በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘የልግስና ስጦታ ለመስጠት የሚያስችል መብት’ በማግኘትህ ደስተኛ ነህ?

‘የልግስና ስጦታ ለመስጠት የሚያስችል መብት’ በማግኘትህ ደስተኛ ነህ?

‘የልግስና ስጦታ ለመስጠት የሚያስችል መብት’ በማግኘትህ ደስተኛ ነህ?

በፊልጵስዩስ የሚኖሩ የጥንቶቹ ክርስቲያኖች እውነተኛውን አምልኮ ለመደገፍ በሚያደርጉት የልግስና ስጦታ ይታወቁ ነበር። ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት በጻፈላቸው ደብዳቤ ላይ እንዲህ ብሎ ነበር፦ “እናንተን ባስታወስኩ ቁጥር ምንጊዜም አምላኬን አመሰግናለሁ፤ ይህንም የማደርገው ስለ ሁላችሁ ምልጃ ባቀረብኩ ጊዜ ሁሉ ነው፤ ደግሞም ምልጃ የማቀርበው በደስታ ነው፤ ምክንያቱም ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ እስከዚህ ጊዜ ድረስ ለምሥራቹ አስተዋጽኦ ስታደርጉ ቆይታችኋል።” (ፊልጵ. 1:3-5) ሊዲያና በቤቷ የሚኖሩ ሰዎች ሲጠመቁ የነበረውን ሁኔታ ጳውሎስ በደንብ ያስታውሳል፤ በዚያ ወቅት ሊዲያ፣ እሱንም ሆነ የአገልግሎት ጓደኞቹን ቤቷ ገብተው በእንግድነት እንዲያርፉ ግድ ብላቸው ነበር።​—ሥራ 16:14, 15

ይህ ከሆነ ብዙም ሳይቆይ ማለትም ሐዋርያው ጳውሎስ 160 ኪሎ ሜትር ያህል ርቃ በምትገኘው በተሰሎንቄ ካሉ የእምነት ባልንጀሮቹ ዘንድ ለበርካታ ሳምንታት በተቀመጠበት ጊዜ አዲስ በተቋቋመው በፊልጵስዩስ ጉባኤ ያሉ ክርስቲያኖች ከአንዴም ሁለቴ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ልከውለት ነበር። (ፊልጵ. 4:15, 16) ከጥቂት ዓመታት በኋላ ደግሞ በፊልጵስዩስና በመቄዶንያ የነበሩ ወንድሞች በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ክርስቲያኖች ችግር ላይ መውደቃቸውን ሲሰሙ እነሱን ለመርዳት ፈልገው ነበር፤ የሚገርመው እንዲህ ለማድረግ የተነሳሱት እነሱ ራሳቸው መከራ እየደረሰባቸውና “ከባድ ድህነት ውስጥ እያሉ” ነበር። ጳውሎስ እነዚህ ክርስቲያኖች ያደረጉት “ከአቅማቸው በላይ” እንደሆነ መሥክሯል። እንዲያውም ጳውሎስ “የልግስና ስጦታ ለመስጠት . . . የሚያስችል መብት እንዲሰጣቸው በራሳቸው ፍላጎት ተነሳስተው ይለምኑን እንዲያውም ይማጸኑን ነበር” በማለት ጽፏል።​—2 ቆሮ. 8:1-4፤ ሮም 15:26

የፊልጵስዩስ ወንድሞች ክርስትናን ከተቀበሉ ከአሥር ዓመት ገደማ በኋላ እንኳ የልግስና መንፈስ ማሳየታቸውን ቀጥለው ነበር። ጳውሎስ በሮም እስር ላይ መሆኑን በሰሙ ጊዜ አፍሮዲጡ በየብስና በባሕር 1,287 ኪሎ ሜትር ተጉዞ የሚያስፈልጉትን ነገሮች እንዲያደርስለት ልከውት ነበር። ከዚህ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው የፊልጵስዩስ ክርስቲያኖች ጳውሎስ በእስር ላይ ሆኖም ጭምር ወንድሞችን ማበረታታቱንና የስብከቱን ሥራ ማካሄዱን እንዲቀጥል የሚያስችለውን እርዳታ ሊያደርጉለት ፈልገው ነበር።​—ፊልጵ. 1:12-14፤ 2:25-30፤ 4:18

በዛሬው ጊዜ የሚገኙ እውነተኛ ክርስቲያኖችም የስብከቱንና ደቀ መዛሙርት የማድረጉን ሥራ መደገፍ መቻላቸውን እንደ ትልቅ መብት ይቆጥሩታል። (ማቴ. 28:19, 20) ከአምላክ መንግሥት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ለማስፋፋት ጊዜያቸውን፣ ጉልበታቸውንና ገንዘባቸውን ይሰጣሉ። ከታች የሚገኘው ሣጥን አምላክ የሰጠንን ይህን ሥራ መደገፍ የምትችልባቸውን አንዳንድ መንገዶች ይጠቁምሃል።

[በገጽ 22 እና 23 ላይ የሚገኝ ሣጥን]

አንዳንዶች መዋጮ የሚያደርጉባቸው መንገዶች

ለዓለም አቀፉ ሥራ የሚደረጉ መዋጮዎች

ብዙዎች “ለዓለም አቀፉ ሥራ” ተብሎ የተለጠፈባቸው ሣጥኖች ውስጥ የሚጨምሩት የተወሰነ ገንዘብ ያስቀምጣሉ ወይም ይመድባሉ።

ጉባኤዎች የተዋጣውን ገንዘብ በአገራቸው ሥራውን ለሚቆጣጠረው የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮ በየወሩ ይልካሉ። ከዚህ በተጨማሪ በፈቃደኝነት የሚደረጉ የገንዘብ መዋጮዎችን በቀጥታ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ፖ.ሣ.ቁ. 5522፣ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ በሚለው አድራሻ ወይም ባላችሁበት አገር ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ መላክ ይቻላል። (ከታች በተዘረዘሩት መንገዶች በፈቃደኝነት የሚደረጉ ስጦታዎችንም ባላችሁበት አገር ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ መላክ ይቻላል።) ቼኮች ለ“የይሖዋ ምሥክሮች” የሚከፈሉ መሆናቸው መገለጽ አለበት። ከውድ ማዕድናት የተሠሩ ጌጣጌጦችን ወይም ሌሎች ውድ ዕቃዎችንም መስጠት ይቻላል። የተላከው ዕቃ ሙሉ በሙሉ ስጦታ መሆኑን የሚገልጽ አጭር ደብዳቤ ተያይዞ መላክ ይኖርበታል።

ተመላሽ ሊሆን የሚችል ገንዘብ የሚሰጥበት ዝግጅት

አንድ ሰው ገንዘቡን የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት ዓለም አቀፉን ሥራ ለማካሄድ እንዲጠቀምበት በአደራ መልክ ሊሰጥና ሲያስፈልገው ድርጅቱን በመጠየቅ መልሶ ማግኘት ይችላል። ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ከላይ በተገለጸው አድራሻ በመጻፍ ወይም በስልክ ቁጥር 011-6603611 በመደወል የይሖዋ ምሥክሮችን ቅርንጫፍ ቢሮ መጠየቅ ይቻላል።

በእቅድ የሚደረግ ስጦታ

ገንዘብ በስጦታ ከመለገስ በተጨማሪ በመላው ዓለም የሚካሄደውን የመንግሥቱን ሥራ መደገፍ የሚቻልባቸው ሌሎች መንገዶችም አሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያጠቃልላሉ፦

ኢንሹራንስ፦ የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት የሕይወት ኢንሹራንስ ፖሊሲ ወይም የጡረታ ክፍያ ተጠቃሚ እንዲሆን ስም ሊዛወርለት ይችላል።

የባንክ ሒሳብ፦ የአገሩ ባንክ ደንብ በሚፈቅደው መሠረት የባንክ ሒሳቦች፣ ገንዘብ መቀመጡን የሚገልጽ የምሥክር ወረቀት ወይም የግል ጡረታ ሒሳቦች በአደራ ወይም በሞት ጊዜ የሚከፈል መሆኑ ተገልጾ ለይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት ሊሰጥ ይችላል።

አክሲዮኖችና ቦንዶች፦ አክሲዮኖችንና ቦንዶችን በስጦታ መልክ ለይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት መስጠት ይቻላል፤ ወይም ደግሞ በሞት ጊዜ ለይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት እንዲሰጥ ስም ሊዛወርለት ይችላል።

የማይንቀሳቀስ ንብረት፦ ሊሸጥ ሊለወጥ የሚችል ቋሚ ንብረት በስጦታ መስጠት ወይም መኖሪያ ቤት በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ ባለ ንብረቱ በሕይወት እስካለ ድረስ ተጠቅሞበት ከዚያ በኋላ ማውረስ ይቻላል። አንድ ሰው ማንኛውንም የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት ከማዛወሩ በፊት በአገሩ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ቢሮ ጋር መነጋገር ይኖርበታል።

የስጦታ አበል፦ የስጦታ አበል አንድ ሰው ገንዘቡን ወይም የባለቤትነት መብትን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን የይሖዋ ምሥክሮችን ወክሎ ለሚሠራው ድርጅት ለማዛወር የሚያደርገውን ዝግጅት ያመለክታል። በምላሹም ለጋሹ ወይም እሱ የወከለው ግለሰብ በሕይወት እስካለበት ጊዜ ድረስ የተወሰነ መጠን ያለው ገንዘብ በየዓመቱ በአበል መልክ ይከፈለዋል።

ኑዛዜዎችና አደራዎች፦ ንብረት ወይም ገንዘብ በሕግ ፊት ተቀባይነት ባለው ኑዛዜ አማካኝነት ለይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት በውርስ ሊሰጥ ወይም የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ድርጅት በአደራ የተሰጠው ንብረት ተጠቃሚ ተደርጎ ስሙ ሊዛወር ይችላል።

“በእቅድ የሚደረግ ስጦታ” የሚለው አገላለጽ፣ እነዚህን የመሳሰሉ መዋጮዎች የሚያደርገው ግለሰብ እቅድ ማውጣት እንደሚያስፈልገው ይጠቁማል። የይሖዋ ምሥክሮችን ዓለም አቀፍ ሥራ በእቅድ በሚደረግ ስጦታ ለመደገፍ ለሚፈልጉ ግለሰቦች ጉዳዩን ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ዓለም አቀፉን የመንግሥቱን ስብከት ሥራ ለመደገፍ በእቅድ የሚደረግ ስጦታ የሚል ብሮሹር በእንግሊዝኛና በስፓንኛ ቋንቋ ተዘጋጅቷል። ይህ ብሮሹር የተዘጋጀው ሰዎች ስጦታ ለመስጠት ወይም በሚሞቱበት ጊዜ በኑዛዜ ውርስ ለመተው የሚችሉባቸውን የተለያዩ መንገዶች አስመልክቶ መረጃ ለመስጠት ነው። ብዙዎች ይህን ብሮሹር ካነበቡ በኋላ ከሕግ ወይም ከቀረጥ አማካሪዎቻቸው ጋር በመማከር በዓለም ዙሪያ የምናከናውነውን ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴና ሰብዓዊ እርዳታ ለመደገፍ ከመቻላቸውም በላይ ከቀረጥ ጋር በተያያዘ የተሻለ ጥቅም ለማግኘት ችለዋል። ይህን ብሮሹር ለማግኘት በእቅድ የሚደረግ ስጦታን ጉዳይ የሚከታተለውን ቢሮ በቀጥታ መጠየቅ ይቻላል።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከታች ያለውን አድራሻ ወይም ስልክ ቁጥር ተጠቅመህ ቅርንጫፍ ቢሮውን መጠየቅ ትችላለህ። አሊያም ባለህበት አገር ለሥራው አመራር የሚሰጠውን ቅርንጫፍ ቢሮ ማነጋገር ትችላለህ።

የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ማኅበር

ፖ.ሣ.ቁ. 5522

አዲስ አበባ

ኢትዮጵያ

ስልክ፦ 011-6603611