በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘በሰማይ የምትኖረው ታማኝ ምስክር’

‘በሰማይ የምትኖረው ታማኝ ምስክር’

‘በሰማይ የምትኖረው ታማኝ ምስክር’

ባለ ቅኔዎችና የሙዚቃ ግጥም ደራሲያን ጨረቃን የውበት ተምሳሌት አድርገው ሲገልጹ መስማት የተለመደ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ አንድ መዝሙር ውበቷ ‘እንደ ጨረቃ ደማቅ ስለሆነ’ አንዲት ሴት ይናገራል። (ማሕልየ መሓልይ 6:10) አንድ መዝሙራዊ ደግሞ ጨረቃን ‘በሰማይ የምትኖር ታማኝ ምስክር’ በማለት ማራኪ በሆነ መንገድ ገልጿታል። (መዝሙር 89:37) ስለ ጨረቃ የተሰጠው ይህ መግለጫ ምን ትርጉም አለው?

ጨረቃ አንዳች ሳታዛንፍ ምድርን በየ27.3 ቀናት አንድ ጊዜ ትዞራለች። በመሆኑም ጨረቃ ታማኝ መባሏ አስተማማኝነቷን ያመለክታል። ይሁን እንጂ መዝሙራዊው ይህን የተናገረው ከዚህ የበለጠ ትርጉም ስላለው ነገር አስቦ ሊሆን ይችላል። ጨረቃን “ታማኝ ምስክር” ሲል የጠራት ስለ አምላክ መንግሥት በዘመረው ትንቢታዊ መዝሙር ላይ ነው። ኢየሱስ ተከታዮቹን ስለዚህ መንግሥት እንዲጸልዩ አስተምሯቸዋል።—ማቴዎስ 6:9, 10

ከ3,000 ዓመታት በፊት ይሖዋ አምላክ የጥንቷ እስራኤል ንጉሥ ከሆነው ከዳዊት ጋር የመንግሥት ቃል ኪዳን ገብቶ ነበር። (2 ሳሙኤል 7:12-16) የዚህ ቃል ኪዳን ዓላማ ኢየሱስ ክርስቶስ የዳዊትን ዙፋን በመውረስ ለዘላለም ለመግዛት የሚያስችለውን ሕጋዊ መሠረት መጣል ነበር። (ኢሳይያስ 9:7፤ ሉቃስ 1:32, 33) መዝሙራዊው፣ የዳዊት ‘ዘር’ የሚወርሰውን ዙፋን አስመልክቶ እንዲህ ሲል ዘምሯል:- “በሰማይ ታማኝ ምስክር ሆና እንደምትኖረው፣ እንደ ጨረቃ እርሱ ለዘላለም ይመሠረታል።”—መዝሙር 89:36, 37

‘በሌሊት የምትሠለጥነው ብርሃን’ ማለትም ጨረቃ የክርስቶስ ግዛት ዘላለማዊ መሆኑን ለማሳየት ተስማሚ ምሳሌ ናት። (ዘፍጥረት 1:16) ዳንኤል 7:14 የክርስቶስን መንግሥት በተመለከተ “ግዛቱም ለዘላለም የማያልፍ ነው፤ መንግሥቱም ፈጽሞ የማይጠፋ ነው” ይላል። ጨረቃ፣ የክርስቶስን መንግሥትና ይህ መንግሥት ለሰው ልጆች የሚያመጣውን በረከት የምታስታውስ ምስክር ናት።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

ጨረቃ:- NASA photo