መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም መስከረም 2013

ይህ እትም ጥበብ የታከለበት ውሳኔ ማድረግ፣ ከይሖዋ አምላክ ጋር ያለንን ዝምድና ማጠናከርና ከይሖዋ ማሳሰቢያዎች ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

ከንጽጽሮች ጥቅም ማግኘት

ኢየሱስ ብዙ ጊዜ በንጽጽሮች ይጠቀም ነበር። አንተም ሌሎችን መጽሐፍ ቅዱስ ስታስተምር እንዴት ንጽጽሮችን መጠቀም እንደምትችል ከዚህ ርዕስ መማር ትችላለህ።

የይሖዋ ማሳሰቢያዎች እምነት የሚጣልባቸው ናቸው

ይሖዋ በማሳሰቢያዎች አማካኝነት ምንጊዜም ሕዝቦቹን ይመራል። በዛሬው ጊዜ በይሖዋ ማሳሰቢያዎች ላይ እምነት መጣል የምንችለው ለምንድን ነው?

ልባችሁ በይሖዋ ማሳሰቢያዎች ሐሴት ያድርግ

የይሖዋን ትእዛዛት መከተል ያስደስተናል? ወይስ አንዳንድ ጊዜ እንደ ሸክም እናያቸዋለን? በይሖዋ ማሳሰቢያዎች ላይ ያለንን እምነት መገንባት የምንችለው እንዴት ነው?

ተለውጣችኋል?

ሁሉም ክርስቲያኖች ‘የመለወጥ’ ጉዳይ ሊያሳስባቸው የሚገባው ለምንድን ነው? መለወጥ ምን ነገሮችን ይጨምራል? መለወጥ የምንችለውስ እንዴት ነው?

ጥበብ የታከለበት ውሳኔ አድርግ

የምናደርገው ውሳኔ ከአምላክ ፈቃድ ጋር የሚስማማ መሆኑን ማረጋገጥ የምንችለው እንዴት ነው? ያደረግነውን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ ምን ሊረዳን ይችላል?

አቅኚነት ከአምላክ ጋር ያለንን ዝምድና ያጠናክርልናል

አቅኚነት ከይሖዋ ጋር ያለህን ዝምድና ለማጠናከር ይረዳሃል እንድንል የሚያደርጉንን ስምንት ምክንያቶች በዚህ ርዕስ ውስጥ ተብራርተዋል። ብዙ በረከቶች በሚያስገኘው በዚህ የአገልግሎት መስክ ለመቀጠል ምን ሊረዳህ ይችላል?

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ዮሐንስ 11:35 ላይ እንደተገለጸው ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት ከማስነሳቱ በፊት እንባውን ያፈሰሰው ለምንድን ነው?