በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በደንብ አንብበሃቸዋል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

ያልተገራ አንደበት የሚያስከትለውን እሳት ማጥፋት የምንችለው እንዴት ነው?

ልባችንን መመርመር ይኖርብናል። አንድን ወንድም ከመንቀፍ ይልቅ እንዲህ ያለ አመለካከት እንዲያድርብን ያደረገን ምን እንደሆነ መመርመራችን ተገቢ ነው። እሱን የነቀፍነው እኛ የተሻልን ሆነን ለመታየት ስለምንፈልግ ይሆን? በተጨማሪም ነቃፊ መሆን የተፈጠረውን ውጥረት ይበልጥ ያባብሰዋል።—8/15 ገጽ 21

ሕጉ አምላክ ለሴቶች ያለውን አመለካከት የሚያንጸባርቀው እንዴት ነው?

እስራኤላዊ ሴቶች ከፍተኛ ነፃነት የነበራቸው ከመሆኑም በላይ የትምህርት ዕድል ያገኙ ነበር። ሴቶች ይከበሩና መብቶቻቸው ይጠበቁላቸው ነበር።—9/1 ገጽ 5-7

የይሖዋ ቀን ከመምጣቱ በፊት የትኞቹ ነገሮች መፈጸም ይኖርባቸዋል?

“ሰላምና ደኅንነት” ይሆናል የሚል አዋጅ ይታወጃል። መንግሥታት በታላቂቱ ባቢሎን ላይ ጥቃት ሰንዝረው ያጠፏታል። በአምላክ ሕዝቦች ላይም ጥቃት ይሰነዘራል። የአርማጌዶን ጦርነት ይጀምራል፤ ከዚያም ሰይጣንና አጋንንቱ ወደ ጥልቁ ይጣላሉ።—9/15 ገጽ 4

መጨረሻው የሚመጣበትን ጊዜ አለማወቃችን የሚጠቅመን እንዴት ነው?

መጨረሻው የሚመጣበትን ጊዜ አለማወቃችን የልባችንን ትክክለኛ ዝንባሌ ለማወቅ ያስችለናል። የአምላክን ልብ ደስ ለማሰኘት የሚያስችል አጋጣሚ ይከፍትልናል። እንዲሁም ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ሕይወት እንድንመራና በአምላክም ሆነ በቃሉ ላይ ሙሉ እምነት እንድንጥል ምክንያት ይሆነናል። በተጨማሪም ዛሬ በሚደርሱብን መከራዎች ውስጥ በማለፍ እንድንጠራ ያስችለናል።—9/15 ገጽ 24-25

ገሃነመ እሳት እንዳለ ከሚያምን ሰው ጋር ስንወያይ ዘፍጥረት 3:19ን መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?

ጥቅሱ የሚናገረው አዳም ሲሞት ወደ አፈር እንደሚመለስ እንጂ ወደ ገሃነመ እሳት እንደሚሄድ አይደለም።—10/1 ገጽ 13

በራእይ 1:16, 20 ላይ በኢየሱስ ቀኝ እጅ ውስጥ እንዳሉ የተጠቀሱት ‘ሰባት ከዋክብት’ የሚያመለክቱት ማንን ነው?

እነዚህ “ከዋክብት” በዋነኝነት ቅቡዓን የበላይ ተመልካቾችን የሚያመለክቱ ሲሆን በጉባኤ ያሉትን ሁሉንም የበላይ ተመልካቾች ሊያመለክቱም ይችላሉ።—10/15 ገጽ 14

አንድ ቤተሰብ ዕዳ ውስጥ ቢገባ ከዚያ መውጣት የሚችለው እንዴት ነው?

አንድ ባልና ሚስት ስላለባቸው የገንዘብ ዕዳ ረጋ ብለው በግልጽ መነጋገር አለባቸው። በጀታቸውን መለስ ብሎ ማጤን ሊረዳቸው ይችላል። ገቢያቸውን ማሳደግ ወይም የቤተሰቡን ወጪ መቀነስ ይችሉ ይሆን? የትኛውን ዕዳ በቅድሚያ መክፈል እንዳለባቸው መወሰን ምናልባትም ከአበዳሪዎቻቸው ጋር ስለ ክፍያው መነጋገር ያስፈልጋቸው ይሆናል። ሆኖም ምክንያታዊ ሊሆኑና ለገንዘብ ተገቢ የሆነ አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል። (1 ጢሞ. 6:8)—11/1 ገጽ 19-21

በኢሳይያስ 50:4, 5 ላይ በተገለጸው መሠረት ኢየሱስ ትሑት መሆኑን ያሳየው እንዴት ነው?

ጥቅሱ “የተባ አንደበት” ያለው ሰው ‘ወደ ኋላ እንደማያፈገፍግ’ ይናገራል። ኢየሱስ አባቱ የሚሰጠውን ትምህርት በትኩረት በመከታተል ትሑት መሆኑን አሳይቷል። ኢየሱስ ከይሖዋ ለመማር ፈቃደኛ የነበረ ከመሆኑም ሌላ ጉጉት ነበረው፤ እንዲሁም አምላክ ኃጢአተኛ ለሆኑት የሰው ልጆች ምሕረት በማድረግ ያሳየውን ትሕትና በቅርበት ተመልክቷል።—11/15 ገጽ 11

የኢስቶኒያ ፖስታ ቤት ያወጣው የመታሰቢያ ቴምብር የይሖዋ ምሥክሮች ንጹሕ አቋማቸውን እንደጠበቁ የሚመሠክረው እንዴት ነው?

በ2007 የኢስቶኒያ ብሔራዊ ፖስታ ቤት የስታሊን መንግሥት በኢስቶናውያን ላይ ባካሄደው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ላይ ያተኮረ ቴምብር አወጣ። ቴምብሩ ላይ የሰፈረው 382 የሚለው ቁጥር በ1951 ከቤታቸው ተፈናቅለው ሩቅ በሆኑ የሩሲያ ግዛቶች ውስጥ ባሉ ካምፖች የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ የተጋዙ የይሖዋ ምሥክሮችንና ልጆቻቸውን ብዛት ያመለክታል።—12/1 ገጽ 27-28