በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አምላክ ክፋት እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?

አምላክ ክፋት እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?

አምላክ ክፋት እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?

ክፋትና መከራ ምን ያህል እንደበዛ ለማወቅ ሩቅ መሄድ አያስፈልግህም። ጦርነት የሰላማዊ ዜጎችንም ሆነ የወታደሮችን ሕይወት ይቀጥፋል። ወንጀልና ዓመጽ የተለመዱ ነገሮች ሆነዋል። በቅርቡ አንተም በደል ወይም ኢፍትሐዊ ድርጊት ተፈጽሞብህ ሊሆን ይችላል። ከምታያቸውና ከደረሱብህ ነገሮች በመነሳት ‘አምላክ ክፋት እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?’ ብለህ ሳትጠይቅ አትቀርም።

ይህን ጥያቄ ለመጠየቅ አንተ የመጀመሪያው ሰው አይደለህም። ከዛሬ 3,600 ዓመታት ገደማ በፊት ኢዮብ የተባለ አንድ ታማኝ የአምላክ አገልጋይ “ኀጢአተኞች [“ክፉ ሰዎች፣” የ1980 ትርጉም] ለምን በሕይወት ይኖራሉ?” ሲል ጠይቆ ነበር። (ኢዮብ 21:7) በሰባተኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት ይኖር የነበረው ነቢዩ ኤርምያስ ወገኖቹ ይፈጽሙት በነበረው የክፋት ድርጊት እጅግ በማዘኑ “የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል? የከዳተኞችስ ኑሮ ለምን ይሳካል?” በማለት ጠይቋል። (ኤርምያስ 12:1) ኢዮብም ሆነ ኤርምያስ አምላክ ጻድቅ መሆኑን ያውቁ ነበር። ያም ሆኖ ክፋት የበዛበት ምክንያት ጥያቄ ፈጥሮባቸዋል። አንተም በዚህ ሁኔታ ግራ ተጋብተህ ይሆናል።

አንዳንዶች በሰዎች ላይ ለሚደርሰው ክፋትና መከራ ተጠያቂው አምላክ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሌሎች ደግሞ እንደሚከተለው በማለት ይጠይቃሉ:- ‘አምላክ ኃያል፣ ጻድቅና አፍቃሪ ከሆነ ክፋትንና መከራን የማያስወግደው ለምንድን ነው? ክፋት እስከ ዛሬ እንዲኖር የፈቀደው ለምንድን ነው?’ የሚቀጥለው ርዕስ እነዚህን ጨምሮ ለሌሎች አስፈላጊ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

AP Photo/Adam Butler