ይሖዋ ሕዝቡን እንዴት እንደሚያድን ያውቃል
ይሖዋ ሕዝቡን እንዴት እንደሚያድን ያውቃል
“ይሖዋ፣ ለአምላክ ያደሩ ሰዎችን ከፈተና እንዴት እንደሚያድን . . . ያውቃል።”—2 ጴጥ. 2:9
የሚከተሉት ነገሮች በይሖዋ ላይ እምነት ማሳደር እንድንችል የሚረዱን እንዴት ነው?
ከዓላማው አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ነገሮች የሚከናወኑበትን ጊዜ የሚያውቅ መሆኑ፣
ሕዝቦቹን ለማዳን ሲል ኃይሉን የሚጠቀም መሆኑ፣
በትንቢት የተነገሩት ወሳኝ ነገሮች እንዴት እንደሚፈጸሙ የሚያውቅ መሆኑ፣
1. ‘ታላቁ መከራ’ ሲመጣ ምን ነገሮች ይከሰታሉ?
የአምላክ ፍርድ በሰይጣን ዓለም ላይ ሳይታሰብ ድንገት ይመጣል። (1 ተሰ. 5:2, 3) ‘ታላቁ የይሖዋ ቀን’ ሲመጣ ሰብዓዊው ኅብረተሰብ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ ይወድቃል። (ሶፎ. 1:14-17) በዚያን ቀን በመላው ምድር ላይ መከራና እጦት ይከሰታል። እንዲሁም “ከዓለም መጀመሪያ አንስቶ እስካሁን ድረስ ሆኖ” በማያውቅ መንገድ መላው የሰው ዘር በጭንቀት ይዋጣል።—ማቴዎስ 24:21, 22ን አንብብ።
2, 3. (ሀ) የአምላክ ሕዝቦች ‘በታላቁ መከራ’ ወቅት ምን ያጋጥማቸዋል? (ለ) የወደፊቱን ጊዜ በልበ ሙሉነት እንድንጠባበቅ የሚያደርገን ምንድን ነው?
2 ‘ታላቁ መከራ’ ወደፍጻሜው ሲደርስ ‘በማጎግ ምድር የሚገኘው ጎግ’ በአምላክ ሕዝቦች ላይ መጠነ ሰፊ የሆነ ጥቃት ይሰነዝራል። በዚህ ወቅት “እጅግ ታላቅ ኀያል ሰራዊት” “ምድርን እንደሚሸፍን ደመና” በመሆን በአምላክ ሕዝቦች ላይ ይወጣል። (ሕዝ. 38:2, 14-16) በዚያን ጊዜ የይሖዋን ሕዝቦች ከዚህ ጥቃት ለመታደግ የሚቆም ምንም ዓይነት ሰብዓዊ ተቋም አይኖርም። መዳናቸው የተመካው በአምላክ ላይ ብቻ ይሆናል። ታዲያ የይሖዋ ሕዝቦች፣ ጥፋት ከፊት ለፊታቸው ሲደቀንባቸው ምን ያደርጋሉ?
3 የይሖዋ አገልጋይ እንደመሆንህ መጠን ይሖዋ ከታላቁ መከራ ሕዝቡን ማዳን እንደሚችልና ይህንንም እንደሚያደርግ እምነት አለህ? ሐዋርያው ጴጥሮስ እንዲህ በማለት ጽፏል፦ “ይሖዋ፣ ለአምላክ ያደሩ ሰዎችን ከፈተና እንዴት እንደሚያድንና ዓመፀኛ ሰዎችን ደግሞ በፍርድ ቀን ለሚደርስባቸው ጥፋት እንዴት ጠብቆ እንደሚያቆይ ያውቃል።” (2 ጴጥ. 2:9) ይሖዋ ከዚህ ቀደም ሕዝቡን ለማዳን በወሰዳቸው እርምጃዎች ላይ ማሰላሰላችን የወደፊቱን ጊዜ በልበ ሙሉነት እንድንጠባበቅ ያስችለናል። እስቲ ይሖዋ ሕዝቡን በማዳን ረገድ ባለው ችሎታ ላይ እንድንተማመን የሚያደርጉንን ሦስት ምሳሌዎች እንመልከት።
ከዓለም አቀፍ የጥፋት ውኃ መትረፍ
4. ከጥፋት ውኃው ጋር በተያያዘ ሁሉም ነገር በተባለው ጊዜ መከናወን የነበረበት ለምንድን ነው?
4 በመጀመሪያ በኖኅ ዘመን ስለተከሰተው የጥፋት ውኃ የሚናገረውን
ዘገባ እንመልከት። የይሖዋ ፈቃድ እንዲፈጸም ከተፈለገ ሁሉም ነገር በተባለው ጊዜ ላይ መከናወን ነበረበት። የጥፋት ውኃው ከመምጣቱ በፊት ግዙፉን መርከብ የመገንባቱ ሥራ መጠናቀቅ እንዲሁም እንስሳቱ ወደ መርከቡ መግባት ነበረባቸው። የዘፍጥረት መጽሐፍ ይሖዋ የጥፋት ውኃው የሚመጣበትን ቀን የወሰነው መርከቡ ተገንብቶ ካለቀ በኋላ እንደሆነ አይናገርም፤ በሌላ አባባል የመርከቡ ግንባታ ከታሰበው ጊዜ ቢዘገይ የጥፋት ውኃው የሚመጣበትን ጊዜ ለመቀየር እንዲያመቸው በማሰብ ቀኑን አስቀድሞ ከመወሰን መቆጠብ አላስፈለገውም። ከዚህ ይልቅ ስለ መርከቡ ግንባታ ለኖኅ ምንም ነገር ከመናገሩ ከረጅም ጊዜ በፊት ይሖዋ የጥፋት ውኃው የሚጀምርበትን ቀን ወስኖ ነበር። ይህን እንዴት እናውቃለን?5. በዘፍጥረት 6:3 ላይ እንደተገለጸው ይሖዋ ምን ውሳኔ አስተላለፈ? ውሳኔውን ያስተላለፈውስ መቼ ነው?
5 መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ በሰማይ አንድ ውሳኔ እንዳሳለፈ ይናገራል። በዘፍጥረት 6:3 ላይ እንደተገለጸው ይሖዋ እንዲህ ብሏል፦ “ሰው ሟች ስለ ሆነ መንፈሴ እያዘነ ከእርሱ ጋር ለዘላለም አይኖርም፤ ዕድሜው 120 ዓመት ይሆናል።” ይሖዋ ይህን የተናገረው የሰዎችን አማካይ ዕድሜ ለመግለጽ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ፈሪሃ አምላክ የሌላቸውን ሰዎች ከምድረ ገጽ ለማስወገድ የቀጠረውን ጊዜ የሚገልጽ የፍርድ ውሳኔ ነው። * የጥፋት ውኃው የጀመረው በ2370 ዓ.ዓ. ስለሆነ አምላክ ይህን ውሳኔ ያስተላለፈው በ2490 ዓ.ዓ. ነው ብለን መደምደም እንችላለን። በዚያን ጊዜ ኖኅ ዕድሜው 480 ዓመት ነበር። (ዘፍ. 7:6) ከ20 ዓመት በኋላ ማለትም በ2470 ዓ.ዓ. ኖኀ ልጅ መውለድ ጀመረ። (ዘፍ. 5:32) የጥፋት ውኃው ሊመጣ የቀረው ጊዜ አንድ መቶ ዓመት ገደማ ቢሆንም ኖኅ የሰውን ዘር ከጥፋት ከማዳን ጋር በተያያዘ ስለሚጫወተው ልዩ ሚና እስከዚያን ጊዜ ድረስ ይሖዋ አልገለጸለትም። ታዲያ አምላክ ይህን ቀን ለማሳወቅ ምን ያህል ጊዜ መጠበቅ ነበረበት?
6. ይሖዋ፣ ኖኅን መርከብ እንዲሠራ ያዘዘው መቼ ነው?
6 ይሖዋ ወደፊት ስለሚያደርገው ነገር ለኖኅ ከመንገሩ በፊት አሥርተ ዓመታት ሳይጠብቅ አልቀረም። እዚህ መደምደሚያ ላይ እንድንደርስ ያደረገን ምንድን ነው? በመንፈስ መሪነት የተጻፈው ዘገባ እንደሚጠቁመው አምላክ ኖኅን መርከብ እንዲሠራ ሲያዘው ልጆቹ አድገው ትዳር መሥርተው ነበር። ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “ካንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እመሠርታለሁ። አንተና ወንዶች ልጆችህ፣ ሚስትህና የልጆችህ ሚስቶች ከአንተ ጋር ወደ መርከቧ ትገባላችሁ።” (ዘፍ. 6:9-18) በመሆኑም ኖኅ መርከብ የመሥራት ተልእኮውን የተቀበለው የጥፋት ውኃው ሊመጣ 40 ወይም 50 ዓመት ሲቀረው ነው ብለን መናገር እንችላለን።
7. (ሀ) ኖኅና ቤተሰቡ እምነት እንደነበራቸው ያሳዩት እንዴት ነው? (ለ) አምላክ የጥፋት ውኃው የሚመጣበትን ትክክለኛ ጊዜ ለኖኅ የነገረው መቼ ነው?
7 ኖኅና ቤተሰቡ መርከቡን በሚገነቡበት ወቅት፣ አምላክ ዓላማውን ስለሚፈጽምበት መንገድና የጥፋት ውኃው ስለሚጀምርበት ጊዜ ጥያቄ ሳይፈጠርባቸው አልቀረም። ይሁንና እነዚህን ዝርዝር ነገሮች አለማወቃቸው መርከቡን ከመገንባት አላገዳቸውም። የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ “ኖኅም ሁሉን እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ” ይላል። (ዘፍ. 6:22) የጥፋት ውኃው ከመምጣቱ ከሰባት ቀን በፊት ይኸውም ኖኅና ቤተሰቡ እንስሳቱን ወደ መርከብ ለማስገባት እንዲችሉ በቂ ጊዜ ከሰጣቸው በኋላ ይሖዋ የጥፋት ውኃው የሚመጣበትን ትክክለኛ ጊዜ ለኖኅ ነገረው። በመሆኑም “ኖኀ በተወለደ በ600ኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ቀን” ላይ የሰማይ መስኮቶች ተከፍተው የጥፋት ውኃው በወረደ ጊዜ ሁሉም ነገር ተጠናቅቆ ነበር።—ዘፍ. 7:1-5, 11
8. ስለ ጥፋት ውኃ የሚናገረው ዘገባ ይሖዋ ሕዝቡን መቼ እንደሚያድን የሚያውቅ አምላክ ስለመሆኑ ያለንን እምነት የሚያጠናክርልን እንዴት ነው?
8 ስለ ጥፋት ውኃው የሚናገረው ዘገባ ይሖዋ የቀጠረውን ጊዜ የመጠበቅ ብቻ ሳይሆን ሕዝቡን የማዳን ችሎታም እንዳለው ያረጋግጣል። ይህን ሥርዓት ለማጥፋት የቀጠረው ቀን እየቀረበ ነው፤ ማቴ. 24:36፤ ዕንባቆም 2:3ን አንብብ።
እንግዲያው ይሖዋ ያሰበው ነገር በሙሉ፣ ‘ቀኑና ሰዓቱ’ ሳይዛነፍ እሱ በወሰነው ጊዜ እንደሚመጣ እርግጠኛ መሆን እንችላለን።—ቀይ ባሕር ላይ አዳናቸው
9, 10. ይሖዋ የግብፅን ሠራዊት ወጥመድ ውስጥ ለማስገባት በሕዝቦቹ የተጠቀመው እንዴት ነው?
9 እስካሁን እንደተመለከትነው ይሖዋ ከዓላማው አፈጻጸም ጋር በተያያዘ ነገሮች የሚከናወኑበትን ጊዜ ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር ችሎታ አለው። በሁለተኛ ደረጃ የምንመለከተው ምሳሌ ይሖዋ ሕዝቦቹን የሚያድን አምላክ ስለመሆኑ እምነት እንድናሳድር የሚያስችለንን ሌላ ምክንያት ይጠቁመናል፤ ከዚህ ምሳሌ እንደምንረዳው ይሖዋ ፈቃዱን ለመፈጸም ገደብ የለሽ ኃይሉን ይጠቀማል። ይሖዋ አገልጋዮቹን እንደሚያድናቸው የተረጋገጠ ቢሆንም ጠላቶቹን ወጥመድ ውስጥ ለማስገባት በሕዝቦቹ የሚጠቀምበት ጊዜ አለ። ይሖዋ እስራኤላውያንን ከግብፅ ባርነት ባወጣቸው ጊዜ ይህ ሁኔታ ታይቷል።
10 ከግብፅ የወጡት እስራኤላውያን ቁጥራቸው ወደ ሦስት ሚሊዮን ገደማ ይሆናል። ይሖዋ፣ ሕዝቡን እየመራ እንዲወስድ ለሙሴ የነገረው አቅጣጫ ግራ የሚያጋባ ይመስል ነበር፤ ይህም ፈርዖን፣ እስራኤላውያን መግቢያ መውጫው ጠፍቷቸው እየተቅበዘበዙ እንዳሉ አድርጎ እንዲያስብ አደረገው። (ዘፀአት 14:1-4ን አንብብ።) አንድ እንስሳ ወጥመድ ላይ የተቀመጠለትን ነገር ለመብላት እንደሚጓጓ ሁሉ ፈርዖንም የቀድሞ ባሮቹን ቀይ ባሕር ላይ እንደሚይዛቸው በማሰብ የጦር ሠራዊቱን አስከትሎ እነሱን ማሳደዱን ተያያዘው። በሰብዓዊ ዓይን ሲታይ እስራኤላውያን ምንም ዓይነት ማምለጫ ቀዳዳ ያላቸው አይመስልም። (ዘፀ. 14:5-10) እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ምንም የሚያሰጋቸው ነገር አልነበረም። እንደዚህ የምንለው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ይሖዋ እነሱን ለማዳን እጁን ጣልቃ ሊያስገባ ነው።
11, 12. (ሀ) ይሖዋ ሕዝቦቹን ለማዳን እጁን ጣልቃ ያስገባው እንዴት ነው? ውጤቱስ ምን ነበር? (ለ) ይህ ዘገባ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረናል?
11 እስራኤላውያንን ሲመራቸው የነበረው ‘የደመና ዓምድ’ ከበስተኋላቸው ሄዶ የፈርዖን ሠራዊት በጨለማ እንዲዋጥ በማድረግ ሠራዊቱ ወደፊት እንዳይሄድ አገደው። በእስራኤላውያን በኩል ግን የደመናው ዓምድ ተአምራዊ በሆነ መንገድ ጨለማው ዘፀአት 14:19, 20ን አንብብ።) ከዚያም ይሖዋ ብርቱ የምሥራቅ ነፋስ አስነስቶ ባሕሩን ለሁለት በመክፈል “ደረቅ ምድር አደረገው።” ይህም ረዘም ያለ ጊዜ እንደወሰደ ምንም ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም ዘገባው ነፋሱ “ሌሊቱን በሙሉ” ሲነፍስ እንደነበረ ይናገራል። ከዚያም “እስራኤላውያን ውሃው በግራና በቀኝ እንደ ግድግዳ ሆኖ በየብስ በባሕሩ ውስጥ አለፉ።” በጦር ሠረገሎች ከሚገሰግሱት የፈርዖን ሠራዊት አንጻር ሲታይ የእስራኤላውያን ጉዞ የዔሊ ጉዞ ነበር ለማለት ይቻላል። ይሁን እንጂ ይሖዋ ለእስራኤላውያን እየተዋጋላቸው ስለነበር ግብፃውያን ሊደርሱባቸው አልቻሉም። ይሖዋ “በግብፃውያን ሰራዊት ላይ ሽብር ላከባቸው። መንዳት እንዳይችሉም የሠረገላዎቹን መሽከርከሪያዎች አቈላለፈባቸው።”—ዘፀ. 14:21-25
ብርሃን እንዲሆን አደረገ። (12 እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ባሕሩ ዳርቻ በሰላም ከደረሱ በኋላ ይሖዋ ሙሴን “ውሃው ግብፃውያንን ሠረገሎቻቸውንና ፈረሰኞቻቸውን ተመልሶ እንዲሸፍናቸው እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርጋ” አለው። የግብፅ ወታደሮች እየተወረወረ ከሚመጣው ውኃ ለመሸሽ ቢሞክሩም ይሖዋ “በባሕሩ ውስጥ ጣላቸው።” ከዚህ ሁኔታ አመልጣለሁ ብሎ ማሰብ ዘበት ነበር። ከመካከላቸው “አንድም እንኳ አልተረፈም።” (ዘፀ. 14:26-28) በዚህ መንገድ ይሖዋ ሕዝቡን ከማንኛውም ሁኔታ የማዳን ኃይል እንዳለው አሳይቷል።
በኢየሩሳሌም ላይ ከደረሰው ጥፋት ማምለጥ
13. ኢየሱስ በዘመኑ ለሚገኙ ክርስቲያኖች ምን መመሪያ ሰጥቶ ነበር? በተከታዮቹ አእምሮ ውስጥ ምን ዓይነት ጥያቄ ተፈጥሮባቸው ሊሆን ይችላል?
13 ይሖዋ ዓላማውን ለመፈጸም ነገሮች የሚከናወኑበትን መንገድ በትክክል ያውቃል። ሦስተኛው ምሳሌ ይህንን ያጎላል፤ ታሪኩ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ከተከሰተው የኢየሩሳሌም ከበባ ጋር የተያያዘ ነው። ይሖዋ ኢየሩሳሌም በ70 ዓ.ም. ከመጥፋቷ በፊት በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች ከጥፋት መዳን የሚችሉበትን መመሪያ በልጁ አማካኝነት ሰጥቷቸዋል። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፦ “በነቢዩ ዳንኤል በተነገረው መሠረት ጥፋት የሚያመጣው ርኩስ ነገር በተቀደሰ ስፍራ ቆሞ ስታዩ . . . በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ።” (ማቴ. 24:15, 16) ይሁንና የኢየሱስ ተከታዮች ይህ ትንቢት እየተፈጸመ መሆኑን ማወቅ የሚችሉት እንዴት ነው?
14. በትንቢቱ ላይ የተጠቀሱት ነገሮች መከሰታቸው የኢየሱስን መመሪያ ግልጽ ያደረገው እንዴት ነው?
14 ክርስቲያኖች፣ ኢየሱስ የተናገረው ነገር ይበልጥ ግልጽ የሆነላቸው በትንቢቱ ላይ የጠቀሳቸው ነገሮች መከሰት ሲጀምሩ ነው። በ66 ዓ.ም. በሴስቲየስ ጋለስ የሚመራው የሮም ሠራዊት የአይሁዳውያንን ዓመፅ ለማስቆም ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። ዜሎት በመባል የሚታወቁት የአይሁድ ዓማፅያን ቤተ መቅደስ ውስጥ ገብተው በመሸጉ ጊዜ የሮም ወታደሮች የቤተ መቅደሱን ግንብ ማፍረስ ጀመሩ። ንቁ ለሆኑ ክርስቲያኖች ይህ ምን ትርጉም እንዳለው ግልጽ ነበር፤ የጣዖት አርማ (“ርኩስ ነገር”) የያዘው የአረማውያን ሠራዊት የቤተ መቅደሱ ግንብ (“በተቀደሰ ስፍራ”) ድረስ ተጠግቶ ነበር። የኢየሱስ ተከታዮች ‘ወደ ተራሮች የሚሸሹበት’ ጊዜ አሁን ነው። ይሁንና ከተከበበችው ከተማ መውጣት የሚችሉት እንዴት ነው? ነገሮች ባልታሰበ ሁኔታ መልካቸውን ሊቀይሩ ነው።
15, 16. (ሀ) ኢየሱስ ምን ግልጽ መመሪያ ሰጥቷል? ተከታዮቹ ይህን መመሪያ መታዘዛቸው በጣም አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? (ለ) መዳናችን የተመካው በምን ላይ ነው?
ማቴዎስ 24:17, 18ን አንብብ።) እንዲህ ያለ ፈጣን እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ነበር? የዚህ ጥያቄ መልስ ብዙም ሳይቆይ ግልጽ ሆኗል። ከተወሰኑ ቀናት በኋላ የአይሁድ ዓማፅያን ወደ ከተማዋ ተመልሰው የኢየሩሳሌምና የአይሁድ ነዋሪዎች በዓመፁ እንዲካፈሉ ማስገደድ ጀመሩ። የተለያዩ የአይሁድ አንጃዎች የበላይነት ለማግኘት በሚያደርጉት ትግል ሳቢያ በከተማዋ ውስጥ ያለው ሁኔታ ከዕለት ወደ ዕለት እየከፋ ሄደ። ከከተማዋ ሸሽቶ መውጣትም በጣም አስቸጋሪ እየሆነ መጣ። የሮም ሠራዊት በ70 ዓ.ም. ተመልሶ ሲመጣ ደግሞ ከከተማዋ ሸሽቶ መውጣት ፈጽሞ የማይታሰብ ነገር ሆነ። (ሉቃስ 19:43) ከተማዋን ለቀው ለመውጣት ሲያቅማሙ የነበሩ ሁሉ ወጥመድ ውስጥ ገቡ! ወደ ተራሮች የሸሹት ክርስቲያኖች ግን የኢየሱስን መመሪያ መከተላቸው ሕይወታቸውን አትርፎላቸዋል። ይሖዋ ሕዝቡን እንዴት እንደሚያድን በገዛ ዓይናቸው ተመልክተዋል። ታዲያ ከዚህ ዘገባ ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?
15 ሴስቲየስ ጋለስና ሠራዊቱ ባልታወቀ ምክንያት ኢየሩሳሌምን ትተው ወደኋላ አፈገፈጉ። ዓማፅያኑም የሮም ወታደሮችን ማባረር ጀመሩ። ሁለቱም ወገኖች ከተማዋን ለቀው ስለሄዱ የኢየሱስ ተከታዮች ለመሸሽ ጥሩ አጋጣሚ ተከፈተላቸው። ኢየሱስ፣ ቁሳዊ ነገሮቻቸውን በመተው ሳይዘገዩ ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ ለተከታዮቹ ግልጽ መመሪያ ሰጥቷቸው ነበር። (16 በታላቁ መከራ ወቅት በትንቢት የተነገሩት ነገሮች መፈጸም ሲጀምሩ ክርስቲያኖች ከአምላክ ቃልና ከድርጅቱ የሚያገኙትን መመሪያ መከተል ያስፈልጋቸዋል። ለምሳሌ ክርስቲያኖች ‘ወደ ተራሮች እንዲሸሹ’ ኢየሱስ የሰጠው መመሪያ ዘመናዊ ፍጻሜም ይኖረዋል። ይህ መመሪያ ተግባራዊ የሚሆነው እንዴት ነው የሚለው ጉዳይ ጊዜ የሚያሳየን ይሆናል። * ይሁንና ይህን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ የምንጀምርበት ጊዜ ሲደርስ ይሖዋ ሁኔታውን ግልጽ እንደሚያደርግልን ምንም ጥርጥር የለውም። መዳናችን የተመካው ታዛዥ በመሆናችን ላይ ስለሆነ ራሳችንን እንዲህ በማለት መጠየቃችን ተገቢ ነው፦ ‘ይሖዋ በዛሬው ጊዜ ለሕዝቡ መመሪያዎችን በሚያስተላልፍበት ጊዜ ምን ምላሽ እሰጣለሁ? ፈጣን እርምጃ እወስዳለሁ ወይስ ለመታዘዝ አንገራግራለሁ?’—ያዕ. 3:17
የወደፊቱን ጊዜ በልበ ሙሉነት መጠባበቅ
17. የዕንባቆም ትንቢት ወደፊት በአምላክ ሕዝቦች ላይ ከሚሰነዘረው ጥቃት ጋር በተያያዘ ምን ይገልጻል?
17 እስቲ አሁን በመግቢያችን ላይ ስለጠቀስነው ጎግ የሚሰነዝረው መጠነ ሰፊ ጥቃት መለስ ብለን እናስብ። ዕንባቆም ይህን ጊዜ አስመልክቶ እንዲህ የሚል ትንቢት ተናግሯል፦ “እኔ ሰማሁ፤ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከንፈሬ ከድምፁ የተነሣ ተንቀጠቀጠ፤ ፍርሀት እስከ ዐጥንቴ ዘልቆ ገባ፤ እግሬም ተብረከረከ፤ ሆኖም [አምላክ] በሚወረን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፣ የጥፋትን ቀን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ።” (ዕን. 3:16) ነቢዩ በአምላክ ሕዝብ ላይ ስለሚሰነዘረው ጥቃት ሲሰማ ልቡ ርዷል፣ ከንፈሩ ተንቀጥቅጧል እንዲሁም ጉልበቱ ከድቶታል። የጎግ ሠራዊት በሚወረን ወቅት የሚኖረው ሁኔታ ምን ያህል አስፈሪ ሊሆንብን እንደሚችል የዕንባቆም ስሜት ይጠቁማል። ያም ቢሆን ነቢዩ ዕንባቆም፣ አምላክ ሕዝቦቹን እንደሚያድን በመተማመን የይሖዋን ታላቅ ቀን በትዕግሥት ለመጠባበቅ ፈቃደኛ ነበር። እኛም እንዲህ ዓይነት እምነት ሊኖረን ይገባል።—ዕን. 3:18, 19
18. (ሀ) በቅርቡ በአምላክ ሕዝቦች ላይ የሚሰነዘረው ጥቃት ሊያስፈራን የማይገባው ለምንድን ነው? (ለ) በሚቀጥለው ርዕስ የትኛውን ጉዳይ እንመረምራለን?
18 ከላይ የተመለከትናቸው ሦስቱ ምሳሌዎች እንደሚያሳዩት ይሖዋ ያለምንም ጥርጥር ሕዝቡን እንዴት እንደሚያድን ያውቃል። ዓላማው ፈጽሞ ሊጨናገፍ አይችልም፤ ድል የይሖዋ እንደሚሆን የተረጋገጠ ነው። ይሖዋ ድል በሚጎናጸፍበት ወቅት የደስታው ተካፋይ ለመሆን ከፈለግን ግን እስከመጨረሻው ታማኞች መሆን ይጠበቅብናል። ታዲያ ይሖዋ በአሁኑ ጊዜ ንጹሕ አቋማችንን ጠብቀን እንድንመላለስ የሚረዳን እንዴት ነው? የሚቀጥለው የጥናት ርዕስ በዚህ ላይ ያተኩራል።
[የግርጌ ማስታወሻዎች]
^ አን.16 የግንቦት 1, 1999 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 19ን ተመልከት።
[የአንቀጾቹ ጥያቄዎች]
[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
እስራኤላውያን የፈርዖንን ሠራዊት የሚፈሩበት ምክንያት ነበራቸው?