በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዓለም አቀፋዊ አንድነት እንዲኖር ማድረግ ይቻል ይሆን?

ዓለም አቀፋዊ አንድነት እንዲኖር ማድረግ ይቻል ይሆን?

ዓለም አቀፋዊ አንድነት እንዲኖር ማድረግ ይቻል ይሆን?

ዓለማችን ወደ ሰላም እያመራች ነው ወይስ በጥፋት አፋፍ ላይ ትገኛለች? ሁለቱም ሁኔታዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል።

በአንድ በኩል አንዳንድ የዓለም መሪዎች ዓለም አቀፋዊ ሰላም ሊገኝ እንደሚችል በእርግጠኝነት ይናገራሉ፤ ምናልባትም እንዲህ የሚሉት ሌሎቹ አማራጮች ለማሰብ እንኳ ስለሚያስፈሯቸው ሊሆን ይችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ብዙዎች እንደሚከተሉት ያሉት ጥያቄዎች ያስጨንቋቸዋል:- ጅምላ ጨራሽ የጦር መሣሪያዎች ያሏቸው ብሔራት የትኞቹ ናቸው? እነዚህ ብሔራት ባሏቸው የጦር መሣሪያዎች ይጠቀሙ ይሆን? እንዲህ ቢያደርጉ ምን ሊፈጠር ይችላል?

ፉክክርና ጭፍን ጥላቻ አንድነት እንዳይኖር ዋነኛ እንቅፋት ሆነው እንደቆዩ ታሪክ ያሳያል፤ ብዙውን ጊዜ ደግሞ ሃይማኖት ይህን ችግር ከማስወገድ ይልቅ እንዲባባስ አስተዋጽዎ አድርጓል። ጄምስ ሆት የተባሉ ጋዜጠኛ እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል:- “በሰዎች መካከል መከፋፈል የሚፈጥር ማንኛውም ነገር ለጥላቻ መንስኤ ሊሆን ይችላል፤ ሰዎችን ከሚከፋፍሉ ነገሮች ዋነኛው ደግሞ ሃይማኖት ነው። ሃይማኖት፣ ሰዎች ‘ጥሩ’ እንዲሆኑ ያደርጋል የሚል የተለመደ አመለካከት ቢኖርም አንዳንድ ሰዎች አሰቃቂ ድርጊቶችን እንዲፈጽሙ እንደሚያደርጋቸው ግልጽ ነው።” ስቲቨን ዋይንበርግ የተባሉ ደራሲም ተመሳሳይ አመለካከት አላቸው። “ጥሩ ሰዎች መጥፎ ነገር እንዲፈጽሙ ሊያደርጋቸው የሚችለው ሃይማኖት ብቻ ነው” በማለት ጽፈዋል።

ታዲያ ዓለማችን አንድነት ይኖራታል ብለን ተስፋ ማድረግ እንችላለን? አዎን፣ ተስፋ የምናደርግበት በቂ ምክንያት አለን! ሆኖም ዓለም አቀፋዊ አንድነት የሚገኘው የሰው ልጆች በሚያደርጉት ጥረት ወይም የሰው ልጆች በመሠረቷቸው ሃይማኖቶች እንዳልሆነ ቀጥለን እንመለከታለን።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ዓለማችን እንደ ቦምብ ትፈነዳ ይሆን?