“ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለባችሁ ልታስቡበት ይገባል!”
“ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለባችሁ ልታስቡበት ይገባል!”
“እነዚህ ሁሉ ነገሮች እንዲህ የሚቀልጡ ከሆነ ቅዱስ ሥነ ምግባር በመከተልና ለአምላክ ያደራችሁ መሆናችሁን የሚያሳዩ ተግባሮች በመፈጸም ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለባችሁ ልታስቡበት ይገባል!”—2 ጴጥ. 3:11
1. የጴጥሮስ ሁለተኛ ደብዳቤ በዘመኑ ለነበሩ ክርስቲያኖች ወቅታዊ ማሳሰቢያ ነበር የምንለው ለምንድን ነው?
ሐዋርያው ጴጥሮስ በመንፈስ መሪነት ሁለተኛ ደብዳቤውን በጻፈበት ወቅት የክርስቲያን ጉባኤ ብዙ ስደት አሳልፎ ነበር፤ ይህ ሁኔታ ግን የጉባኤውን ቅንዓት አላቀዘቀዘውም ወይም እድገቱን አልገታውም። በመሆኑም ዲያብሎስ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ጊዜያት ውጤታማ ሆኖ ያገኘውን ሌላ ዘዴ ተጠቀመ። ጴጥሮስ እንደገለጸው ሰይጣን “አመንዝራ ዓይን” እንዲሁም “መጎምጀት የለመደ ልብ” ባላቸው ሐሰተኛ አስተማሪዎች አማካኝነት የአምላክን ሕዝቦች ለመበከል ጥረት እያደረገ ነበር። (2 ጴጥ. 2:1-3, 14፤ ይሁዳ 4) በዚህም የተነሳ ጴጥሮስ በሁለተኛ ደብዳቤው ላይ ክርስቲያኖች ታማኝነታቸውን እንዲጠብቁ ከልብ የመነጨ ማሳሰቢያ ሰጥቷቸዋል።
2. ሁለተኛ ጴጥሮስ ምዕራፍ 3 ትኩረት የሚያደርገው በምን ላይ ነው? ራሳችንን ምን ብለን ልንጠይቅ ይገባል?
2 ጴጥሮስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “በዚህ ድንኳን እስካለሁ ድረስ እናንተን በማሳሰብ ማነቃቃት ተገቢ ይመስለኛል፤ . . . ይህን ድንኳን ትቼ የምሄድበት ጊዜ እንደቀረበ አውቃለሁ። ስለዚህ እኔ ከሄድኩ በኋላ እነዚህን ነገሮች ሁልጊዜ ማስታወስ እንድትችሉ አቅሜ የፈቀደውን ሁሉ አደርጋለሁ።” (2 ጴጥ. 1:13-15) ጴጥሮስ የሚሞትበት ቀን እንደቀረበ ቢያውቅም የሰጠው ወቅታዊ ማሳሰቢያ ምንጊዜም እንዲታወስ ፈልጎ ነበር። በእርግጥም ይህ ማሳሰቢያ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በመሆኑ ዛሬ ሁላችንም ልናነበው ችለናል። የጴጥሮስ ሁለተኛ ደብዳቤ 3ኛው ምዕራፍ ትኩረት የሚያደርገው “በመጨረሻው ዘመን” እንዲሁም ምሳሌያዊ በሆኑት ሰማያትና ምድር ላይ በሚመጣው ጥፋት ላይ በመሆኑ በቁም ነገር ልንመለከተው ይገባል። (2 ጴጥ. 3:3, 7, 10) ጴጥሮስ ምን ምክር ሰጥቶናል? የሰጠንን ምክር ተግባራዊ ማድረጋችን የይሖዋን ሞገስ ለማግኘት የሚረዳን እንዴት ነው?
3, 4. (ሀ) ጴጥሮስ ምን ምክር ሰጥቷል? ከምን ነገር እንድንጠበቅስ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል? (ለ) የትኞቹን ሦስት ነጥቦች እንመረምራለን?
3 ጴጥሮስ የሰይጣን ዓለም ስለሚደርስበት ጥፋት ከጠቀሰ በኋላ እንዲህ ብሏል፦ “ቅዱስ ሥነ ምግባር በመከተልና ለአምላክ ያደራችሁ መሆናችሁን የሚያሳዩ ተግባሮች 2 ጴጥ. 3:11, 12) ጴጥሮስ ከመጪው “የበቀል ቀን” መዳን የሚችሉት የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉና አምላካዊ ባሕርያትን የሚያንጸባርቁ ሰዎች ብቻ እንደሆኑ ያውቅ ነበር። (ኢሳ. 61:2) በመሆኑም ሐዋርያው አክሎ እንዲህ ብሏል፦ “ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ ይህን አስቀድማችሁ ስላወቃችሁ ሕግ የሚተላለፉ ሰዎች በሚፈጽሙት ስህተት ከእነሱ [ከሐሰተኛ አስተማሪዎች] ጋር ተታልላችሁ እንዳትወሰዱና ከጽኑ አቋማችሁ እንዳትወድቁ ተጠንቀቁ።”—2 ጴጥ. 3:17
በመፈጸም ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለባችሁ ልታስቡበት ይገባል!” (4 ክርስቲያኖች ‘አስቀድመው ካወቁት’ ሰዎች መካከል እንደመሆናቸው መጠን በመጨረሻው ዘመን ታማኝነታቸውን ለመጠበቅ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ጴጥሮስ ያውቅ ነበር። ይህን ማድረግ የሚያስፈልጋቸው ለምን እንደሆነ ከጊዜ በኋላ ሐዋርያው ዮሐንስ በግልጽ አብራርቷል። ሰይጣን ከሰማይ እንደሚባረር እንዲሁም “የአምላክን ትእዛዛት የሚጠብቁትንና ስለ ኢየሱስ የመመሥከር ሥራ የተሰጣቸውን” ለማጥቃት “በታላቅ ቁጣ” እንደሚሞላ ዮሐንስ በራእይ አስቀድሞ ተመልክቷል። (ራእይ 12:9, 12, 17) ታማኝ የሆኑት የአምላክ ቅቡዓን አገልጋዮች ታማኝ ባልንጀሮቻቸው ከሆኑት “ሌሎች በጎች” ጋር በመሆን ድል ይነሳሉ። (ዮሐ. 10:16) እኛስ በግለሰብ ደረጃ እንዴት ነን? ታማኝነታችንን እንጠብቃለን? ይህን ለማድረግ የሚያስችለንን እርዳታ ማግኘት ከፈለግን (1) አምላካዊ ባሕርያትን ለማዳበር፣ (2) በሥነ ምግባርና በመንፈሳዊ ቆሻሻም ሆነ እድፍ እንዳይገኝብን ለማድረግ እንዲሁም (3) ለፈተና ተገቢ አመለካከት ለመያዝ ጥረት ማድረግ ያስፈልገናል። እስቲ እነዚህን ነጥቦች እንመርምር።
አምላካዊ ባሕርያትን አዳብሩ
5, 6. የትኞቹን ባሕርያት ለማዳበር ጥረት ማድረግ ይኖርብናል? ይህስ “ልባዊ ጥረት” የሚጠይቀው ለምንድን ነው?
5 ጴጥሮስ በሁለተኛ ደብዳቤው መግቢያ ላይ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “ልባዊ ጥረት በማድረግ በእምነታችሁ ላይ በጎነትን ጨምሩ፤ በበጎነት ላይ እውቀትን፣ በእውቀት ላይ ራስን መግዛትን፣ ራስን በመግዛት ላይ ጽናትን፣ በጽናት ላይ ለአምላክ ማደርን፣ ለአምላክ በማደር ላይ ወንድማዊ መዋደድን፣ በወንድማዊ መዋደድ ላይ ፍቅርን ጨምሩ። እነዚህ ነገሮች በውስጣችሁ ቢኖሩና ቢትረፈረፉ፣ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን ትክክለኛ እውቀት ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ሥራ ፈቶችና ፍሬ ቢሶች እንዳትሆኑ ይጠብቋችኋል።”—2 ጴጥ. 1:5-8
6 አምላካዊ ባሕርያትን እንድናዳብር በሚረዱን እንቅስቃሴዎች ለመካፈል “ልባዊ ጥረት” ማድረግ እንደሚያስፈልገን እሙን ነው። ለምሳሌ ያህል፣ በሁሉም ክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ መገኘት፣ መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ማንበብ እንዲሁም ጥሩ የግል ጥናት ፕሮግራም እንዲኖረን ማድረግ ጥረት ይጠይቃል። በተመሳሳይም ቋሚ፣ አስደሳችና ትርጉም ያለው የቤተሰብ አምልኮ ምሽት እንዲኖረን ብርቱ ጥረት ማድረግና ጥሩ እቅድ ማውጣት ያስፈልገናል። ይሁንና እንዲህ ያሉትን ጥሩ ልማዶች የሕይወታችን ክፍል ስናደርጋቸው፣ በተለይ ደግሞ የሚያስገኙትን ጥቅም ስናጣጥመው እነዚህን እንቅስቃሴዎች ማከናወን ይበልጥ ቀላል ይሆንልናል።
7, 8. (ሀ) ስለ ቤተሰብ አምልኮ ምሽት አንዳንዶች ምን አስተያየት ሰጥተዋል? (ለ) አንተስ ከቤተሰብ አምልኮ ምን ጥቅም እያገኘህ ነው?
7 የቤተሰብ አምልኮ ዝግጅትን በተመለከተ አንዲት እህት “ስለ ብዙ ነገሮች እንድናውቅ አስችሎናል” በማለት ጽፋለች። ሌላ እህት ደግሞ እንዲህ ብላለች፦ “እውነቱን ለመናገር የመጽሐፍ ጥናት መቅረቱ ደስ አላለኝም ነበር። በጣም የምወደው ስብሰባ ነበር። በቤተሰብ አምልኮ ዝግጅት መጠቀም ከጀመርን ወዲህ ግን ይሖዋ ምን ነገር በምን ጊዜ እንደሚያስፈልገን የሚያውቅ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ።” አንድ የቤተሰብ ራስም እንዲህ ብሏል፦ “የቤተሰብ አምልኮ በብዙ መንገዶች ጠቅሞናል። እኔና ባለቤቴ፣ የሚያስፈልገንን ነገር ግምት ውስጥ በማስገባት ልንጠቀምበት የምንችል ስብሰባ ማግኘታችን በጣም ደስ ብሎናል! ሁለታችንም የመንፈስ ቅዱስን ፍሬ በማፍራት ረገድ ለውጥ እያደረግን እንዳለን ይሰማናል፤ እንዲሁም ከምንጊዜውም የበለጠ በአገልግሎታችን ደስታ እያገኘን ነው።” ሌላ የቤተሰብ ራስ ደግሞ እንዲህ ብሏል፦ “ልጆቻችን የራሳቸውን ምርምር ስለሚያደርጉ ብዙ እውቀት እያገኙ ነው፤ በዚያ ላይ በጣም ወደውታል። ይህ ዝግጅት ይሖዋ ጭንቀታችንን የሚረዳና ለጸሎታችን መልስ የሚሰጥ አምላክ መሆኑን ይበልጥ እንድንተማመን አድርጎናል።” አንተስ ይህን ድንቅ ዝግጅት በተመለከተ እንደነዚህ ክርስቲያኖች ይሰማሃል?
8 እምብዛም አስፈላጊ ያልሆኑ ነገሮች የቤተሰብ አምልኮ
ፕሮግራማችሁን እንዲያስተጓጉሉባችሁ አትፍቀዱ። አንድ ባልና ሚስት እንዲህ ብለዋል፦ “ላለፉት አራት ሳምንታት ሁልጊዜ ሐሙስ ሐሙስ ጥናታችንን እንድንሰርዝ ሊያደርገን የሚችል የሆነ ነገር በቤተሰባችን ውስጥ ያጋጥመን ነበር፤ በዚህ ወቅት ጥናታችንን ለመሰረዝ ትንሽ ቀርቶን የነበረ ቢሆንም እንዲህ አላደረግንም።” እርግጥ ነው፣ ፕሮግራማችሁን መለወጥ የሚያስፈልጋችሁ ጊዜ ይኖር ይሆናል። ሆኖም ለአንድ ሳምንትም እንኳ ቢሆን የቤተሰብ አምልኮ ፕሮግራማችሁን ላለመሰረዝ ቁርጥ ውሳኔ አድርጉ!9. ይሖዋ ለኤርምያስ የሚያስፈልገውን ነገር የሰጠው እንዴት ነው? ከእሱ ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን?
9 ነቢዩ ኤርምያስ ግሩም ምሳሌ ይሆነናል። ይሖዋ ለኤርምያስ የሚያስፈልገውን መንፈሳዊ ምግብ የሰጠው ሲሆን እሱም አመስጋኝ ነበር። ይህ ምግብ መልእክቱን ለመስማት ፈቃደኛ ላልሆኑ ሰዎች በጽናት እንዲሰብክ አስችሎታል። ኤርምያስ “የእግዚአብሔር ቃል፣ . . . እንደ እሳት፣ በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ ሆነብኝ” ብሏል። (ኤር. 20:8, 9) ከዚህም በተጨማሪ ከአምላክ ያገኘው ምግብ ኢየሩሳሌም በጠፋችበት ወቅት የነበረውን ከባድ ሁኔታ ለመቋቋም አስችሎታል። በዛሬው ጊዜ በጽሑፍ የሰፈረው ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ አለን። የአምላክን ቃል በትጋት ስናጠናውና የይሖዋ ዓይነት አስተሳሰብ ስናዳብር እኛም እንደ ኤርምያስ በአገልግሎት ደስተኞች ሆነን መጽናት፣ ፈተናዎች ሲያጋጥሙን ታማኝነታችንን መጠበቅ እንዲሁም ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ ንጽሕናችንን መጠበቅ እንችላለን።—ያዕ. 5:10
“ቆሻሻና እድፍ ሳይኖርባችሁ” ለመገኘት ጥረት አድርጉ
10, 11. ‘ቆሻሻና እድፍ ሳይኖርብን’ ለመገኘት የተቻለንን ጥረት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው? ይህስ ምን ማድረግን ይጨምራል?
10 ክርስቲያኖች እንደ መሆናችን መጠን በመጨረሻው ጊዜ እንደምንኖር እናውቃለን። በመሆኑም ዓለም እንደ ስግብግብነት፣ የፆታ ብልግና እንዲሁም ዓመፅ ላሉት ይሖዋ የሚጸየፋቸው ድርጊቶች ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱ አያስገርመንም። ሰይጣን የሚጠቀምበት ዘዴ በሚከተለው መንገድ ጠቅለል ተደርጎ ሊገለጽ ይችላል፦ ‘የአምላክ አገልጋዮችን ማስፈራራት ካልተቻለ መበከል ይቻል ይሆናል።’ (ራእይ 2:13, 14) በመሆኑም ጴጥሮስ በፍቅር ተነሳስቶ የሰጠውን የሚከተለውን ማሳሰቢያ ልብ ማለት አለብን፦ “በመጨረሻ [በአምላክ] ፊት ቆሻሻና እድፍ ሳይኖርባችሁ በሰላም እንድትገኙ የተቻላችሁን ጥረት አድርጉ።”—2 ጴጥ. 3:14
11 “የተቻላችሁን ጥረት አድርጉ” የሚለው አገላለጽ ጴጥሮስ “ልባዊ ጥረት [አድርጉ]” በማለት ቀደም ሲል ከሰጠው ማሳሰቢያ ጋር ይመሳሰላል። ጴጥሮስ እነዚህን ማሳሰቢያዎች የጻፈው በአምላክ መንፈስ ተመርቶ በመሆኑ ይሖዋ በሰይጣን ዓለም “ቆሻሻና እድፍ” ሳንበከል ለመገኘት ጥረት ማድረግ እንደሚያስፈልገን የሚያውቅ መሆኑን በግልጽ መመልከት ይቻላል። የተቻለንን ጥረት ማድረግ ሲባል በመጥፎ ምኞቶች እንዳንሸነፍ ልባችንን መጠበቅን ይጨምራል። (ምሳሌ 4:23ን እና ያዕቆብ 1:14, 15ን አንብብ።) ከዚህም በተጨማሪ ክርስቲያናዊ አኗኗራችንን በማየት የሚደነቁና ‘የሚሰድቡን’ ሰዎች የሚያሳድሩብንን ተጽዕኖ በጽናት መቋቋምን ያካትታል።—1 ጴጥ. 4:4
12. ሉቃስ 11:13 ምን ማረጋገጫ ይሰጠናል?
12 ፍጹማን ባለመሆናችን ትክክል የሆነውን ማድረግ ትግል ይጠይቅብናል። (ሮም 7:21-25) ጥረታችን ሊሳካ የሚችለው ከልብ ለሚለምኑት ቅዱስ መንፈሱን አብዝቶ ወደሚሰጠው ወደ ይሖዋ ዞር ካልን ብቻ ነው። (ሉቃስ 11:13) ይህ መንፈስ ደግሞ የአምላክን ሕግ እንድንጥስ የሚያጋጥሙንን ተፈታታኝ ሁኔታዎች ብቻ ሳይሆን የይሖዋ ቀን እየቀረበ ሲመጣ እየጨመሩ የሚሄዱትን ፈተናዎች እንድንቋቋም ብሎም የአምላክን ሞገስ እንድናገኝ የሚረዱንን ባሕርያት እንድናዳብር ያስችለናል።
ፈተና ሊያጠናክራችሁ ይገባል
13. በሕይወታችን ውስጥ ፈተና ሲያጋጥመን እንድንጸና ምን ሊረዳን ይችላል?
13 በዚህ አሮጌ ሥርዓት ውስጥ እስከኖርን ድረስ የተለያዩ ፈተናዎች እንደሚያጋጥሙን የታወቀ ነው። ሆኖም ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ፈተናዎችን ለአምላክ ያለህን ፍቅር ለማረጋገጥ የሚረዱ እንዲሁም በእሱና በቃሉ ላይ ያለህን እምነት ለማጠናከር የሚያስችሉ አጋጣሚዎች እንደሆኑ አድርገህ ለምን አታያቸውም? ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ “ወንድሞቼ ሆይ፣ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቁጠሩት፤ ይህን ስታደርጉ ተፈትኖ የተረጋገጠው እምነታችሁ ጽናት እንደሚያስገኝ ታውቃላችሁ” በማለት ጽፏል። (ያዕ. 1:2-4) “ይሖዋ፣ ለአምላክ ያደሩ ሰዎችን ከፈተና እንዴት እንደሚያድን” የሚያውቅ መሆኑንም መዘንጋት የለብህም።—2 ጴጥ. 2:9
14. ዮሴፍ የተወው ምሳሌ አንተን የሚያበረታታህ እንዴት ነው?
14 የገዛ ወንድሞቹ በባርነት የሸጡትን የያዕቆብ ልጅ የሆነውን ዮሴፍን እንደ ምሳሌ እንመልከት። (ዘፍ. 37:23-28፤ 42:21) ዮሴፍ እንዲህ ያለ የጭካኔ ድርጊት ስለተፈጸመበት በይሖዋ ላይ ያለውን እምነት አጥቷል? ዮሴፍ መጥፎ ነገር እንዲያጋጥመው አምላክ በመፍቀዱ በእሱ ላይ ተማርሯል? የአምላክ ቃል እንዲህ እንዳላደረገ በግልጽ ይነግረናል። የዮሴፍ ፈተና ግን በዚህ አላበቃም። ከጊዜ በኋላ አስገድዶ የመድፈር ሙከራ አድርጓል በሚል በሐሰት ተከሶ ወህኒ ወርዷል። በዚህ ጊዜም ቢሆን ለአምላክ ያደረ መሆኑን አሳይቷል። (ዘፍ. 39:9-21) የደረሱበት ፈተናዎች እንዲያጠናክሩት የፈቀደ ሲሆን ይህን በማድረጉም ታላቅ በረከት አግኝቷል።
15. ከኑኃሚን ምሳሌ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?
15 ፈተናዎች እንድናዝን አልፎ ተርፎም በጭንቀት እንድንዋጥ ሊያደርጉን እንደሚችሉ አይካድም። ዮሴፍ እንደዚህ የተሰማው ወቅት እንደሚኖር መገመት ይቻላል። ሌሎች ታማኝ የአምላክ አገልጋዮችም ተመሳሳይ ስሜት አድሮባቸው ነበር። ባሏንና ሁለት ልጆቿን በሞት ያጣችውን የኑኃሚንን ሁኔታ እንመልከት። “ሁሉን የሚችል አምላክ ሕይወቴን እጅግ መራራ አድርጎታልና ማራ [“መራራ” ማለት ነው] በሉኝ እንጂ፣ ኑኃሚን ብላችሁ አትጥሩኝ” በማለት ተናግራለች። (ሩት 1:20, 21፣ የግርጌ ማስታወሻ) ኑኃሚን እንዲህ የተሰማት መሆኑ የሚያስገርም አይደለም። ያም ቢሆን እሷም እንደ ዮሴፍ የደረሰባት ፈተና እምነቷን እንዲያሳጣትም ሆነ ታማኝነቷን እንድታጎድል እንዲያደርጋት አልፈቀደችም። ይሖዋም ይህችን ተወዳጅ ሴት ባርኳታል። (ሩት 4:13-17, 22) ከዚህም በተጨማሪ ሰይጣንና ክፉ የሆነው የእሱ ዓለም ያደረሱትን ጉዳት ሁሉ ይሖዋ በቅርቡ ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ያስተካክለዋል። “ያለፉት ነገሮች አይታሰቡም፤ አይታወሱም።”—ኢሳ. 65:17
16. ለጸሎት ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖረን ይገባል? ለምንስ?
16 ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን የአምላክ ፍቅር ፈተናውን እንድንወጣው ይረዳናል። (ሮም 8:35-39ን አንብብ።) ሰይጣን እኛን ተስፋ ለማስቆረጥ ጥረት ማድረጉን ባያቋርጥም “ጤናማ አስተሳሰብ” ካለን እንዲሁም “በጸሎት ረገድ ንቁዎች” ከሆንን አይሳካለትም። (1 ጴጥ. 4:7) ኢየሱስ “መፈጸማቸው ከማይቀረው ከእነዚህ ሁሉ ነገሮች ማምለጥና በሰው ልጅ ፊት መቆም እንድትችሉ ሁልጊዜ ምልጃ እያቀረባችሁ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ” ብሏል። (ሉቃስ 21:36) ኢየሱስ ከልብ የመነጨ ጸሎትን የሚያመለክተውን “ምልጃ” የሚለውን ቃል እንደተጠቀመ ልብ በል። ኢየሱስ ምልጃ እንድናቀርብ ምክር በመስጠት ካለንበት ጊዜ አንጻር በእሱም ሆነ በአባቱ ፊት መቆምን አክብደን መመልከታችን አስፈላጊ እንደሆነ ጎላ አድርጎ ገልጿል። ከይሖዋ ቀን መትረፍ የሚችሉት በአምላክ ፊት ሞገስ ያገኙ ብቻ ናቸው።
በይሖዋ አገልግሎት ምንጊዜም ንቁ ተሳትፎ ይኑራችሁ
17. የአገልግሎት ክልልህ አስቸጋሪ ከሆነ በጥንት ዘመን የኖሩ ነቢያት ከተዉት ግሩም ምሳሌ ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለህ?
17 በመንፈሳዊ እንቅስቃሴዎች መካፈል መንፈሳችንን ያድስልናል። ይህም ጴጥሮስ እንደሚከተለው በማለት የተናገረውን ሐሳብ ያስታውሰናል፦ “ቅዱስ ሥነ ምግባር በመከተልና ለአምላክ ያደራችሁ መሆናችሁን የሚያሳዩ ተግባሮች በመፈጸም ምን ዓይነት ሰዎች መሆን እንዳለባችሁ ልታስቡበት ይገባል!” (2 ጴጥ. 3:11) ከእነዚህ ተግባሮች መካከል ዋነኛው ምሥራቹን መስበክ ነው። (ማቴ. 24:14) እውነት ነው፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ሰዎች ግዴለሾች ወይም ተቃዋሚዎች በመሆናቸው አሊያም ከዕለታዊ ሕይወታቸው ጋር በተያያዙ ጉዳዮች የተጠመዱ በመሆናቸው የስብከቱን ሥራ ማከናወን ተፈታታኝ ሊሆን ይችላል። በጥንት ዘመን የኖሩ የይሖዋ አገልጋዮችም እንዲህ ያለውን የሰዎች ዝንባሌ መቋቋም አስፈልጓቸው ነበር። ያም ቢሆን ግን ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ አምላክ የሰጣቸውን መልእክት ለማድረስ ወደ ሰዎቹ ‘መላልሰው’ ይሄዱ ነበር። (2 ዜና መዋዕል 36:15, 16ን በታረመው የ1980 ትርጉም አንብብ፤ * ኤር. 7:24-26) እንዲጸኑ የረዳቸው ምንድን ነው? ለተሰጣቸው ተልእኮ ዓለም ምንም ዓይነት አመለካከት ይኑረው እነሱ ሥራውን በተመለከተ የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ነበራቸው። ከዚህም በተጨማሪ የአምላክን ስም መሸከምን እንደ ታላቅ ክብር ይቆጥሩት ነበር።—ኤር. 15:16
18. የመንግሥቱ ስብከት ሥራ የአምላክ ስም ከፍ እንዲል በማድረግ ረገድ ወደፊት ምን ሚና ይኖረዋል?
18 እኛም የይሖዋን ስምና ዓላማ የማወጅ መብት አለን። እስቲ አስበው፦ እኛ የስብከቱን ሥራ በማከናወናችን፣ የአምላክ ጠላቶች በታላቁ የፍርድ ቀን ይሖዋ የጥፋት እርምጃ በሚወስድባቸው ወቅት መልእክቱን እንዳልሰሙ ሰበብ ማቅረብ አይችሉም። በእርግጥም በጥንት ዘመን እንደኖረው ፈርዖን ሁሉ እነዚህ የአምላክ ጠላቶችም እርምጃ የሚወስድባቸው ይሖዋ መሆኑን ይገነዘባሉ። (ዘፀ. 8:1, 20፤ 14:25) በሌላ በኩል ደግሞ ይሖዋ፣ ታማኝ አገልጋዮቹ በእርግጥም የእሱ ወኪሎች መሆናቸውን በማያሻማ መንገድ በማሳየት ያከብራቸዋል።—ሕዝቅኤል 2:5ን እና 33:33ን አንብብ።
19. የይሖዋን ትዕግሥት በአግባቡ እንደምንጠቀምበት እንዴት ማሳየት እንችላለን?
19 ጴጥሮስ በሁለተኛ ደብዳቤው መደምደሚያ አካባቢ ለእምነት ባልንጀሮቹ “የጌታችንን ትዕግሥት እንደ መዳን ቁጠሩት” በማለት ጽፏል። (2 ጴጥ. 3:15) አዎን፣ የይሖዋን ትዕግሥት በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል። ይህን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? እሱን የሚያስደስቱ ባሕርያትን በማዳበር፣ ‘ቆሻሻና እድፍ ሳይኖርብን’ ለመገኘት ጥረት በማድረግ፣ ለፈተናዎች ተገቢ አመለካከት በመያዝ እንዲሁም በመንግሥቱ የስብከት ሥራ ራሳችንን በማስጠመድ ነው። እንዲህ ካደረግን “አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር” በሚኖርበት ጊዜ ከሚመጡት ማለቂያ የሌላቸው በረከቶች መካፈል እንችላለን።—2 ጴጥ. 3:13
[የግርጌ ማስታወሻ]
^ አን.17 ሁለተኛ ዜና መዋዕል 36:15, 16 (የታረመው የ1980 ትርጉም)፦ “የቀድሞ አባቶቻቸው አምላክ እግዚአብሔር ለሕዝቡና ለቤተ መቅደሱ ስላዘነ ያስጠነቅቁአቸው ዘንድ ነቢያትን መላልሶ መላክን ቀጠለ። እስራኤላውያን ግን በእግዚአብሔር መልእክተኞች ላይ ተሳለቁ፤ በነቢያቱም በማፌዝ፣ የእግዚአብሔርን ቃል አቃለሉ፤ ከዚህም የተነሳ፣ የእግዚአብሔር ቊጣ በሕዝቡ ላይ ወረደ፤ ከታላቅ ቊጣውም ለማምለጥ አልቻሉም።”
ታስታውሳለህ?
• አምላካዊ ባሕርያትን ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው?
• ‘ቆሻሻና እድፍ ሳይኖርብን’ መገኘት የምንችለው እንዴት ነው?
• ከዮሴፍና ከኑኃሚን ምን መማር እንችላለን?
• በስብከቱ ሥራ መካፈል ታላቅ መብት ነው የምንለው ለምንድን ነው?
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ባሎች፣ እናንተም ሆናችሁ ቤተሰባችሁ አምላካዊ ባሕርያትን እንድታዳብሩ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
[በገጽ 10 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ዮሴፍ ፈተናዎች ሲያጋጥሙት ካደረገው ነገር ምን ትምህርት እናገኛለን?