መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም መስከረም 2014

ይህ እትም ከጥቅምት 27 እስከ ኅዳር 30, 2014 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

‘ለመልካም ሥራ እየተጣጣርክ’ ነው?

ይህን ማድረግ የምትችልበት ትክክለኛው አካሄድ ምንድን ነው?

እውነትን እንዳገኘህ እርግጠኛ ነህ? ለምን?

ይህ ርዕስ ብዙ ሰዎች፣ የይሖዋ ምሥክሮች እውነትን እንደያዙ እርግጠኛ የሆኑበትን ምክንያት ያብራራል። የይሖዋ ምሥክሮች ራሳቸው እውነትን መያዛቸውን እርግጠኞች የሆኑበትን ምክንያትም ያብራራል።

“ብዙ መከራ” ቢኖርም አምላክን በታማኝነት አገልግሉ

በሰይጣን ዓለም ውስጥ ስለምንኖር ሁላችንም መከራ ያጋጥመናል። ሰይጣን እኛን ለማጥቃት ከሚጠቀምባቸው ዘዴዎች አንዳንዶቹ የትኞቹ ናቸው? ለእነዚህ መከራዎች መዘጋጀት የምንችለውስ እንዴት ነው?

ወላጆች—ልጆቻችሁን እንደ እረኛ ተንከባከቧቸው

ወላጆች ልጆቻቸውን “በይሖዋ ተግሣጽ እንዲሁም የእሱን አስተሳሰብ በውስጣቸው በመቅረጽ” የማሳደግ ኃላፊነት አለባቸው። (ኤፌሶን 6:4) ይህ ርዕስ ወላጆች እንደ እረኛ ልጆቻቸውን መንከባከብ እና ይሖዋን እንዲወድዱ መርዳት የሚችሉባቸውን ሦስት መንገዶች ያጎላል።

የአንባቢያን ጥያቄዎች

መዝሙር 37:25 እና በማቴዎስ 6:33 ይሖዋ ክርስቲያኖች እንዲራቡ ፈጽሞ የማይፈቅድ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው?

የመጨረሻው ጠላት የሆነው ሞት ይደመሰሳል

ሞትና ለሞት የሚያደርሱ ነገሮች በሙሉ በሰው ልጆች ላይ ከፍተኛ ሥቃይ አስከትለዋል። ሰዎች የሚሞቱት ለምንድን ነው? ‘የመጨረሻው ጠላት የሆነው ሞት የሚደመሰሰው’ እንዴት ነው? (1 ቆሮንቶስ 15:26) ለእነዚህ ጥያቄዎች የተሰጡት መልሶች የይሖዋን ፍትሕ፣ ጥበብና በተለይ ደግሞ ፍቅሩን ጎላ አድርጎ የሚያሳዩት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

በሙሉ ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ያሉትን አስቧቸው

በርካታ የይሖዋ አገልጋዮች በሙሉ ጊዜ አገልግሎት በትጋት ይካፈላሉ። እነዚህ ክርስቲያኖች የሚያከናውኑትን “የእምነት ሥራ” እና ‘ከፍቅር የመነጨ ድካም’ እንደምናስብ ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?—1 ተሰሎንቄ 1:3