በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአካል ጉዳተኛ ቢሆንም የማገልገል ጉጉት አለው

የአካል ጉዳተኛ ቢሆንም የማገልገል ጉጉት አለው

የአካል ጉዳተኛ ቢሆንም የማገልገል ጉጉት አለው

ሊዮናርዶን ለመጀመሪያ ጊዜ ስታየው በግንባታ ሥራ ላይ መሳተፍ የሚችል ሰው አድርገህ አትመለከተው ይሆናል። ከዚህ በፊት በሥራ ላይ እያለ በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ ምክንያት ሁለት እጆቹን አጥቷል። ሊዮናርዶ የአካል ጉዳተኛ ቢሆንም እንኳ በፎቶግራፉ ላይ እንደምታየው በአካሁትላ፣ ኤል ሳልቫዶር በሚካሄድ አንድ የግንባታ ሥራ ላይ በትጋት እየተካፈለ ነው።

ሊዮናርዶ በዚህ ሥራ ላይ ለመካፈል የሚያስችሉትን መሣሪያዎች ሠርቷል። ቀኝ ክንዱን አካፋው ጫፍ ላይ በተሠራው የብረት ቀለበት ውስጥ በማስገባት ቆሻሻዎችን በዘዴ እየዛቀ ጋሪ ላይ ይጭናል። ጋሪውን ብቻውን መግፋት እንዲችል በእጀታዎቹ ላይ ቀለበቶች አያይዟል። በዚህ የግንባታ ሥራ ላይ እንዲካፈል ያነሳሳው ምንድን ነው?

ሊዮናርዶ በአካባቢው ለሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች በሚሠራው የመንግሥት አዳራሽ ወይም የአምልኮ ቦታ ግንባታ ላይ መካፈል ስለፈለገ ነው። በግንባታ ሥራው ላይ ላለመካፈል በርካታ ምክንያቶችን ማቅረብ ይችል ነበር። የሙሉ ቀን ሰብዓዊ ሥራ ያለው ከመሆኑም በላይ የአካል ጉዳተኛ ነው፤ በዚያ ላይ የጉባኤ አገልጋይ ነው። ቢሆንም በዚህ የግንባታ ሥራ ላይ በመካፈል አምላክን ለማገልገል አቅሙ የፈቀደለትን ሁሉ ለማድረግ ፈለገ።

አንተስ አምላክን ለማገልገል እንዲህ ዓይነት ፍላጎት አለህ? ሊዮናርዶ የአካል ጉዳተኛ ነኝ ብሎ ወደኋላ ከማለት ይልቅ የማሰብ ችሎታውን ተጠቅሞ በሥራ ለመካፈል የሚያስችሉትን መሣሪያዎች ሠርቷል፤ ይህ ባይሆን ኖሮ በሥራው መካፈል አይችልም ነበር። በእርግጥም ሊዮናርዶ አምላክን ‘በፍጹም ሐሳቡ’ አገልግሏል። (ማቴዎስ 22:37) በዓለም ዙሪያ የይሖዋ ምሥክሮች የሚሰበሰቡባቸውን የመንግሥት አዳራሾች በመገንባቱ ሥራ ላይ የሚካፈሉ ሠራተኞች የአካል ጉዳተኛ ሆኑም አልሆኑ የፈቃደኝነት መንፈስ አላቸው። በስብሰባዎቻቸው ላይ ማንኛውም ሰው መገኘት የሚችል ሲሆን አንተም ተጋብዘሃል።