መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም የካቲት 2015
ይህ እትም ከሚያዝያ 6 እስከ ግንቦት 3, 2015 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።
ያልተጠበቀ ስጦታ ለጃፓናውያን
“መጽሐፍ ቅዱስ—የማቴዎስ ወንጌል” የተባለ አዲስ ጽሑፍ በጃፓን ወጣ። ይህ መጽሐፍ ምን ገጽታዎች አሉት? የተዘጋጀበት ዓላማ ምንድን ነው?
ኢየሱስን በትሕትናውና በርኅራኄው ምሰሉት
1 ጴጥሮስ 2:21 የኢየሱስን ፈለግ በጥብቅ እንድንከተል ያሳስበናል። ፍጽምና የጎደለን ብንሆንም ኢየሱስን በትሕትናውና በርኅራኄው መምሰል የምንችለው እንዴት ነው?
ኢየሱስን በድፍረቱና በአስተዋይነቱ ምሰሉት
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ዘገባ ኢየሱስ ምን ዓይነት ሰው እንደነበረ ለማወቅ ያስችለናል። የኢየሱስን ድፍረትና አስተዋይነቱን በመምሰል ረገድ ፈለጉን በጥብቅ መከተል የምንችለው እንዴት እንደሆነ መርምር።
ለአገልግሎት ያላችሁ ቅንዓት እንዳይቀዘቅዝ ጥረት አድርጉ
በዛሬው ጊዜ በምድር ላይ ካሉት ሥራዎች ሁሉ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ሥራ ምሥራቹን መስበክ እንደሆነ እናውቃለን። ለክርስቲያናዊው አገልግሎት ያለን ቅንዓት እንዳይቀዘቅዝ ማድረግ አልፎ ተርፎም ማሳደግ የምንችለው እንዴት ነው?
‘የይሖዋን ትምህርት’ እንዲቀበሉ ብሔራትን ማዘጋጀት
የጥንቶቹ ክርስቲያኖች ምሥራቹን በመስበክ ረገድ ምን ያህል ተሳክቶላቸው ነበር? በታሪክ ውስጥ ከሌላ ከየትኛውም ዘመን ይልቅ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ምሥራቹን መስበክ ቀላል እንዲሆን ያደረጉት የትኞቹ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ?
ይሖዋ ዓለም አቀፉን የማስተማር ሥራችንን ይመራል
የይሖዋ አገልጋዮች ምሥራቹን በምድር ዙሪያ በመስበክ ረገድ እንዲሳካላቸው አስተዋጽኦ ያደረጉ በቅርቡ የተከናወኑ ምን ነገሮች አሉ?
የአንባቢያን ጥያቄዎች
የሽቶ መዓዛ የሚረብሻቸው ወንድሞችና እህቶች እንዳይቸገሩ ለመርዳት ምን ማድረግ ይቻላል? አንዲት እህት ራሷን መሸፈን የሚያስፈልጋት መቼ ነው?
ከታሪክ ማኅደራችን
“እጅግ ክቡር ወቅት”
የጽዮን መጠበቂያ ግንብ የክርስቶስ ሞት መታሰቢያ በዓል የሚከበርበትን ወቅት ‘እጅግ ክቡር ወቅት በማለት የጠራው ሲሆን አንባቢዎቹ በዓሉን እንዲያከብሩ አበረታቷል።በቀድሞዎቹ ዘመናት የመታሰቢያው በዓል የሚከበረው እንዴት ነበር?