መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም የካቲት 2014

ይህ እትም በመዝሙር 45 ላይ የተጠቀሱትን አስደሳች ክንውኖች ይገልጻል። በተጨማሪም የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ ለሚሰጠን፣ ለሚጠብቀንና የቅርብ ወዳጃችን ለሆነው ይሖዋ አምላክ አድናቆታችንን ከፍ እንድናደርግ ይረዳናል።

ክብር የተጎናጸፈውን ንጉሥ ክርስቶስን አወድሱ!

መዝሙር 45 ላይ የተገለጹት አስደሳች ክንውኖች በዛሬው ጊዜ ለእኛ ምን ትርጉም አላቸው?

በበጉ ሠርግ ደስ ይበላችሁ!

የበጉ ሙሽራ ማን ናት? ክርስቶስ ሙሽራዋን ለሠርጉ ሲያዘጋጃት የቆየው እንዴት ነው? ሠርጉ በሚከናወንበት ጊዜ የደስታው ተካፋይ የሚሆኑት እነማን ናቸው?

በሰራፕታ የነበረችው መበለት ያሳየችው እምነት ክሷታል

የሰራፕታዋ መበለት ልጇ ከሞት መነሳቱ በሕይወቷ ውስጥ ከተፈጸሙ እምነቷን ካጠናከሩላት ነገሮች መካከል ዋነኛው ነው። ከእሷ ምን እንማራለን?

ይሖዋ—የሚያስፈልገንን የሚሰጠንና የሚጠብቀን አምላክ

በሰማይ ለሚኖረው አባታችን ለይሖዋ አምላክ ያለንን አድናቆት ከፍ እናድርግ። የሚያስፈልገንን ነገር ሁሉ ከሚሰጠንና ከሚጠብቀን አምላክ ጋር ያለንን ዝምድና እንዴት ማጠናከር እንደሚቻል እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

የቅርብ ወዳጃችን የሆነው ይሖዋ

የይሖዋ አምላክ የቅርብ ወዳጆች የነበሩትን የአብርሃምንና የጌዴዎንን ምሳሌ ተመልከት። የይሖዋ ወዳጅ ለመሆን የትኞቹን ብቃቶች ማሟላት ይኖርብናል?

የአንባቢያን ጥያቄዎች

በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይኖሩ የነበሩት አይሁዳውያን መሲሑን ‘እንዲጠባበቁ’ ምክንያት የሆኗቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?

‘ይሖዋ ደስ የሚያሰኝ መሆኑን በትኩረት ተመልከቱ’

የጥንቷ እስራኤል ንጉሥ የነበረው ዳዊት አምላክ በእውነተኛው አምልኮ ውስጥ ያደረገውን ዝግጅት ያደንቅ ነበር። እኛስ በዛሬው ጊዜ በእውነተኛው አምልኮ መደሰት የምንችለው እንዴት ነው?

ከታሪክ ማኅደራችን

አንድ መቶ ዓመት ያስቆጠረ የእምነት ገድል

በዚህ ዓመት፣ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ስለመሆኑ ጠንካራ እምነት እንዲኖራቸው ለመርዳት ሲባል የተዘጋጀው “የፍጥረት ፎቶ ድራማ” ለመጀመሪያ ጊዜ ለእይታ ከበቃ 100 ዓመት ይሞላዋል።