ለይሖዋ የሙሉ ነፍስ መሥዋዕት ማቅረብ
“የምታደርጉትን ሁሉ . . . ለይሖዋ እንደምታደርጉት በማሰብ በሙሉ ነፍሳችሁ አድርጉት።”—ቆላ. 3:23
1-3. (ሀ) ኢየሱስ በመከራ እንጨት ላይ ተሰቅሎ መሞቱ ይሖዋ ምንም ዓይነት መሥዋዕት ማቅረብ እንደማይጠብቅብን ያሳያል? አብራራ። (ለ) በዛሬው ጊዜ የሚቀርቡ መሥዋዕቶችን አስመልክቶ የትኛው ጥያቄ ይነሳል?
ይሖዋ፣ በኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት የሙሴን ሕግ እንደሻረው በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. ለሕዝቡ ገልጾላቸው ነበር። (ቆላ. 2:13, 14) አይሁዳውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሲያደርጉ እንደነበረው መሥዋዕቶችን ማቅረብ ከዚያን ጊዜ አንስቶ አስፈላጊ አልነበረም፤ ከዚያ በኋላ የሚቀርቡ መሥዋዕቶች ምንም ዋጋ የላቸውም። ሕጉ ‘ወደ ክርስቶስ የሚያደርስ ሞግዚት’ በመሆን የሚጫወተውን ሚና ከፍጻሜው አድርሷል።—ገላ. 3:24
2 ይህ ማለት ግን ክርስቲያኖች ጨርሶ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልጋቸውም ማለት አይደለም። እንዲያውም ሐዋርያው ጴጥሮስ “በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መንፈሳዊ መሥዋዕት ማቅረብ” አስፈላጊ እንደሆነ ተናግሯል። (1 ጴጥ. 2:5) ከዚህም በተጨማሪ ራሳቸውን የወሰኑ ክርስቲያኖች ሕይወታቸው ማለትም በሕይወታቸው ውስጥ የሚያደርጉት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ እንደ “መሥዋዕት” ሊቆጠር እንደሚችል ሐዋርያው ጳውሎስ በግልጽ ተናግሯል።—ሮም 12:1
3 በመሆኑም አንድ ክርስቲያን ለይሖዋ አንዳንድ ነገሮችን በመስጠት ወይም አምላክን ለማገልገል ሲል አንዳንድ ነገሮችን በመተው መሥዋዕት ያቀርብ ይሆናል። ከመሥዋዕት ጋር በተያያዘ አምላክ ከእስራኤላውያን ምን ይጠብቅ እንደነበር እናውቃለን፤ ታዲያ ከዚህ በመነሳት እኛ የምናቀርባቸው መሥዋዕቶች በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ይኖራቸው እንደሆነና እንዳልሆነ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
በዕለት ተዕለት ሕይወታችን
4. በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የምናደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች አስመልክቶ ምን ነገር ማስታወስ ይኖርብናል?
4 በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ለይሖዋ ከምናቀርበው መሥዋዕት ጋር ምን ግንኙነት እንዳላቸው በቀላሉ አይታየን ይሆናል። ገበያ ስንወጣ ወይም በቤት ውስጥ፣ በትምህርት ቆላስይስ 3:18-24ን አንብብ።
ቤት፣ በሥራ ቦታ አሊያም በሌሎች ቦታዎች የምናደርጋቸው ነገሮች ከላይ ከላይ ሲታዩ ከመንፈሳዊ ጉዳዮች ጋር የሚያያይዛቸው ምንም ነገር እንደሌለ ሊሰማን ይችላል። ይሁንና ራስህን ለይሖዋ የወሰንክ ክርስቲያን ወይም በቅርቡ ይህን ለማድረግ የምታስብ ሰው ከሆንክ በዕለት ተዕለት ሕይወትህ የምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ከአምላክ ጋር ያለህን ግንኙነት እንደሚነኩ ማስታወስ ይኖርብሃል። ምክንያቱም እኛ የ24 ሰዓት ክርስቲያኖች ነን። በቅዱሳን መጻሕፍት ላይ የሚገኙትን መሠረታዊ ሥርዓቶች በየትኛውም የሕይወታችን ዘርፍ ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል። ጳውሎስ ይህን በተመለከተ እንዲህ የሚል ማሳሰቢያ ሰጥቷል፦ “የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለይሖዋ እንደምታደርጉት በማሰብ በሙሉ ነፍሳችሁ አድርጉት።”—5, 6. በዕለት ተዕለት ሕይወታችን በምናሳየው ምግባርና በአለባበሳችን ረገድ ግምት ውስጥ ልናስገባ የሚገባን ነገር ምንድን ነው?
5 እርግጥ ነው፣ አንድ ክርስቲያን የሚያደርጋቸው የዕለት ተለት እንቅስቃሴዎች ለይሖዋ የሚያቀርበው ቅዱስ አገልግሎት ክፍል አይደሉም። ሆኖም ጳውሎስ ማንኛውንም ነገር ‘ለይሖዋ እንደምናደርገው በማሰብ በሙሉ ነፍሳችን’ እንድናከናውን የሰጠን ማሳሰቢያ መላ ሕይወታችንን ቆም ብለን እንድንፈትሽ ያደርገናል። ታዲያ ይህን ተግባራዊ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ምንጊዜም አለባበሳችንና ምግባራችን ከአንድ ክርስቲያን የሚጠበቅ ነው? ወይስ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያችንን በምናከናውንበት ወቅት በምናሳየው ምግባር ወይም በአለባበሳችን ምክንያት የይሖዋ ምሥክር መሆናችንን መግለጽ ያሳፍረናል? በፍጹም እንዲህ መሆን የለበትም! የይሖዋ ሕዝቦች በአምላክ ስም ላይ ነቀፋ የሚያመጣ ምንም ነገር ማድረግ አይፈልጉም።—ኢሳ. 43:10፤ 2 ቆሮ. 6:3, 4, 9
6 ማንኛውንም ነገር ‘ለይሖዋ እንደምናደርግ በማሰብ በሙሉ ነፍሳችን’ ለማከናወን ያለን ፍላጎት በተለያዩ የሕይወታችን ዘርፎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት እንደሆነ እስቲ እንመልከት። ይህን በምንመረምርበት ጊዜ እስራኤላውያን ምንም ዓይነት መሥዋዕት ሲያቀርቡ ምርጣቸውን መስጠት እንደነበረባቸው በአእምሯችን መያዛችን አስፈላጊ ነው።—ዘፀ. 23:19
ሕይወታችንን የሚነካው እንዴት ነው?
7. ራስን መወሰን ምን ነገሮችን ይጨምራል?
7 ራስህን ለይሖዋ ስትወስን፣ ምንም ሳትቆጥብ መላ ሕይወትህን ለእሱ አገልግሎት እንደምታውል ቃል መግባትህ ነበር። በሌላ አባባል በየትኛውም የሕይወትህ ዘርፍ የይሖዋን ፍላጎት ለማስቀደም ወስነሃል ማለት ነው። (ዕብራውያን 10:7ን አንብብ።) ይህ ደግሞ ትክክለኛ ምርጫ ነው። አንድን ጉዳይ አስመልክቶ የይሖዋ ፈቃድ ምን እንደሆነ ለማወቅና ከዚህ ጋር የሚስማማ እርምጃ ለመውሰድ ጥረት ማድረግ አስደሳች ውጤት እንደሚያስገኝ ሳትመለከት አልቀረህም። (ኢሳ. 48:17, 18) የአምላክ ሕዝቦች ከይሖዋ የተማሩ እንደመሆናቸው መጠን የእሱን ባሕርይ ያንጸባርቃሉ፤ በመሆኑም ቅዱስ እንዲሁም ደስተኛ ናቸው።—ዘሌ. 11:44፤ 1 ጢሞ. 1:11
8. ይሖዋ በጥንት ጊዜ የሚቀርቡ መሥዋዕቶችን ቅዱስ እንደሆኑ አድርጎ የሚመለከታቸው መሆኑ ለእኛ ምን ትርጉም አለው?
8 እስራኤላውያን ለይሖዋ የሚያቀርቧቸው መሥዋዕቶች እንደ ቅዱስ ተደርገው ይታዩ ነበር። (ዘሌ. 6: 25፤ 7:1) “ቅድስና” ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል መለየት፣ ለአምላክ ብቻ መወሰን ወይም ለእሱ የተቀደሱ መሆን የሚል ሐሳብ ያስተላልፋል። የምናቀርበው መሥዋዕት በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከተፈለገ ከዚህ ዓለም የተለየ መሆን ይገባዋል፤ እንዲሁም ከዓለም ጋር ምንም ዓይነት ንኪኪ የሌለው መሆን ይኖርበታል። ይሖዋ የሚጠላውን ማንኛውንም ነገር መውደድ አይኖርብንም። (1 ዮሐንስ 2:15-17ን አንብብ።) በሌላ አባባል በአምላክ ዓይን እንድንረክስ ሊያደርጉን ከሚችሉ ሰዎች ወይም ድርጊቶች መራቅ ይኖርብናል። (ኢሳ. 2:4፤ ራእይ 18:4) ከዚህም በተጨማሪ ንጹሕ ያልሆኑ ወይም ሥነ ምግባር የጎደላቸውን ነገሮች አንመለከትም እንዲሁም እንዲህ ስላሉ ነገሮች አናውጠነጥንም።—ቆላ. 3:5, 6
9. ክርስቲያኖች ሌሎችን የሚይዙበት መንገድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ለምንድን ነው?
9 ጳውሎስ የእምነት ባልንጀሮቹን እንዲህ ሲል አሳስቧቸው ነበር፦ “መልካም ማድረግንና ያላችሁን ነገር ለሌሎች ማካፈልን አትርሱ፤ ምክንያቱም አምላክ እንዲህ ባሉት መሥዋዕቶች እጅግ ይደሰታል።” (ዕብ. 13:16) በመሆኑም ለሌሎች ጥሩ ሰው መሆንና መልካም ማድረግ የሕይወታችን ክፍል ከሆነ ይሖዋ ይህን አድራጎታችንን ተቀባይነት እንዳለው መሥዋዕት አድርጎ ይመለከተዋል። ለሌሎች ፍቅራዊ አሳቢነት ማሳየት የእውነተኛ ክርስቲያኖች መለያ ነው።—ዮሐ. 13:34, 35፤ ቆላ. 1:10
ከአምልኳችን ጋር የተያያዙ መሥዋዕቶች
10, 11. ይሖዋ ክርስቲያናዊ አገልግሎታችንን እና አምልኮታችንን የሚመለከተው እንዴት ነው? ይህስ ምን እንድናደርግ ሊያነሳሳን ይገባል?
10 ክርስቲያኖች ለሰዎች መልካም ከሚያደርጉባቸው መንገዶች መካከል ዋነኛው ‘ተስፋቸውን በይፋ ማወጅ’ ነው። አንተስ በምታገኘው በእያንዳንዱ አጋጣሚ ተጠቅመህ ምሥክርነት ትሰጣለህ? ጳውሎስ ስለዚህ ወሳኝ ሥራ ሲገልጽ እንዲህ ብሏል፦ “የምስጋና መሥዋዕት ዘወትር ለአምላክ እናቅርብ፤ ይህም ስለ ስሙ በይፋ የምናውጅበት የከንፈር ፍሬ ነው።” (ዕብ. 10:23፤ 13:15፤ ሆሴዕ 14:2) የመንግሥቱን ምሥራች የምንሰብክበትን መንገድ ለማሻሻል ማድረግ የምንችለውን ነገርና ለዚህ ሥራ የምናውለውን ጊዜ በተመለከተ ቆም ብለን ማሰባችን አስፈላጊ ነው፤ በአገልግሎት ስብሰባዎች ላይ የሚቀርቡት አብዛኞቹ ክፍሎች ይህን ለማድረግ ይረዱናል። ያም ሆነ ይህ አንድ ነገር ማስታወስ ይኖርብናል፦ የመስክ አገልግሎታችንም ሆነ መደበኛ ባልሆነ መንገድ የምንሰጠው ምሥክርነት “የምስጋና መሥዋዕት” ሲሆን ይህ ደግሞ የአምልኳችን ክፍል ነው፤ በመሆኑም ይህን መሥዋዕት ስናቀርብ ምርጣችንን መስጠት ይኖርብናል። እርግጥ ያለንበት ሁኔታ ከሰው ወደ ሰው ይለያያል፤ ይሁንና በአብዛኛው ምሥራቹን ለማወጅ የምንመድበው የጊዜ መጠን ለመንፈሳዊ ነገሮች ያለን አድናቆት ምን ያህል እንደሆነ ያሳያል።
11 ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን በግልም ሆነ በቡድን የምናካሂደው ቋሚ የሆነ የአምልኮ 1 ተሰ. 5:17፤ ዕብ. 10:24, 25) መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎቻችንን አስመልክቶ ‘ለይሖዋ የማቀርበውን አምልኮ ጥራት ማሻሻል ይኖርብኝ ይሆን?’ በማለት ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል።
ፕሮግራም አለን። ይሖዋም ቢሆን ይህን እንድናደርግ ይጠብቅብናል። እውነት ነው፣ የሰንበትን ሕግ ማክበር ወይም በዓል ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም መጓዝ አይጠበቅብንም። ይሁን እንጂ በጥንት ጊዜ ይከበሩ የነበሩ በዓላት ለክርስቲያኖች የሚሆን ጠቃሚ ትምህርት ይዘዋል። ዛሬም ቢሆን አምላክ፣ የሞቱ ሥራዎችን መሥራታችንን አቁመን ቃሉን ለማጥናት፣ ለመጸለይና በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ጊዜ እንድንመድብ ይፈልጋል። በተጨማሪም ክርስቲያን የሆኑ የቤተሰብ ራሶች ከተቀረው የቤተሰቡ አባላት ጋር በመሆን የቤተሰብ አምልኮ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው። (12. (ሀ) በጥንት ጊዜ ለአምልኮ ይቀርብ የነበረው ዕጣን በዛሬው ጊዜ ከምን ጋር ሊመሳሰል ይችላል? (ለ) ይህን ማወቃችን በጸሎታችን ይዘት ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?
12 ንጉሥ ዳዊት “ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን ትቈጠርልኝ” በማለት ዘምሯል። (መዝ. 141:2) እስቲ ስለ ጸሎትህ ልማድ ቆም ብለህ ለማሰብ ሞክር፤ አዘውትረህ ትጸልያለህ? የጸሎትህ ይዘትስ ምን ይመስላል? የራእይ መጽሐፍ ‘የቅዱሳንን ጸሎት’ ከዕጣን ጋር ያመሳስለዋል፤ በሌላ አባባል በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ጸሎቶች ልክ እንደ ጥሩ ሽታና አስደሳች መዓዛ ወደ እሱ ይደርሳሉ። (ራእይ 5:8) በጥንቷ እስራኤል፣ በይሖዋ መሠዊያ ላይ ዘወትር ይቀርብ የነበረው ዕጣን ትክክለኛውን መንገድ ተከትሎ በጥንቃቄ መዘጋጀት ነበረበት። ዕጣኑ በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት የሚኖረው እሱ በሰጠው መመሪያ መሠረት ከቀረበ ብቻ ነው። (ዘፀ. 30:34-37፤ ዘሌ. 10:1, 2) በተመሳሳይም ጸሎታችንን የምናቀርበው እሱ በሚፈልገው መንገድ ከሆነ በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት እንደሚኖረው እርግጠኞች መሆን እንችላለን።
መስጠትና መቀበል
13, 14. (ሀ) አፍሮዲጡና የፊልጵስዩስ ጉባኤ አባላት ለጳውሎስ ምን አድርገውለት ነበር? ጳውሎስስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ተሰማው? (ለ) አፍሮዲጡና የፊልጵስዩስ ጉባኤ አባላት የተዉትን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?
13 የምናደርገው መዋጮ ጥቂትም ሆነ ብዙ፣ ዓለም አቀፉን ሥራ ለመደገፍ የምንሰጠው ገንዘብ ከመሥዋዕት ጋር ሊመሳሰል ይችላል። (ማር. 12:41-44) በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. የነበሩት የፊልጵስዩስ ጉባኤ አባላት ለጳውሎስ የሚያስፈልገውን ቁሳዊ እርዳታ እንዲያደርስ አፍሮዲጡን ወደ ሮም ልከውት ነበር። ይህ መልእክተኛ ይዞ ከሄደው ነገር መካከል ጉባኤው የላከው የገንዘብ ስጦታ እንደሚገኝበት ምንም ጥርጥር የለውም። የፊልጵስዩስ ጉባኤ ለጳውሎስ ደግነት ሲያሳይ ይህ የመጀመሪያ ጊዜው አልነበረም። እነዚህ ክርስቲያኖች እንዲህ ያለ ደግነት ያሳዩት ጳውሎስ የሚያስፈልጉትን ቁሳዊ ነገሮች ለማሟላት ሳይጨነቅ ይበልጥ በአገልግሎት ላይ እንዲያተኩር ስለፈለጉ ነው። ታዲያ ጳውሎስ ይህን ስጦታ እንዴት ተመለከተው? ጳውሎስ ስጦታውን “ጥሩ መዓዛ ያለው ሽታ፣ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕትና አምላክ ደስ የሚሰኝበት” በማለት ገልጾታል። (ፊልጵስዩስ 4:15-19ን አንብብ።) ጳውሎስ የፊልጵስዩስ ክርስቲያኖች ላሳዩት ደግነት ልባዊ አድናቆት ነበረው፤ ይሖዋም ቢሆን የተሰማው እንደዚህ ነበር።
14 ዛሬም ቢሆን ዓለም አቀፉን ሥራ ለመደገፍ የምናደርገውን መዋጮ ይሖዋ ከፍ አድርጎ ይመለከተዋል። ከዚህም በተጨማሪ በሕይወታችን ውስጥ ከመንግሥቱ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ካስቀደምን በመንፈሳዊም ሆነ በሥጋዊ የሚያስፈልጉንን ነገሮች እንደሚያሟላልን ቃል ገብቷል።—ማቴ. 6:33፤ ሉቃስ 6:38
አድናቆት እንዳላችሁ አሳዩ
15. ይሖዋን እንድታመሰግነው የሚገፋፉህ አንዳንድ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
15 ይሖዋን እንድናመሰግነው የሚያነሳሱንን ምክንያቶች እንዘርዝር ብንል ጊዜ አይበቃንም። ይሖዋ ሕይወት ስለሰጠን በየዕለቱ ልናመሰግነው ይገባል ቢባል አትስማማም? የምንተነፍሰውን አየር ጨምሮ በሕይወት ለመኖር የሚያስፈልጉንን ነገሮች ይኸውም ምግብ፣ ልብስና መጠለያ ይሰጠናል። በተጨማሪም በትክክለኛ እውቀት ላይ የተመሠረተው እምነታችን ተስፋ እንዲኖረን አድርጓል። በመሆኑም ከማንነቱና ለእኛ ካደረገልን ነገር በመነሳት ብቻ እንኳ ይሖዋን ማምለክና ለእሱ የምሥጋና መሥዋዕት ማቅረብ ይገባናል።—ራእይ 4:11ን አንብብ።
16. ለክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት አድናቆት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
16 ቀደም ባለው የጥናት ርዕስ ላይ እንደተመለከትነው 1 ዮሐ. 4:10) ታዲያ ለዚህ ስጦታ አድናቆት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? ጳውሎስ እንዲህ በማለት ተናግሯል፦ “አንድ ሰው ለሁሉም መሞቱን ስለተረዳን ክርስቶስ ያለው ፍቅር ግድ ይለናል፤ . . . በሕይወት ያሉት ከእንግዲህ ለራሳቸው ከመኖር ይልቅ ለእነሱ ለሞተውና ለተነሳው እንዲኖሩ እሱ ለሁሉም ሞቷል።” (2 ቆሮ. 5:14, 15) ጳውሎስ ይህን ሲል የአምላክን ጸጋ የምናደንቅ ከሆነ ሕይወታችንን እሱንና ልጁን በሚያስከብር መንገድ እንደምንመራ መናገሩ ነበር። ለአምላክ ብሎም ለክርስቶስ ያለን ፍቅርና አድናቆት በምናሳየው የታዛዥነት መንፈስ እንዲሁም በስብከቱና ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ለመካፈል ባለን ልባዊ ፍላጎት ይገለጻል።—1 ጢሞ. 2:3, 4፤ 1 ዮሐ. 5:3
አምላክ ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ስጦታዎች ሁሉ የላቀው የክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት ነው። ቤዛው አምላክ ለእኛ ፍቅር እንዳለው የሚያሳይ ጉልህ ማስረጃ ነው። (17, 18. አንዳንዶች ለይሖዋ የሚያቀርቡትን የምስጋና መሥዋዕት ከፍ ማድረግ የቻሉት እንዴት ነው? ምሳሌ ስጥ።
17 ለአምላክ ከምታቀርበው የምስጋና መሥዋዕት ጋር በተያያዘ ማሻሻያ ማድረግ ይኖርብህ ይሆን? ብዙዎች ይሖዋ ባደረገላቸው መልካም ነገር ላይ ማሰላሰላቸው ጊዜያቸውንና ፕሮግራማቸውን በማመቻቸት በስብከቱ ሥራና በሌሎች ቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች የበለጠ ጊዜ ለማሳለፍ አነሳስቷቸዋል። አንዳንዶች በየዓመቱ ለአንድ ወይም ከዚያ ለሚበልጡ ወራት ረዳት አቅኚ ሆነው ሲያገለግሉ ሌሎች ደግሞ የዘወትር አቅኚ ሆነዋል። አንዳንድ አስፋፊዎች ደግሞ በግንባታ ሥራዎች ላይ መካፈል ችለዋል። እንዲህ ያሉ እንቅስቃሴዎች አንድ ሰው አድናቆቱን የሚገልጽባቸው ግሩም መንገዶች ናቸው ቢባል አትስማማም? አንድ ሰው እነዚህን ነገሮች የሚያደርገው በትክክለኛ ዝንባሌ ማለትም ለአምላክ ካለው አድናቆት የተነሳ ከሆነ አምላክ ይህን ቅዱስ አገልግሎት ይቀበለዋል።
18 ለይሖዋ አድናቆታቸውን የመግለጽ ዕዳ እንዳለባቸው ስለተሰማቸው ይህን ለማድረግ የተነሳሱ በርካታ ክርስቲያኖች አሉ። ከእነዚህ መካከል አንዷ ሞሪና ናት። ሞሪና ባደገችበት የካቶሊክ እምነት ውስጥም ሆነ የሩቅ ምሥራቅ ፍልስፍናዎችን በማጥናት ለመንፈሳዊ ጥያቄዎቿ መልስ ማግኘት ሞክራ ነበር። ሆኖም ከሁለቱም አቅጣጫ መልስ ለማግኘት ያደረገችው ጥረት አልተሳካላትም። ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ስትጀምር ግን መንፈሳዊ ጥማቷን ማርካት ቻለች። ሞሪና ለጥያቄዎቿ በሙሉ ቅዱስ ጽሑፋዊ መልስ ስላገኘችና ይህ ደግሞ ሕይወቷን በተረጋጋ መንገድ እንድትመራ ስላስቻላት ለይሖዋ አድናቆቷን መግለጽ እንዳለባት ተሰማት፤ በመሆኑም ባላት ጉልበት ሁሉ ይሖዋን በማገልገል ምስጋናዋን መግለጽ ፈለገች። ልክ እንደተጠመቀች በቋሚነት ረዳት አቅኚ ሆና ማገልገል የጀመረች ሲሆን ሁኔታዋ ሲመቻችላት ደግሞ ወዲያው የዘወትር አቅኚ ሆነች። ይህ ከሆነ 30 ዓመታት ያለፉ ሲሆን ሞሪና አሁንም ድረስ በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ትገኛለች።
19. አንተ በግልህ ለይሖዋ የምታቀርበውን መሥዋዕት ከፍ ማድረግ የምትችልባቸው አጋጣሚዎች የትኞቹ ናቸው?
19 እርግጥ ነው፣ አቅኚ ሆነው ለማገልገል ሁኔታቸው የማይፈቅድላቸው ብዙ ታማኝ ክርስቲያኖች አሉ። በይሖዋ አገልግሎት ልናበረክተው የምንችለው አስተዋጽኦ ምንም ይሁን ምን ሁላችንም በእሱ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መንፈሳዊ መሥዋዕት ማቅረብ እንችላለን። ምንጊዜም ይሖዋን የምንወክል መሆናችንን በማስታወስ በምግባራችን የጽድቅ መሠረታዊ ሥርዓቶችን እንደምናከብር ማሳየት እንችላለን። እምነት የምናዳብር ከሆነ አምላክ ዓላማዎቹን ከፍጻሜው እንደሚያደርስ ሙሉ በሙሉ እንተማመናለን። መልካም ሥራዎችን በመሥራት የምንተጋ ከሆነ ደግሞ ምሥራቹን በማስፋፋት ረገድ አስተዋጽኦ እናደርጋለን። እንግዲያው ይሖዋ ላደረገልን ነገር ባለን ልባዊ አድናቆት ተነሳስተን ለእሱ የሙሉ ነፍስ መሥዋዕት ማቅረባችንን እንቀጥል።
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]
የይሖዋ ጥሩነት ከምስጋና መሥዋዕት ጋር በተያያዘ ማሻሻያ እንድታደርግ ይገፋፋሃል?
[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
በምታገኘው በእያንዳንዱ አጋጣሚ ተጠቅመህ ምሥክርነት ትሰጣለህ?