መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ሚያዝያ 2015

ይህ እትም ከሰኔ 1 እስከ 28, 2015 የሚጠኑ የጥናት ርዕሶችን ይዟል።

ሽማግሌዎች፣ ሌሎችን ስለማሠልጠን ምን አመለካከት አላችሁ?

ሌሎችን በማሠልጠን ረገድ የተዋጣላቸው ሽማግሌዎች የሰጧቸውን ሰባት ሐሳቦች ተመልከት።

ሽማግሌዎች ሌሎች ብቃቱን እንዲያሟሉ ማሠልጠን የሚችሉት እንዴት ነው?

ሽማግሌዎች ሌሎችን ሲያሠለጥኑ ኢየሱስን መምሰል ይችላሉ፤ ተማሪዎች ደግሞ የኤልሳዕን ምሳሌ መከተል ይችላሉ።

የሕይወት ታሪክ

“አመቺ በሆነ ጊዜም ሆነ በአስቸጋሪ ጊዜ” ያገኘናቸው በረከቶች

ትሮፊም ንሶምባ በማላዊ በእምነታቸው ምክንያት የደረሰባቸውን ከባድ ስደት ተቋቁመዋል፤ የሕይወት ታሪካቸውን ማንበብህ በታማኝነት እንድትጸና ይረዳሃል።

ከይሖዋ ጋር ያለህ ወዳጅነት ምን ያህል ጠንካራ ነው?

የሐሳብ ልውውጥ ወዳጅነትን ያጠናክራል። ታዲያ ይህን በማድረግ ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና ማጠናከር የምትችለው እንዴት ነው?

ምንጊዜም በይሖዋ ታመኑ!

ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት በማጠናከር ረገድ ሊያጋጥሙህ ከሚችሉ ተፈታታኝ ሁኔታዎች መካከል አንዱን እንዴት በተሳካ ሁኔታ መወጣት እንደምትችል አንብብ።

ውገዳ ፍቅራዊ ዝግጅት ነው ሊባል የሚችለው እንዴት ነው?

ውገዳ ከፍተኛ ስሜታዊ ሥቃይ የሚፈጥር ሆኖ ሳለ ለሁሉም ጥቅም ያስገኛል የሚባለው ለምንድን ነው?

ዛፍ ቢቆረጥ መልሶ ሊያቆጠቁጥ ይችላል?

የዚህ ጥያቄ መልስ ወደፊት ከምናገኘው ተስፋ ጋር የተያያዘ ነው።