በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በደንብ አንብበሃቸዋል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

ሰለሞን የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ሊሆነን ይችላል የምንለው ለምንድን ነው?

አምላክ ሰለሞንን ይጠቀምበት የነበረ ከመሆኑም ሌላ በብዙ መንገድ ባርኮታል። ይሁንና በግዛት ዘመኑ የአምላክን ምክር ችላ ብሎ ነበር። አረማዊ የነበረችውን የፈርዖንን ልጅ ጨምሮ ሌሎች ብዙ ሚስቶችን ያገባ ሲሆን ከጊዜ በኋላ እነዚህ ሴቶች የሐሰት አምልኮን እንዲከተል አድርገውታል። እኛም የተሳሳተ ዝንባሌና አመለካከት ቀስ በቀስ እንዳናዳብር መጠንቀቅ አለብን። (ዘዳ. 7:1-4፤ 17:17፤ 1 ነገ. 11:4-8)​—12/15 ከገጽ 10-12

ሣራ አምላክን የምትፈራ ሴት እና ተወዳጅ ሚስት ነበረች የምንለው ለምንድን ነው?

አምላክ ዑርን ለቆ እንዲወጣ ለአብርሃም የሰጠው ትእዛዝ ቤተሰቡን፣ ወዳጆቹን እና በአጠቃላይ የለመደውን ኑሮ ትቶ ወደማያውቀው አካባቢ እንዲሄድ የሚጠይቅ ነበር። ሆኖም ሣራ አምላክ እንደሚባርካት ስለተማመነች ከባሏ ጋር ለመተባበር ፈቃደኛ ነበረች። እንዲሁም መልካም ባሕርያትን በማፍራት አብርሃምን እንደምታከብረው አሳይታለች።​—1/1 ገጽ 8

አብርሃም የሚወደውን ልጁን መሥዋዕት እንዲያደርግ ይሖዋ የጠየቀው ለምንድን ነው?

በመጀመሪያ ደረጃ፣ አብርሃም ይስሐቅን መሥዋዕት ለማድረግ ቢዘጋጅም ይሖዋ ግን እንዳልፈቀደ ማስታወሳችን አስፈላጊ ነው። ይህ ሁኔታ አምላክ ልጁ ኢየሱስን መሥዋዕት ሆኖ እንዲሞት በመፍቀድ ለሚከፍለው ከፍተኛ ዋጋ ተምሳሌት ነው።​—1/1 ገጽ 23

ከአንደኛው መቶ ዘመን ጀምሮ በዘመናት ሁሉ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ያልነበሩበት ወቅት እንደሌለ የሚጠቁመን ምንድን ነው?

ኢየሱስ ስለ “ስንዴው” እና “እንክርዳዱ” በተናገረው ምሳሌ ላይ “ጥሩው ዘር” የሚያመለክተው ‘የመንግሥቱን ልጆች’ ነው። (ማቴ. 13:24-30, 38) እንክርዳዱ እስከ መከር ጊዜ ድረስ ከስንዴው ጋር አብሮ ያድጋል። በመሆኑም የትኞቹ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች በስንዴ ከተመሰለው የቅቡዓን ክፍል እንደሚመደቡ በእርግጠኝነት መናገር ባንችልም በዘመናት ሁሉ የተወሰኑ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ነበሩ ብለን መናገር እንችላለን።​—1/15 ገጽ 7

ወደ አርማጌዶን የሚያመሩ ክንውኖች የትኞቹ ናቸው?

ብሔራት “ሰላምና ደኅንነት ሆነ!” የሚል ትልቅ ትርጉም ያዘለ አዋጅ ያወጣሉ። (1 ተሰ. 5:3) ከዚያም የዓለም መንግሥታት የሐሰት ሃይማኖትን ለማጥፋት ይነሳሉ። (ራእይ 17:15-18) በመቀጠል እነዚህ መንግሥታት በእውነተኛ የይሖዋ አምላኪዎች ላይ ጥቃት ይሰነዝራሉ። ከዚህ በኋላ ይህ ሥርዓት ወደ ፍፃሜው ይመጣል።​—2/1 ገጽ 9

የቅናት ዝንባሌ እንዳይቆጣጠረን ምን ማድረግ እንችላለን?

በዚህ ረገድ የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ሊረዳን ይችላል፦ ፍቅርንና የወንድማማች መዋደድን ማዳበር፣ ፈሪሃ አምላክ ካላቸው ሰዎች ጋር መወዳጀት፣ መልካም ለማድረግ መጣርና “ደስ ከተሰኙ ሰዎች ጋር ደስ” መሰኘት። (ሮም 12:15)​—2/15 ከገጽ 16-17

የናዋትል ቋንቋ ተናጋሪዎች እነማን ናቸው? እነሱን ለመርዳትስ ምን ጥረት እየተደረገ ነው?

ናዋትል የጥንቶቹ አዝቴኮች ይናገሩት የነበረ ቋንቋ ሲሆን በዛሬው ጊዜም በሜክሲኮ የሚኖሩ 1.5 ሚሊዮን የሚያህሉ ሰዎች በዚህ ቋንቋ ይጠቀማሉ። የይሖዋ ምሥክሮች በናዋትል ቋንቋ እየሰበኩ ሲሆን አንዳንድ ጽሑፎቻችንም በዚህ ቋንቋ ተተርጉመዋል።​—3/1 ከገጽ 13-14

ምክር በምንሰጥበት ወቅት የትኞቹን መሠረታዊ ሥርዓቶች በአእምሯችን መያዝ አለብን?

ስለ ጉዳዩ ትክክለኛ ግንዛቤ መያዝ። ያልታሰበበት መልስ አለመስጠት። እንዲሁም ትሑት በመሆን የአምላክን ቃል መጠቀም። የሚቻል ከሆነ በቲኦክራሲያዊ ቤተ መጻሕፍት መጠቀም። ከዚህም በተጨማሪ ለሌሎች ውሳኔ ላለማድረግ መጠንቀቅ።​—3/15 ከገጽ 7-9

ኢየሱስ አድማጮቹን ሁለት ኪሎ ሜትር እንዲሄዱ አሳስቧቸዋል። (ማቴ. 5:41) ታዲያ እንዲህ ሲል ምን ማለቱ ነበር?

በወቅቱ እስራኤል ውስጥ ቅኝ ገዥ የሆኑት ሮማውያን የፈለጉትን አገልግሎት እንዲሰጥ አንድን ሰው ሊያስገድዱት ይችሉ ነበር። በመሆኑም ኢየሱስ ለአድማጮቹ ሁለት ኪሎ ሜትር ሂዱ ሲል በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች የሚጠይቋቸው አገልግሎቶች ከአምላክ ሕግ ጋር የሚጋጩ እስካልሆኑ ድረስ ሳያማርሩ እንዲሠሩ እያሳሰባቸው ነበር።​—4/1 ገጽ 9