በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በማንበብ ተጠቅመሃል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

የሰው ዕድል አስቀድሞ ተወስኗል ብለው የሚያምኑ ሃይማኖቶች ይህንን መሠረተ ትምህርት ያመጡት ከየት ነው?

ካልቪን የሰው ዕድል አስቀድሞ ተወስኗል ለሚለው መሠረተ ትምህርት ከፍተኛ ቦታ ይሰጥ ነበር። የተሃድሶ አራማጅ የነበረው የዣን ኮቨን (ጆን ካልቪን) ትምህርቶች እንደ ፕሬስባይቲሪያን፣ ኮንግርጌሽናል፣ የተሃድሶ ቤተ ክርስቲያንና ፒዩሪታን ባሉት በፕሮቴስታንት ሥር በሚታቀፉ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ተጽዕኖ አሳድረዋል።—9/1 ከገጽ 18-21

ቃየን ሚስቱን ያገኘው ከየት ነበር?

የቃየን ሚስት ከሔዋን ዝርያዎች መካከል አንዷ መሆን አለባት፤ ሔዋን “ወንዶችና ሴቶች ልጆችን” ወልዳ ነበር። (ዘፍ. 5:4)—9/1 ገጽ 25

አምላክ እስራኤላውያንን ከግብፅ ሲያወጣቸው በፊታቸው እንዲሄድ የላከው የትኛውን መልአክ ነበር? (ዘፀ. 23:20, 21)

ይሖዋ “ስሜ በርሱ ላይ ነው” ብሎ የተናገረለት ይህ መልአክ ከጊዜ በኋላ ኢየሱስ የተባለው የአምላክ የበኩር ልጅ ነው ብሎ ማመኑ ምክንያታዊ ነው።—9/15 ገጽ 21

በአንደኛ ቆሮንቶስ ላይ ለጣዖት ስለተሠዋ ሥጋ የተነሳው ለምን ነበር?

በግሪካውያንና በሮማውያን ቤተ መቅደስ ውስጥ እንስሳት መሥዋዕት ሆነው ይቀርቡ ነበር፤ ሆኖም በሥነ ሥርዓቱ ላይ ያልተበላው ሥጋ በሥጋ ገበያ ይሸጥ ነበር። ክርስቲያኖች በአረማውያን አምልኮ አይካፈሉም፤ ይሁንና ከቤተ መቅደስ ወጥቶ በሥጋ ገበያ ላይ የሚሸጠውን ሥጋ እንደረከሰ አድርገው አይመለከቱትም። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “ከሕሊናችሁ የተነሳ ምንም ጥያቄ ሳታነሱ በሥጋ ገበያ የሚሸጠውን ሁሉ ብሉ፤ ምክንያቱም ‘ምድርና ምድርን የሞላት ነገር ሁሉ የይሖዋ ነው።’” (1 ቆሮ. 10:25, 26)—10/1 ገጽ 12

ከእውነተኛው አምልኮ ጋር በተያያዘ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት የሌላቸው ሰበቦች የትኞቹ ናቸው?

‘በጣም ከባድ ነው። የመስበክ ፍላጎት የለኝም። በጣም ሥራ ይበዛብኛል። ጥሩ ችሎታ የለኝም። አንድ ሰው ጎድቶኛል።’ እነዚህ ነገሮች የአምላክን ትእዛዝ ላለመፈጸም የሚቀርቡ ተቀባይነት የሌላቸው ሰበቦች ናቸው።—10/15 ከገጽ 12-15

ስብሰባዎቻችን አንተንም ሆነ ሌሎችን የሚያንጹ እንዲሆኑ ማድረግ የምትችልባቸው አንዳንድ መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

አስቀድመህ መዘጋጀት። አዘውትረህ በስብሰባዎች ላይ መገኘት። በጊዜ መድረስ። የሚያስፈልጉህን ጽሑፎች ይዘህ መሄድ። ትኩረት የሚሰርቁ ነገሮችን ማስወገድ። ተሳትፎ ማድረግ። አጠር ያለ መልስ መስጠት። የተሰጠህን ክፍል በሚገባ ማቅረብ። ማመስገን። ከስብሰባዎች በፊትና በኋላ ከወንድሞች ጋር ጊዜ ማሳለፍ።—10/15 ገጽ 22

በዛሬው ጊዜ ሃንሰንስ ዲዚዝ ተብሎ የሚጠራውን በሽታ የሚያጠቃልለው የለምጽ በሽታ ከአንዲት እስራኤላዊት ልጃገረድ ጋር በተያያዘ የተጠቀሰው በየትኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ውስጥ ነው?

ሁለተኛ ነገሥት ምዕራፍ አምስት፣ ንዕማን በተባለ የሶርያ ጦር አዛዥ ቤት ስለምታገለግል አንዲት እስራኤላዊት ልጃገረድ ይናገራል። ንዕማን በለምጽ በሽታ ይሠቃይ ስለነበር ወደ ነቢዩ ኤልሳዕ ሄዶ እንዲፈወስ ሐሳብ አቀረበች።—11/1 ገጽ 22

አሮን ለእኩዮች ተጽዕኖ ስለመሸነፉ ከሚገልጸው ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን?

ሙሴ አብሮት ባልነበረበት ወቅት እስራኤላውያን ጣዖት እንዲሠራላቸው አሮንን ወተወቱት። አሮንም ለእነሱ ተጽዕኖ ተሸንፎ ያሉትን አደረገላቸው። ከዚህ ሁኔታ መመልከት እንደሚቻለው የእኩዮች ተጽዕኖ የሚያጋጥማቸው ወጣቶች ብቻ አይደሉም። ትክክል የሆነውን ለማድረግ የሚፈልጉ ትልልቅ ሰዎችም ጭምር የእኩዮች ተጽዕኖ ሊያጋጥማቸው ይችላል። እኩዮች የሚያሳድሩብንን መጥፎ ተጽዕኖ መቋቋም ይኖርብናል።—11/15 ገጽ 8

እውነት ወይም ሐሰት በል።

ሰይጣን ሕልውና ያለው አካል ነው፦ እውነት። (2 ቆሮ. 11:14) ሁሉም ሰዎች ሲሞቱ ወደ መንፈሳዊው ዓለም ይሄዳሉ፦ ሐሰት። (መክ. 9:5) ታማኝ የሆኑ መላእክት ስለ እኛ ያስባሉ፦ እውነት። (መዝ. 34:7) ኢየሱስ ከአምላክ ጋር እኩል ነው፦ ሐሰት። (1 ቆሮ. 11:3)—12/1 ገጽ 8, 9