በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአንባቢያን ጥያቄዎች

የአንባቢያን ጥያቄዎች

እስራኤላውያን፣ ወንጀለኞችን ግንድ ላይ በመስቀል በሞት ይቀጡ ነበር?

በጥንት ጊዜ የነበሩ በርካታ ብሔራት አንዳንድ ወንጀለኞችን ግንድ ወይም ምሰሶ ላይ በመስቀል በሞት ይቀጡ ነበር። ሮማውያን እንዲህ ያለውን ግለሰብ ግንድ ላይ በማሰር ወይም በመቸንከር ይቀጡ የነበረ ሲሆን ግለሰቡ በሥቃይ፣ በጥም፣ በረሃብ እንዲሁም በቁርና በሐሩር አቅሙ ተዳክሞ እስኪሞት ድረስ ለበርካታ ቀናት በሕይወት ሊቀጥል ይችላል። ሮማውያን ስቅላትን የከፋ ወንጀል የፈጸሙ ሰዎች የሚጠብቃቸው ክብር የሚነካ ቅጣት አድርገው ይመለከቱ ነበር።

በጥንቱ የእስራኤል ብሔር ውስጥስ ምን ይደረግ ነበር? እስራኤላውያን፣ ወንጀለኞችን ግንድ ላይ በመስቀል በሞት ይቀጡ ነበር? የሙሴ ሕግ እንዲህ የሚል ድንጋጌ ይዟል፦ “አንድ ሰው ለሞት የሚያበቃ በደል ፈጽሞ ቢገደልና በድኑ በዕንጨት ላይ ቢሰቀል፤ በድኑን በዕንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድረው፤ . . . በዚያኑ ዕለት ቅበረው።” (ዘዳ. 21:22, 23) በመሆኑም የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት በተጻፉበት ዘመን አንድ ሰው የሞት ቅጣት ሲበየንበት ከተገደለ በኋላ ግንድ ወይም ዛፍ ላይ ይሰቀል እንደነበረ በግልጽ መረዳት ይቻላል።

በዚህ ረገድ ዘሌዋውያን 20:2 እንዲህ ይላል፦ “ከልጆቹ አንዱን ለሞሎክ የሚሰጥ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በእስራኤል የሚኖር መጻተኛ ይገደል፤ እርሱንም የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው።” በተጨማሪም ‘ሙታን ጠሪዎች ወይም መናፍስት ጠሪዎች’ በሞት ይቀጡ ነበር። እንዴት? ሕዝቡ ‘በድንጋይ ይወግራቸው’ ነበር።—ዘሌ. 20:27

ዘዳግም 22:23, 24 እንዲህ ይላል፦ “አንድ ሰው የታጨች ድንግል በከተማ ውስጥ አግኝቶ ከእርሷ ጋር ቢተኛ፣ ልጃገረዲቱ በከተማ ውስጥ እያለች አስጥሉኝ ብላ ስላልጮኸች፣ ሰውየውም የሌላን ሰው ሚስት አስገድዶ ስለ ደፈረ፣ ሁለቱንም ወደ ከተማ ደጃፍ ወስዳችሁ እስኪሞቱ ድረስ በድንጋይ ውገሯቸው። ክፉውን ከመካከልህ ማስወገድ አለብህ።” እንግዲያው የጥንቶቹ እስራኤላውያን ከባድ ወንጀል የፈጸሙ ሰዎችን የሚገድሉበት ዋነኛው መንገድ በድንጋይ መውገር ነበር። *

የዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት በተጻፉበት ዘመን አንድ ሰው የሞት ቅጣት ሲበየንበት ከተገደለ በኋላ ግንድ ወይም ዛፍ ላይ ይሰቀል እንደነበረ በግልጽ መረዳት ይቻላል

ዘዳግም 21:23 “በዕንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነው” ይላል። “በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ” የአንድ ክፉ ሰው አስከሬን፣ በአደባባይ እንዲቆይ መደረጉ ለእስራኤላውያን የሚያስተላልፈው መልእክት እንደነበረ ጥርጥር የለውም። በእርግጥም የግለሰቡ አስከሬን በዚህ ዓይነት ሁኔታ በእንጨት ወይም በዛፍ ላይ መሰቀሉ ለሌሎች የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ሆኖ ያገለግላል።

^ አን.6 በርካታ ምሁራን በሕጉ መሠረት አንድ ወንጀለኛ በእንጨት ላይ ከመሰቀሉ በፊት ይገደል እንደነበር ያምናሉ። ይሁንና በመጀመሪያው መቶ ዘመን አይሁዳውያን አንዳንድ ወንጀለኞች በሕይወት እያሉ በእንጨት ላይ ተሰቅለው እንዲሞቱ ያደርጉ እንደነበር የሚጠቁም ማስረጃ አለ።