በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሥነ ጽሑፍ—በጥንቷ እስራኤል የነበረው ጠቀሜታ

ሥነ ጽሑፍ—በጥንቷ እስራኤል የነበረው ጠቀሜታ

ሥነ ጽሑፍ—በጥንቷ እስራኤል የነበረው ጠቀሜታ

ኢሊያድ እና ኦዲሲ በመባል የሚታወቁትን ሁለት ታላላቅ የግጥም መድብሎች አንብበሃቸው ታውቃለህ? ስለ ጥንት ግሪካውያን የጀግንነት ታሪክ የሚያወሱት እነዚህ ግጥሞች በዘጠነኛው ወይም በስምንተኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደተቀናበሩ ይገመታል። እነዚህ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች፣ ከእነሱ አስቀድሞ ከብዙ መቶ ዘመናት በፊት መጻፍ ከተጀመረው ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ሲወዳደሩ ምን ይመስላሉ? ዘ ጂዊሽ ባይብል ኤንድ ዘ ክርስቺያን ባይብል በሚል ርዕስ የተዘጋጀ አንድ ጥራዝ እንዲህ የሚል አስተያየት ሰጥቷል:- “መጽሐፍ ቅዱስ ከ429 ባላነሱ ቦታዎች ላይ ስለ መጻፍና በጽሑፍ ስለሚገኙ መዛግብት ይጠቅሳል። ይሁን እንጂ በኢሊያድ ግጥም ውስጥ ስለ መጻፍ የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን በኦዲሲ ውስጥ ደግሞ ጭራሹኑ የለም።”

ዚ ኦክስፎርድ ኢንሳይክሎፒዲያ ኦቭ አርኪኦሎጂ ኢን ዘ ኒር ኢስት የተባለው መጽሐፍ “በጥንት እስራኤላውያን ዘንድ ሥነ ጽሑፍና ሃይማኖት የማይነጣጠሉ ነገሮች የነበሩ ይመስላል” ብሏል። ለምሳሌ ያህል፣ የሕጉ ቃል ኪዳን በጽሑፍ እንዲሰፍር የተደረገ ሲሆን በኋላም ወንዶች፣ ሴቶችና ልጆች በተሰበሰቡበት በቋሚነት ይነበብ ነበር። በተጨማሪም ሕጉ በቡድንም ሆነ በግለሰብ ደረጃ ይነበብና ይጠና ነበር። የሊቨርፑል ዩኒቨርሲቲ አንጋፋ መምህር የሆኑት አለን ሚለርድ የሕጉን አንዳንድ ገጽታዎች ከመረመሩ በኋላ እንዲህ የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል:- “የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ሁሉም እስራኤላውያን ማንበብና መጻፍ እንደሚችሉ አድርገው ያስቡ እንደነበር በግልጽ ማየት ይቻላል።”—ዘዳግም 31:9-13፤ ኢያሱ 1:8 NW፤ ነህምያ 8:13-15፤ መዝሙር 1:2 NW

ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያኖች ለቅዱሳን መጻሕፍት ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖራቸው እንደሚገባ ሲገልጽ “በጽናትና ቅዱሳት መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ እንዲኖረን፣ ቀደም ብሎ የተጻፈው ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአል” ብሏል። አንተስ መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረህ በማንበብ ለመጽሐፉ አድናቆት እንዳለህ ታሳያለህ?—ሮሜ 15:4