በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህ?

ታስታውሳለህ?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች በደንብ አንብበሃቸዋል? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

ኢየሱስ ‘በእስር ላሉት መናፍስት የሰበከላቸው’ መቼ ነው? (1 ጴጥ. 3:19)

ኢየሱስ ይህን ያደረገው ከሞት ከተነሳ ብዙም ሳይቆይ ይመስላል፤ እነዚህ ክፉ መናፍስት የሚጠብቃቸውን ተገቢ የቅጣት ፍርድ አውጇል።—6/15, page 23

በሁለተኛ ትዳር ውስጥ የሚያጋጥሙ ሦስት ተፈታታኝ ነገሮች የትኞቹ ናቸው?

የቀድሞ ትዳርህ ትዝታ በአሁኑ ትዳርህ ላይ ችግር እንዳይፈጥር ጥረት ማድረግ፣ አዲሷ የትዳር ጓደኛህ ከማታውቃቸው የቀድሞ ወዳጆችህ ጋር ያለህ ግንኙነት እንዲሁም የቀድሞ የትዳር ጓደኛህ ለአንተ ታማኝ ስላልነበረች በአዲሷ ባለቤትህ ላይ እምነት መጣል ተፈታታኝ ሊሆንብህ ይችላል።—7/1, pages 9-10

ኢየሱስ በበጎቹና በፍየሎቹ ላይ የሚፈርደው መቼ ነው? (ማቴ. 25:32)

ይህ የሚሆነው የሐሰት ሃይማኖት ከጠፋ በኋላ ኢየሱስ በሕዝቦች ላይ ለመፍረድ በሚመጣበት በታላቁ መከራ ወቅት ነው።—7/15, page 6

ስለ ስንዴውና እንክርዳዱ በሚናገረው ምሳሌ ላይ የተጠቀሱት ዓመፀኞች የሚያለቅሱትና በሐዘን ጥርሳቸውን የሚያፋጩት መቼ ነው? (ማቴ. 13:36, 41, 42)

ይህን የሚያደርጉት በታላቁ መከራ ወቅት ከጥፋቱ ማምለጥ እንደማይችሉ ሲገነዘቡ ነው።—7/15, page 13

ኢየሱስ ስለ ታማኝና ልባም ባሪያ የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን ማግኘት የጀመረው መቼ ነው? (ማቴ. 24:45-47)

ይህ ትንቢት መፈጸም የጀመረው በ33 ዓ.ም. በተከበረው የጴንጤቆስጤ ዕለት ሳይሆን ከ1914 በኋላ ነው። በ1919 ባሪያው በአገልጋዮቹ ላይ ተሹሟል፤ አገልጋዮቹ የተባሉት፣ ከሚቀርበው መንፈሳዊ ምግብ የሚመገቡት ክርስቲያኖች በሙሉ ናቸው።—7/15, pages 21-23

ኢየሱስ ታማኙን ባሪያ በንብረቱ ሁሉ ላይ የሚሾመው መቼ ነው?

ይህ የሚሆነው ወደፊት ማለትም ታማኙ ባሪያ በታላቁ መከራ ወቅት በሰማይ ሽልማቱን ሲቀበል ነው።—7/15, page 25

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ባለ ታሪኮች ስማቸው ያልተጠቀሰው መጥፎ ሰዎች ስለሆኑ ወይም ያን ያህል ቦታ ስላልተሰጣቸው ነው?

እንደዚያ ብለን መደምደም አንችልም። ስማቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተገለጸ ጥሩም መጥፎም ባለ ታሪኮች አሉ። (ሩት 4:1-3፤ ማቴ. 26:18) ከታማኝ መላእክት መካከልም ስማቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው የሁለቱ ብቻ ነው።—8/1, page 10

ከዛክሰንሃውዘን ማጎሪያ ካምፕ ተነስተው ረጅም ጉዞ ያደረጉት 230 የይሖዋ ምሥክሮች ከአምላክ ካገኙት ኃይል በተጨማሪ በሕይወት እንዲተርፉ የረዳቸው ምንድን ነው?

በረሃብና በበሽታ ዝለው የነበሩ ቢሆንም ጉዞውን መቀጠል እንዲችሉ ሁልጊዜ እርስ በርስ ይበረታቱ ነበር።—8/15, page 18

እስራኤላውያን ወደ ተስፋይቱ ምድር ለመግባት የዮርዳኖስን ወንዝ ስለ ማቋረጣቸው የሚናገረው ዘገባ የሚያበረታታን እንዴት ነው?

ወንዙ ጢም ብሎ ሞልቶ የነበረ ቢሆንም ይሖዋ ሕዝቦቹ እንዲሻገሩ ሲል ወንዙ መፍሰሱን እንዲያቆም አድርጓል። ይህም በእሱ ላይ ያላቸውን እምነት አጠናክሮላቸው እንደሚሆን እሙን ነው፤ ይህ ዘገባ እኛም በይሖዋ እንድንታመን ይረዳናል።—9/15, page 16

ቀለማት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተደጋጋሚ መጠቀሳቸው ምን ያሳያል?

መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ስለ ቀለማት የሚገልጹ ሐሳቦች፣ ቀለማት በሰዎች ስሜት ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩና ነገሮችን ለማስታወስ እንደሚረዱን አምላክ በሚገባ እንደሚያውቅ ይጠቁማሉ።—10/1, pages 14-15

በሚክያስ 5:5 ላይ ስለ አለቆችና ስለ እረኞች የተነገረው ትንቢት በዛሬው ጊዜ ፍጻሜውን እያገኘ ያለው እንዴት ነው?

በሚክያስ 5:5 ላይ የተጠቀሱት ‘ሰባት እረኞችና ስምንት አለቆች’ በጉባኤ ውስጥ የተሾሙ ሽማግሌዎችን እንደሚያመለክቱ እናውቃለን፤ እነዚህ ሽማግሌዎች፣ በአምላክ ሕዝቦች ላይ እንደሚሰነዘር በትንቢት የተነገረው ጥቃት ለሚመጣበት ወቅት የአምላክ ሕዝቦች ከወዲሁ እንዲጠናከሩ ይረዷቸዋል።—11/15, page 20

አምላክ ያስፈልገናል እንድንል የሚያደርጉ አንዳንድ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

ጥሩ መመሪያና በሕይወት ውስጥ ለሚነሱብን ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ያስፈልገናል፤ ሁለቱንም ነገሮች ማግኘት የምንችለው ደግሞ ከአምላክ ነው። ጥሩ ሕይወት እንድመራና ደስተኛ እንድንሆን ሊረዳን ፈቃደኛ ነው፤ በተጨማሪም እንዲህ ያለ ሕይወት እንዲኖረን ለማድረግ ሲል፣ በቃሉ ውስጥ የሰጣቸው ተስፋዎች እንዲፈጸሙ ያደርጋል።—12/1, pages 4-6