-

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሥጋት እንዲያድርባቸው የሚያደርገው ምንድን ነው?

የደኅንነት ስሜት የጠፋው በተለይ ከመቼ ጀምሮ ነው?

እውነተኛ ደኅንነት የሚገኘው ከየትና እንዴት ነው?

በአሥር ሺዎች በሚቆጠሩ ቦታዎች የሚቀርበውን ይህን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ጠቃሚ ንግግር በማዳመጥ ከላይ ላሉት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ይችላሉ። በአብዛኞቹ ቦታዎች ንግግሩ የሚቀርበው በይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ነው። በአካባቢዎ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ንግግሩ የሚቀርብበትን ቦታና ሰዓት ሊነግሩዎት ፈቃደኞች ናቸው። ወቅታዊና አበረታች በሆነው በዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንግግር ላይ እንዲገኙ ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልዎታለን።