በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትሑት መሆን ተፈታታኝ የሆነው ለምንድን ነው?

ትሑት መሆን ተፈታታኝ የሆነው ለምንድን ነው?

ትሑት መሆን ተፈታታኝ የሆነው ለምንድን ነው?

ብዙ ሰዎች በዛሬው ጊዜ ትሑት መሆን ዋጋ እንደሌለው ይሰማቸዋል። በኅብረተሰቡ ዘንድ ጎላ ብለው የሚታዩ ብሎም ስኬታማ የሚመስሉ ሰዎች፣ ከሌሎች ልቀው ለመታየት ሲሉ ማንኛውንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱና ኩሩዎች እንዲሁም እኔ ያልኩት ካልሆነ የሚሉ ናቸው። ብዙዎች የሚመኙት የባለጠጋና የታዋቂ ሰዎችን ሕይወት እንጂ የትሑታንን አይደለም። ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ያሉበት ደረጃ ላይ የደረሱት በጥረታቸው እንደሆነ በጉራ መናገር ይቀናቸዋል። እነዚህ ሰዎች ትሑት ከመሆን ይልቅ ባገኙት ስኬት በመኩራራት ለመመስገን ይፈልጋሉ።

አንድ ካናዳዊ ተመራማሪ በአገራቸው ውስጥ “የራስ ወዳድነትና ራስን ከፍ ከፍ የማድረግ ዝንባሌ ብቅ እያለ” መሆኑን ተናግረዋል። ሌሎች ደግሞ፣ በምንኖርበት ማኅበረሰብ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ኃላፊነታቸውን ከመወጣት ይልቅ ራሳቸውን ለማስደሰት ትልቅ ቦታ እንደሚሰጡና በዛሬው ጊዜ ስለ ራሳቸው ብቻ የሚያስቡ ሰዎች እየተበራከቱ እንዳሉ ይሰማቸዋል። እንደዚህ ዓይነት ዝንባሌ በሚታይበት ዓለም ውስጥ ትሕትና ማሳየት የሚበረታታ ባሕርይ ላይመስል ይችላል።

እርግጥ ነው፣ ትሑት ከሆኑ ሰዎች ጋር መኖር ቀላል በመሆኑ ሌሎች ትሕትና ቢያሳዩ ጥሩ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ይሁን እንጂ በዚህ ፉክክር በሞላበት ዓለም ውስጥ፣ አንዳንድ ሰዎች ትሑት ከሆኑ በሌሎች ዘንድ እንደ ደካማ እንዳይታዩ ይፈራሉ።

የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ በጊዜያችን ሰዎች “ትምክሕተኞች፣ ትዕቢተኞች” እንደሚሆኑ አስቀድሞ ተናግሯል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1, 2) ይህ ትንቢት እየተፈጸመ እንዳለ አይሰማህም? ትሑት መሆን ጥቅም ያለው ይመስልሃል? ወይስ ትሑት የሆነ ሰው እንደ ደካማ እንደሚታይና ሌሎች መጠቀሚያ እንደሚያደርጉት ይሰማሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ትሕትናን ከፍ አድርገን እንድንመለከትና ይህን ባሕርይ እንድናዳብር የሚያነሳሳን በቂ ምክንያት እንዳለ ይገልጽልናል። የአምላክ ቃል ይህን ባሕርይ በተመለከተ ሚዛናዊና አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖረን የሚረዳን ከመሆኑም በላይ እውነተኛ ትሕትና የድክመት ሳይሆን የጥንካሬ ምልክት መሆኑን ያሳያል። የሚቀጥለው ርዕስ እንዲህ የምንልበትን ምክንያት ያብራራል።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ያገኘነውን ስኬት በተመለከተ ምን ሊሰማን ይገባል?