በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በዓመታዊው የአገልግሎት ሪፖርት ላይ ከሚወጡት አኃዞች ምን ግንዛቤ እናገኛለን?

በዓመታዊው የአገልግሎት ሪፖርት ላይ ከሚወጡት አኃዞች ምን ግንዛቤ እናገኛለን?

የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዓመታዊው የአገልግሎት ሪፖርት ላይ ከሚወጡት አኃዞች ምን ግንዛቤ እናገኛለን?

በየዓመቱ በዓመት መጽሐፍ እንዲሁም በመንግሥት አገልግሎታችን ላይ በየካቲት ወር የሚወጣውን የአገልግሎት ሪፖርት ለማየት እንጓጓለን። የይሖዋ ሕዝቦች በኅብረት ሆነው በዓለም አቀፉ የስብከትና የማስተማር ሥር ላይ ምን እንዳከናወኑ መመልከቱ አስደሳች ነው። ከዚህ ሪፖርት የተሟላ ጥቅም ለማግኘት እንድንችል አኃዞቹን በተመለከተ ትክክለኛ ግንዛቤና ሚዛናዊ አመለካከት ሊኖረን ይገባል። እስቲ በሪፖርቱ ላይ ከሚወጡት ነገሮች መካከል አንዳንድ ምሳሌዎችን እንመልከት።

የአገልግሎት ዓመት። ይህ በአንድ ዓመት ውስጥ ከመስከረም እስከ ነሐሴ ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። በዓመት መጽሐፍ ላይ የሚወጣው ሪፖርት ያለፈውን ዓመት የአገልግሎት እንቅስቃሴ የሚያሳይ ነው። በመሆኑም በ2011 የዓመት መጽሐፍ ወይም በየካቲት 2011 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ የወጣው የ2010 የአገልግሎት ዓመት ሪፖርት ሲሆን ይህም ከመስከረም 1, 2009 እስከ ነሐሴ 31, 2010 ያለውን ጊዜ ይሸፍናል።

የአስፋፊ ከፍተኛ ቁጥር እና አማካይ አስፋፊ። “አስፋፊዎች” የሚባሉት የተጠመቁ የይሖዋ ምሥክሮችና የመንግሥቱን ምሥራች ለመስበክ ብቃቱን ያሟሉ ያልተጠመቁ ሰባኪዎች ናቸው። “የአስፋፊ ከፍተኛ ቁጥር” የሚባለው በአንድ የአገልግሎት ዓመት ውስጥ በየትኛውም ወር ላይ የተመዘገበው ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር ነው፤ ይህም ከዚያ በፊት በነበረው ወር ሪፖርት ውስጥ ያልተካተቱ ዘግይተው የደረሱ ሪፖርቶችን ሊያጠቃልል ይችላል። እንዲህ ሲባል አንዳንድ አስፋፊዎች ሁለት ጊዜ ሊቆጠሩ ይችላሉ ማለት ነው። ይሁንና በአገልግሎት ቢካፈሉም ሰዓታቸውን ሪፖርት ያላደረጉ አስፋፊዎች በአስፋፊዎች ከፍተኛ ቁጥር ውስጥ አይካተቱም። ይህም እያንዳንዱ አስፋፊ በየወሩ ሳይዘገይ ሪፖርቱን የመመለሱን አስፈላጊነት ያጎላል። “አማካይ አስፋፊ” የሚባለው ደግሞ በዓመቱ ውስጥ የአገልግሎት እንቅስቃሴያቸውን ሪፖርት ያደረጉ አስፋፊዎች ጠቅላላ ቁጥር በ12 ሲካፈል የሚገኘው አኃዝ ነው።

ጠቅላላ ሰዓት። የ2011 የዓመት መጽሐፍ እንደሚያሳየው የይሖዋ ምሥክሮች በመስክ አገልግሎት ከ1.6 ቢሊዮን በላይ ሰዓታት አሳልፈዋል። ይሁን እንጂ ይህ ሰዓት እረኝነት በማድረግ፣ በስብሰባዎች ላይ በመገኘት፣ በግል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትና በማሰላሰል እንዲሁም በመሳሰሉት እንቅስቃሴዎች ላይ የምናሳልፈውን ጊዜ ስለማይጨምር በአምልኮ የምናሳልፈውን አጠቃላይ ሰዓት የሚያመለክት አይደለም።

የወጣው ገንዘብ። በ2010 የአገልግሎት ዓመት ልዩ አቅኚዎች፣ ሚስዮናውያን እንዲሁም ተጓዥ የበላይ ተመልካቾች በተመደቡበት የመስክ አገልግሎት ክልል ሲያገለግሉ የሚያስፈልጋቸውን ወጪ ለመሸፈን የይሖዋ ምሥክሮች ከ155 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ አውጥተዋል። ይሁንና ይህ አኃዝ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎቻችንን ለማተም የወጣውን ወጪ አይጨምርም፤ በዓለም ዙሪያ በሚገኙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ በፈቃደኝነት ለሚያገለግሉት ከ20,000 በላይ ቤቴላውያን የሚወጣውን ወጪም አያካትትም።

የመታሰቢያው በዓል ተካፋዮች። ይህ አኃዝ በመታሰቢያው በዓል ላይ ከሚቀርበው ምሳሌያዊ ቂጣና ወይን የሚካፈሉ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የተጠመቁ ግለሰቦችን የሚያመለክት ነው። ይህ አኃዝ በምድር ላይ ያሉትን ቅቡዓን አጠቃላይ ቁጥር የሚያሳይ ነው? ላይሆን ይችላል። አንዳንዶች በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ለምሳሌ፣ ቀደም ሲል በነበራቸው ሃይማኖታዊ እምነት አሊያም በአእምሮ ወይም በስሜት መቃወስ የተነሳ ሰማያዊ ጥሪ እንዳላቸው አድርገው በተሳሳተ መንገድ ሊያስቡ ይችላሉ። በመሆኑም በምድር ላይ ያሉትን ቅቡዓንን ትክክለኛ ቁጥር ማወቅ የምንችልበት መንገድ የለም፤ ደግሞም ቁጥራቸውን ማወቅ አያስፈልገንም። የበላይ አካሉ በመታሰቢያው በዓል ላይ ከሚቀርበው ቂጣና ወይን የሚካፈሉ ሰዎችን ስም ዝርዝር አይዝም። *

የምናውቀው ነገር ቢኖር፣ በታላቁ መከራ ወቅት ጥፋት የሚያስከትሉት ነፋሳት ሲለቀቁ ቅቡዓን ከሆኑት ‘የአምላካችን ባሪያዎች’ መካከል የተወሰኑት በምድር ላይ እንደሚኖሩ ነው። (ራእይ 7:1-3) እስከዚያ ጊዜ ድረስ ቅቡዓኑ በዓመታዊው የአገልግሎት ሪፖርታችን ላይ በሚወጣው ሥራ ይኸውም በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ከተከናወኑት ሁሉ ይበልጥ ታላቅ በሆነው የስብከትና የማስተማር እንቅስቃሴ ግንባር ቀደም ሆነው ይካፈላሉ።

[የግርጌ ማስታወሻ]