በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“አምላክን በስም ታውቀዋለህ?”

“አምላክን በስም ታውቀዋለህ?”

“አምላክን በስም ታውቀዋለህ?”

ይህ ጥያቄ በማዕከላዊ እስያ ደቡባዊ ምዕራብ ክፍል የምትኖርን የአንዲት ሴት የማወቅ ፍላጎት ቀስቅሶ ነበር። ጥያቄው የወጣው በመጋቢት 2004 የንቁ! መጽሔት እትም ሽፋን ላይ ነበር። ይህች ሴት ለመጽሔቱ አዘጋጆች እንዲህ በማለት ጽፋለች:- “መጽሔታችሁ የማረከኝ ገና ከጅምሩ ሲሆን ለጥሩ ሥነ ምግባር ትኩረት እንድሰጥ ረድቶኛል። ለሕይወት ያለኝ አመለካከት ይበልጥ አዎንታዊ እየሆነ መጥቷል። ለማገኘው ሰው ሁሉ ስለ አምላካችንና እርሱን ማወቅ ስለሚያስገኘው ሰላም እየተናገርኩ ነው።”

በበርካታ ቦታዎች እንዲያውም “እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ” ያሉ ሰዎች ይሖዋ የሚለውን መለኮታዊ ስም እያወቁ ነው። (የሐዋርያት ሥራ 1:8) ለምሳሌ በተርክሜን ቋንቋ የሖዋ የሚለው ስም፣ በዚሁ ቋንቋ በተዘጋጀ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዛት ይገኛል። መዝሙር 8:1 “ጌታችን ይሖዋ፣ ስምህ በምድር ሁሉ ላይ ምንኛ ግርማዊነትን የተላበሰ ነው!” ይላል።

ሴትየዋ ስለ ይሖዋ አምላክ ይበልጥ ለማወቅ ስለፈለገች ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም የሚል ርዕስ ያለው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር እንዲላክላት ጠይቃለች። አንተም አንድ የይሖዋ ምሥክር ይህንን ብሮሹር እንዲሰጥህ መጠየቅ ትችላለህ።