መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ኅዳር 2014

ይህ እትም ከታኅሣሥ 29, 2014 እስከ የካቲት 1, 2015 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

የኢየሱስ ትንሣኤ ለእኛ ምን ትርጉም አለው?

ኢየሱስ ትንሣኤ እንዳገኘ የሚያረጋግጡ አራት ምክንያቶች እነሆ። ኢየሱስ ሕያው መሆኑን ማወቃችን በእኛ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል?

ቅዱስ መሆን ያለብን ለምንድን ነው?

የዘሌዋውያንን መጽሐፍ ማንበብ ግራ አጋብቶህ ወይም አሰልችቶህ ያውቃል? በዘሌዋውያን መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙት መንፈሳዊ ዕንቁዎች ለይሖዋ በምታቀርበው አምልኮ ረገድ ቅድስናህን ለመጠበቅ ይረዱሃል።

በምግባራችን ሁሉ ቅዱስ መሆን አለብን

አቋማችንን እንዳላላ፣ ለይሖዋ ምርጣችን እንድንሰጥና ጠንካራ መንፈሳዊ ምግብ እንድንመገብ የሚያነሳሳን ምንድን ነው?

“አምላኩ ይሖዋ የሆነለት ሕዝብ”

አምላክ በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ የሚገኙ በቅን ልብ እሱን የሚያመልኩ ሰዎችን ይቀበላል?

‘አሁን የአምላክ ሕዝብ ናችሁ’

“የአምላክ ሕዝብ” መሆንና ይህን መብት ይዘን መቀጠል የምንችለው እንዴት ነው?

የአንባቢያን ጥያቄዎች

በጉባኤ ውስጥ ሽማግሌዎችና አገልጋዮች የሚሾሙት እንዴት ነው? በራእይ ምዕራፍ 11 ላይ የተጠቀሱት ሁለት ምሥክሮች እነማን ናቸው?

ከታሪክ ማኅደራችን

በፀሐይ መውጫዋ ምድር ጎሕ ቀደደ

“ኢዩዎች” የተባሉ ልዩ ተሽከርካሪዎች በጃፓን የመንግሥቱን ስብከት ሥራ ለማስፋፋት አገልግለዋል።