መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ነሐሴ 2014

ይህ እትም ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 26, 2014 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

‘በተገቢው ጊዜ ምግብ’ እያገኘህ ነው?

አንድ ሰው በመንፈሳዊ ጠንካራ ሆኖ መኖር ከፈለገ ታማኙ ባሪያ የሚያቀርባቸውን ትምህርቶች በሙሉ የግድ ማግኘት አለበት?

ሴቶች በይሖዋ ዓላማ ውስጥ ምን ሚና አላቸው?

በአምላክ ላይ የተነሳው ዓመፅ በወንዶችና በሴቶች ላይ ምን ውጤት አስከትሏል? በጥንት ዘመን የኖሩ አንዳንድ ታማኝ ሴቶችን ታሪክ አንብብ። በተጨማሪም ክርስቲያን ሴቶች በዛሬው ጊዜ የአምላክን ሥራ እያከናወኑ ያሉት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የአምላክ ቃል ሕያው ነው—ተጠቀሙበት!

ሁሉም የይሖዋ ምሥክሮች በአገልግሎታቸው ውጤታማ መሆን ይፈልጋሉ። ከሰዎች ጋር ውይይት ስንጀምር በትራክቶቻችን ታግዘን ኃይለኛ የሆነውን የአምላክ ቃል መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው?

ይሖዋ ወደ እኛ የሚቀርበው እንዴት ነው?

ከይሖዋ ጋር የቀረበ ዝምድና መመሥረት ያስፈልገናል። የቤዛው ዝግጅትና መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋ ወደ እሱ እንድንቀርብ እንደሚፈልግ የሚያረጋግጡት እንዴት እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

የትም ብትሆን የይሖዋን ድምፅ ስማ

የይሖዋን ድምፅ ማዳመጥና ከእሱ ጋር የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ይህ ርዕስ ሰይጣንና በውስጣችን ያለው የኃጢአት ዝንባሌ ይሖዋን እንዳናዳምጥ የሚያደርጉብንን ተጽዕኖ እንዴት ማሸነፍ እንደምንችል ያብራራል።

‘ተመልሰህ ወንድሞችህን አበርታ’

ከዚህ በፊት በሽምግልና ሲያገለግል የነበረ አንድ ወንድም እንደገና ‘የበላይ ተመልካች ለመሆን ጥረት’ ማድረግ ይችላል?

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ኢየሱስ ትንሣኤ የሚያገኙ ሰዎች “አያገቡም እንዲሁም አይዳሩም” በማለት ሲናገር ስለ ምድራዊው ትንሣኤ እየገለጸ ነበር?

ከታሪክ ማኅደራችን

“ዩሬካ ድራማ” ብዙዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት እንዲያገኙ ረድቷል

አጠር ባለ መንገድ የተዘጋጀው “ዩሬካ ድራማ” ርቀው በሚገኙ አካባቢዎች ሌላው ቀርቶ ኤሌክትሪክ በሌለባቸው ቦታዎች እንኳ ሊታይ የሚችል ነበር።