በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ደግነት​—ለተመረረ ሰው ፍቱን መድኃኒት!

ደግነት​—ለተመረረ ሰው ፍቱን መድኃኒት!

ደግነት​—ለተመረረ ሰው ፍቱን መድኃኒት!

በኔዘርላንድ የሚኖሩ ዦርዥ እና ማኖን የተባሉ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ሪአ ለተባሉ አንዲት አረጋዊት የመንግሥቱን ምሥራች ለመስበክ ቢሞክሩም ሴትየዋ ጥሩ ፊት አላሳዩአቸውም ነበር። ይሁንና በውይይቱ መሃል እኚህ ሴት ሁለት ባሎቻቸውንና አንድ ወንድ ልጃቸውን በሞት እንዳጡና እሳቸው ደግሞ አርትራይተስ በተባለ በሽታ በጣም እንደሚሠቃዩ ተረዱ። ሴትየዋ በጭውውቱ ወቅት ትንሽ ቢረጋጉም እስኪለያዩ ድረስ ወዳጃዊ መንፈስ አይታይባቸውም ነበር።

ዦርዥ፣ ሴትየዋ በብቸኝነታቸውና ባሳለፉት ሕይወት እጅግ የተመረሩ ስለሆኑ አበባ ይዘው ቢጠይቋቸው ጥሩ እንደሆነ ለማኖን ሐሳብ አቀረበላት። አበባውን ይዘው ሲሄዱ አረጋዊቷ ሪአ በጣም ተደነቁ። ይሁንና የመጡበት ሰዓት ቁጭ ብሎ ለመጫወት አመቺ ስላልነበር ሌላ ጊዜ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዙ። ዦርዥ እና ማኖን በቀጠሮው ቀን ተመልሰው ሲመጡ በር የሚከፍትላቸው ሰው አጡ። በተለያዩ ጊዜያት ተመልሰው ቢሄዱም ሊያገኟቸው አልቻሉም። በመሆኑም ‘እኚህ ሴት እኛን ሊያገኙ አልፈለጉም ማለት ነው’ ብለው አሰቡ።

አንድ ቀን ግን ዦርዥ አረጋዊቷን ቤታቸው አገኛቸው። እኚህ ሴት በቀጠሮው ያልተገኙት ሆስፒታል በመግባታቸው እንደነበር በመግለጽ ይቅርታ ጠየቁ። ከዚያም “እናንተ ከሄዳችሁ በኋላ ምን ማድረግ እንደጀመርኩ ብነግራችሁ በጣም ትገረማላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ጀመርኩ እኮ!” አሉ። በዕለቱ አስደሳች ውይይት ያደረጉ ከመሆኑም በላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ተጀመረላቸው።

አረጋዊቷ ሪአ፣ መጽሐፍ ቅዱስን እያጠኑ ሲሄዱ መመረራቸውን አቁመው ደስተኛና ደግ ሴት ሆኑ። የአልጋ ቁራኛ ቢሆኑም የተማሩትን ነገር ሊጠይቃቸው ለሚመጣ ሰው ሁሉ ማካፈል ጀመሩ። ጤንነታቸው በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ አዘውትረው ለመገኘት ባያስችላቸውም ወንድሞችና እህቶች ሲጠይቋቸው ደስ ይላቸው ነበር። ልክ 82 ዓመት ሲሞላቸው በዕለቱ በተደረገ የወረዳ ስብሰባ ላይ የተገኙ ሲሆን ራሳቸውን ለአምላክ መወሰናቸውን ለማሳየትም ተጠመቁ።

እኚህ ሴት ከተጠመቁ ከጥቂት ወራት በኋላ ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከጊዜ በኋላም የጻፉት ግጥም ተገኝቷል። በግጥሙ ውስጥ በስተርጅና ብቸኛ መሆን ያለውን አበሳ እንዲሁም ደግነት ማሳየት ያለውን ጥቅም ጎላ አድርገው ገልጸዋል። ማኖን “ግጥሙን ሳነብ ልቤ በጥልቅ ተነካ፤ ለእሳቸው ደግነት እንድናሳያቸው ይሖዋ ስለረዳን በጣም ደስ ብሎኛል” በማለት ተናግራለች።

በእርግጥም ይሖዋ አፍቃሪና ደግ መሆኑ እኛም እሱን እንድንመስል ያነሳሳናል። (ኤፌ. 5:1, 2) ‘ደጎች በመሆን ብቁ የአምላክ አገልጋዮች መሆናችንን’ የምናሳይ ከሆነ አገልግሎታችን ፍሬያማ ይሆናል።​—2 ቆሮ. 6:4, 6