በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አዲስ የበላይ አካል አባል

አዲስ የበላይ አካል አባል

መስከረም 5, 2012 ረቡዕ ዕለት በዩናይትድ ስቴትስና በካናዳ ለሚገኙት የቤቴል ቤተሰቦች አዲስ የበላይ አካል አባል እንደተጨመረ የሚገልጽ ማስታወቂያ ተነግሮ ነበር። ወንድም ማርክ ሳንደርሰን ከመስከረም 1, 2012 አንስቶ የበላይ አካል አባል በመሆን ማገልገል ጀምሯል።

ወንድም ማርክ ሳንደርሰን ያደገው በሳንዲያጎ፣ ካሊፎርኒያ ዩናይትድ ስቴትስ ነው፤ ወላጆቹ ክርስቲያኖች ሲሆኑ የተጠመቀው የካቲት 9, 1975 ነው። ከመስከረም 1, 1983 ጀምሮ በሳስካችዋን፣ ካናዳ አቅኚ ሆኖ ማገልገል ጀመረ። ከዚያም ታኅሣሥ 1990 በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከአገልጋዮች ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት (አሁን ለነጠላ ወንድሞች የተዘጋጀ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ይባላል) ሰባተኛው ክፍል ተመረቀ። ሚያዝያ 1991 ካናዳ በሚገኘው ኒውፋውንድላንድ ደሴት ውስጥ ልዩ አቅኚ ሆኖ እንዲያገለግል ተመደበ። በተተኪ የወረዳ የበላይ ተመልካችነት የተወሰነ ጊዜ ካገለገለ በኋላ የካቲት 1997 የካናዳ ቤቴል ቤተሰብ አባል ሆነ። ከዚያም ኅዳር 2000 ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ በመዛወር በመጀመሪያ በሆስፒታል መረጃ አገልግሎት ክፍል ቀጥሎም በአገልግሎት ዘርፍ ውስጥ አገልግሏል።

መስከረም 2008 ወንድም ማርክ ሳንደርሰን ለቅርንጫፍ ኮሚቴ አባላት በተዘጋጀው ትምህርት ቤት ከተካፈለ በኋላ የፊሊፒንስ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል ሆኖ ማገልገል ጀመረ። በኋላም መስከረም 2010 ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲመለስ ግብዣ የቀረበለት ሲሆን በዚያም በበላይ አካሉ ሥር ካሉት ኮሚቴዎች አንዱ በሆነው በአገልግሎት ኮሚቴ ውስጥ ረዳት ሆኖ አገልግሏል።