በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ትንሽ ብትሆንም ልቧ ትልቅ ነው

ትንሽ ብትሆንም ልቧ ትልቅ ነው

ትንሽ ብትሆንም ልቧ ትልቅ ነው

በቅርቡ፣ በብራዚል የምትኖር አንዲት የዘጠኝ ዓመት ልጅ ያጠራቀመችውን 43 ዶላር ሁለት ቦታ ከከፈለች በኋላ 18ቱን ዶላር የጉባኤውን ወጪ ለመሸፈን እንዲውል በመንግሥት አዳራሽ ውስጥ በሚገኘው የመዋጮ ሣጥን ውስጥ ጨመረችው። ቀሪውን 25 ዶላር ደግሞ ከአጭር ደብዳቤ ጋር ለይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ላከችው። ደብዳቤዋ እንዲህ ይላል:- “ይህንን መዋጮ የላክሁት ለዓለም አቀፉ ሥራ እንዲውል ነው። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ወንድሞችና እህቶች ምሥራቹን እንዲሰብኩ መርዳት እፈልጋለሁ። መዋጮውን ያደረግኩት ለይሖዋ ጥልቅ ፍቅር ስላለኝ ነው።”

የዚህች ትንሽ ልጅ ወላጆች የመንግሥቱን የስብከት ሥራ ለመደገፍ በግለሰብ ደረጃ አስተዋጽኦ የማድረግን አስፈላጊነት አስተምረዋታል። ከዚህም በተጨማሪ ‘ይሖዋን በሀብቷ ማክበር’ እንደሚገባት አሠልጥነዋታል። (ምሳሌ 3:9) ሁላችንም ልክ እንደዚህች ትንሽ ልጅ በአገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከመንግሥቱ ጋር በተያያዘ የሚካሄደውን ሥራ በቅንዓት እንደግፍ!