በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአየር ሁኔታን ከመተንበይ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነ ነገር

የአየር ሁኔታን ከመተንበይ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነ ነገር

የአየር ሁኔታን ከመተንበይ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነ ነገር

ብዙ አገሮች ‘ምሽት ላይ ሰማይ መቅላቱ መርከበኛን ማስደሰቱ፤ ጠዋት ላይ ሰማይ መቅላቱ መርከበኛን ማንቃቱ’ እንደሚሉት ያሉ ስለ አየር ሁኔታ የሚናገሩ አባባሎች አሏቸው። በዛሬው ጊዜ የሚገኙ የአየር ትንበያ ባለሙያዎችም የአየር ሁኔታ ለውጥ የሚከሰቱባቸውን ምክንያቶች በተመለከተ ሙያዊ ማብራሪያዎችን ይሰጣሉ።

በተመሳሳይም በኢየሱስ ዘመን የነበሩ ሰዎች የሰማዩን ሁኔታ በመመልከት ቀጥሎ ምን እንደሚከሰት የመናገር ልማድ ነበራቸው። ኢየሱስ ለአንዳንድ አይሁዳውያን እንዲህ ብሏቸው ነበር:- “ምሽት ላይ፣ ‘ሰማዩ ስለ ቀላ ብራ ይሆናል’ ትላላችሁ፤ ንጋት ላይም፣ ‘ሰማዩ ቀልቶአል፣ ከብዶአልም፤ ስለዚህ ዝናብ ይዘንባል’ ትላላችሁ። የሰማዩን ገጽታ ትለያላችሁ።” ቀጥሎም ኢየሱስ “ነገር ግን የዘመኑን ምልክት መለየት አትችሉም” በማለት አንድ ለየት ያለ ነገር ተናገረ።—ማቴዎስ 16:2, 3

‘የዘመኑ ምልክቶች’ የተባሉት ምን ነበሩ? ምልክቶቹ ኢየሱስ ከአምላክ የተላከ እውነተኛው መሲሕ መሆኑን የሚያሳዩት ግልጽ ማስረጃዎች ናቸው። ኢየሱስ ያደረጋቸው ነገሮች የሰማይን መቅላት ያህል በግልጽ የሚታዩ ነበሩ። ይሁን እንጂ አብዛኞቹ አይሁዳውያን የአየር ሁኔታን ከመተንበይ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነውን ነገር ይኸውም መሲሑ እንደመጣ የሚያሳዩትን ምልክቶች ችላ ብለዋል።

ዛሬም በተመሳሳይ ከግዑዙ ሰማይ ቀለም ይበልጥ ማስተዋል የሚኖርብን አንድ አስፈላጊ ምልክት አለ። ኢየሱስ ይህ ክፉ ዓለም እንደሚጠፋና የተሻለ ዓለም እንደሚመጣ አስቀድሞ ተናግሯል። አንድ ላይ ተቀናጅተው ይህ ለውጥ መቅረቡን የሚያሳዩ በርካታ ምልክቶችን ጠቅሷል። ከምልክቶቹ መካከል ዓለም አቀፍ ይዘት ያለው ጦርነትና ረሃብ ይገኙበታል። ኢየሱስ የእነዚህ ምልክቶች መታየት አምላክ ጣልቃ የሚገባበት ጊዜ መቃረቡን እንደሚጠቁም ተናግሯል።—ማቴዎስ 24:3-21

ታዲያ ‘የዘመኑን ምልክቶች’ እያስተዋልክ ነው?