በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የእውነት ዘር ራቅ ወዳሉ አካባቢዎች ደረሰ

የእውነት ዘር ራቅ ወዳሉ አካባቢዎች ደረሰ

የእውነት ዘር ራቅ ወዳሉ አካባቢዎች ደረሰ

ሩሲያ ውስጥ ያለችው የቱቫ ሪፑብሊክ የምትገኘው በሳይቤሪያ ደቡባዊ ጫፍ ሲሆን በስተ ደቡብና በስተ ምሥራቅ ሞንጎሊያ ያዋስናታል። በቱቫ አብዛኞቹ ሰዎች የሚኖሩት በጣም ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች በመሆኑ የመንግሥቱን መልእክት ለእነዚህ ሰዎች ማድረስ አስቸጋሪ ነው። ይሁን እንጂ ከተወሰነ ጊዜ በፊት፣ ርቀው በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ በርከት ያሉ ሰዎች በአንድ ሴሚናር ላይ ለመካፈል የቱቫ ዋና ከተማ ወደሆነችው ወደ ኪዝል መጥተው ነበር። በኪዝል የምትኖር መሪያ የተባለች አቅኚ እነዚህ ሰዎች እንደሚመጡ ስታውቅ ይህ ሁኔታ ምሥራቹን ለእነሱ ለማካፈል ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ ተሰማት።

መሪያ እንዲህ ብላለች፦ “የማስተምርበት ትምህርት ቤት የአልኮል መጠጥና የአደገኛ ዕፆች ሱስ ያለባቸውን ሰዎች ለመርዳት ስለሚቻልባቸው መንገዶች ውይይት የሚደረግበት አንድ ሴሚናር አዘጋጀ። በቱቫ በጣም ርቀው ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ 50 ያህል ሰዎች በሴሚናሩ ላይ ለመገኘት መጥተው ነበር። ከእነዚህ መካከል መምህራን፣ የሥነ ልቦና ባለሞያዎች፣ የሕፃናት ደኅንነት መጠበቁን የሚከታተሉ ባለሞያዎች እና ሌሎች ሰዎች ይገኙበታል።” መሪያ፣ ሴሚናሩ ምሥራቹን ለመስበክ የሚያስችል ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ ቢሰማትም ይህን ማድረግ ለእሷ ቀላል አልነበረም። እንዲህ ብላለች፦ “በተፈጥሮዬ ዓይናፋር ስለሆንኩ መደበኛ ባልሆነ መንገድ መመሥከር ይከብደኛል። ያም ቢሆን በዚህ አጋጣሚ ተጠቅሜ መስበክ እንድችል ፍርሃቴን ለማሸነፍ ድፍረት እንዲሰጠኝ ወደ ይሖዋ ጸለይኩ።” ታዲያ መሪያ ተሳክቶላት ይሆን?

መሪያ በመቀጠል እንዲህ ስትል ተናግራለች፦ “ስለ ፎቢያ [ከመጠን ያለፈ ፍርሃት] የሚያወሳ አንድ ንቁ! መጽሔት አገኘሁ። ‘ይህ ርዕስ የሥነ ልቦና ባለሞያ የሆነን ሰው ትኩረት ሊስብ ይችላል’ ብዬ ስላሰብኩ መጽሔቱን ወደ ትምህርት ቤት ይዤው ሄድኩ። የዚያን ዕለት በሴሚናሩ ላይ ከሚካፈሉት መምህራን መካከል አንዷ ወደ ቢሮዬ ስትመጣ መጽሔቱን አሳየኋት። ሴትየዋ ደስ ብሏት መጽሔቱን የተቀበለችኝ ሲሆን እሷ ራሷ ፎቢያ እንዳለባት ነገረችኝ። በማግሥቱ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ ጥራዝ 1 ወሰድኩላት። ይህንንም መጽሐፍ በደስታ ተቀበለችኝ። የሴትየዋን ምላሽ ስመለከት ሌሎች መምህራንም ይህንን መጽሐፍ ሊወዱት እንደሚችሉ አሰብኩ። በመሆኑም የወጣቶች ጥያቄ የተባለውን መጽሐፍና ሌሎች ጽሑፎችን በካርቶን ሞልቼ ወደ ትምህርት ቤት ወሰድኩ።” ብዙም ሳይቆይ ካርቶኑ ባዶ ሆነ። መሪያ ስለ ሁኔታው ስትገልጽ እንዲህ ብላለች፦ “የወጣቶች ጥያቄ የሚለውን መጽሐፍ የሰጠኋት ሴት የሥራ ባልደረቦች የሆኑ በርካታ መምህራን ወደ ቢሮዬ በመምጣት ‘መጻሕፍት የሚታደሉት የት ነው?’ ብለው ጠየቁኝ።” የመጡት ወደ ትክክለኛው ቦታ ነበር!

ሴሚናሩ የሚያበቃው ቅዳሜ ቀን ነበር። በዚያ ዕለት መሪያ ሥራ ስለማትገባ ጽሑፎቹን በቢሮዋ ውስጥ ባሉ ጠረጴዛዎች ላይ ከደረደረች በኋላ ሰሌዳ ላይ እንዲህ ብላ ጻፈች፦ “ውድ መምህራን፣ ለራሳችሁም ሆነ ለምታውቋቸው ሰዎች ጽሑፎች መውሰድ ትችላላችሁ። ግሩም የሆነ ሐሳብ የያዙት እነዚህ ጽሑፎች በሥራችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ እንዲሁም የቤተሰብ ሕይወታችሁ ጠንካራ እንዲሆን ይረዷችኋል።” መሪያ ምን ውጤት አገኘች? “የዚያን ዕለት ወደ ቢሮዬ ስገባ መምህራኑ አብዛኞቹን ጽሑፎች እንደወሰዷቸው ተመለከትሁ። ወዲያውኑ ተጨማሪ መጻሕፍትና መጽሔቶችን አመጣሁ።” ሴሚናሩ ሲጠናቀቅ መሪያ 380 መጽሔቶችን፣ 173 መጻሕፍትን እንዲሁም 34 ብሮሹሮችን አበርክታ ነበር። በሴሚናሩ ላይ የተገኙት ሰዎች እነዚህን ጽሑፎች ይዘው ራቅ ብሎ ወደሚገኘው አካባቢያቸው ተመለሱ። መሪያ “የእውነት ዘር ራቅ ብለው ወደሚገኙት የቱቫ አካባቢዎች በመድረሱ በጣም ተደስቻለሁ!” ብላለች።—መክ. 11:6

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ካርታ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

ሩሲያ

የቱቫ ሪፑብሊክ