በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በማንበብ ተጠቅመሃል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

ክርስቲያናዊ ንጹሕ አቋማችንን መጠበቃችን በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ንጹሕ አቋማችንን መጠበቅ፣ በፍቅር ተነሳስተን የይሖዋን ሉዓላዊነት ለመደገፍ የሚያስችለን ከመሆኑም ሌላ ሰይጣን ውሸታም መሆኑን ለማረጋገጥ አጋጣሚ ይሰጠናል። ከዚህም በተጨማሪ ይሖዋ የሚፈርድልን ንጹሕ አቋማችንን መሠረት አድርጎ ነው፤ በመሆኑም እንዲህ ያለ አቋም መያዛችን ለተስፋችን በጣም አስፈላጊ ነው።—12/15 ገጽ 4-6

ኢየሱስ በአምላክ ዓላማ ውስጥ የሚጫወተውን ሚና የሚያመለክቱ አንዳንድ ስሞች የትኞቹ ናቸው?

አንድያ ልጅ። ቃል። አሜን። የአዲስ ኪዳን መካከለኛ። ሊቀ ካህናት። ተስፋ የተደረገበት ዘር።—12/15 ገጽ 15

ኤልያስ እየጸለየ ሳለ አገልጋዩን ወደ ባሕሩ እንዲመለከት መላኩ ትኩረታችንን የሚስበው ለምንድን ነው? (1 ነገ. 18:43-45)

ኤልያስ ስለ ውኃ ዑደት እውቀት ነበረው። ከባሕሩ በላይ የተፈጠረው ደመና በነፋስ እየተገፋ ወደ ምድር ከተወሰደ በኋላ ዝናብ ይሆናል።—1/1 ገጽ 15-16

በአገልግሎታችን የበለጠ ደስታ ለማግኘት ምን ማድረግ እንችላለን?

ሌሎችን ምን ያህል ልንጠቅማቸው እንደምንችል በማሰብ ልባችንን ማዘጋጀት እንችላለን። ምሥራቹን ስንሰብክ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት የማግኘት ግብ ሊኖረን ይገባል። በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ ያሉ ሰዎች ለሃይማኖት ግድ የለሾች ከሆኑ ትኩረታቸውን የሚስብ መግቢያ ለመጠቀም ጥረት ማድረግ እንችላለን።—1/15 ገጽ 8-10

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው የለምጽ በሽታ በዛሬው ጊዜ ምን ያመለክታል?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለምጽ ተብሎ የተጠራው የበሽታ ዓይነት በባክቴሪያ የሚተላለፍ ነበር። (ዘሌ. 13:4, 5) መጽሐፍ ቅዱስ፣ እንደሚገልጸው ይህ ዓይነቱ ለምጽ በልብስና በቤቶችም ላይ ሊወጣ ይችላል። ይህ ዓይነቱ ለምጽ ወይም “ደዌ” በአሁኑ ጊዜ ሻጋታ ወይም ሽበት ተብሎ የሚጠራውን ሊያመለክት ይችላል። (ዘሌ. 13:47-52)—2/1 ገጽ 19

የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት፣ አንድ ክርስቲያን ስለ ቀብር ሥነ ሥርዓቶች ባለው አመለካከት ላይ ምን ተጽዕኖ ሊኖረው ይገባል? ከቀብር ጋር በተያያዙ ልማዶች ረገድስ ምን እንዲያደርግ ሊያነሳሳው ይገባል?

አንድ ክርስቲያን የሚወደው ሰው ሲሞት ሐዘኑን የሚገልጽ ቢሆንም የሞቱ ሰዎች ምንም እንደማያውቁ ይገነዘባል። የማያምኑ ሰዎች ቢነቅፉትም እንኳ ሙታን በሕያዋን ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ ከሚለው እምነት ጋር ተያያዥነት ባላቸው ልማዶች አይሳተፍም። አንዳንድ ክርስቲያኖች ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ ሲሉ የቀብር ሥነ ሥርዓቶችን የሚመለከቱ መመሪያዎችን በጽሑፍ ያሰፍራሉ።—2/15 ገጽ 29-31

መዝሙር 1:1 እንደሚገልጸው ደስተኛ ለመሆን ልንርቃቸው የሚገቡን ሦስት ነገሮች ምንድን ናቸው?

በዚህ ጥቅስ ላይ ‘የክፉዎች ምክር፣’ ‘የኃጢአተኞች መንገድ’ እና ‘የፌዘኞች ወንበር’ ተጠቅሰዋል። ደስተኛ መሆን ከፈለግን በአምላክ ሕግ ከሚያፌዙ ወይም ሕጉን ችላ ከሚሉ ሰዎች መራቅ ይኖርብናል። ከዚህ በተቃራኒ በይሖዋ ሕግ ደስ መሰኘት ይገባናል።—3/1 ገጽ 17

‘የያሻር መጽሐፍ’ እንዲሁም ‘የይሖዋ የጦርነት መጽሐፍ’ ከጊዜ በኋላ የጠፉ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ናቸው? (ኢያሱ 10:13፤ ዘኍ. 21:14)

አይደሉም። እነዚህ መጻሕፍት የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች በማመሳከሪያነት የተጠቀሙባቸውና በአምላክ መንፈስ መሪነት ያልተጻፉ በጊዜው የነበሩ የታሪክ መዛግብት ሳይሆኑ አይቀሩም።—3/15 ገጽ 32

ዘመናዊው የላቲን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ምን የጎላ ለውጥ ተደርጎበታል?

በ1979 ጳጳስ ጆን ፖል ሁለተኛ፣ ኖቫ ቩልጋታ ለተባለው አዲስ የላቲን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም እውቅና ሰጡ። የዚህ መጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ እትም ያዋ የሚለውን መለኮታዊ ስም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ አስገብቶ ነበር። (ዘፀ. 3:15፤ 6:3) ሆኖም በ1986 ሁለተኛው እትም ሲወጣ ያዋ የሚለው ቃል ወጥቶ ዶሚነስ [ጌታ] የሚለው ቃል እንዲገባ ተደርጓል።—4/1 ገጽ 22