በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዛፍ ቢቆረጥ መልሶ ሊያቆጠቁጥ ይችላል?

ዛፍ ቢቆረጥ መልሶ ሊያቆጠቁጥ ይችላል?

በሊባኖስ ከሚገኘውና ግርማ ሞገስ ካለው አርዘ ሊባኖስ ጋር ሲወዳደር ጉጥ የበዛበትና ጥምም ያለው የወይራ ዛፍ ያን ያህል ላይማርክ ይችላል። ይሁን እንጂ የወይራ ዛፍ አስቸጋሪ የአየር ሁኔታን የመቋቋም አስደናቂ ችሎታ አለው። አንዳንድ የወይራ ዛፎች የ1,000 ዓመት ዕድሜ እንዳላቸው ይገመታል። የወይራ ዛፍ ሥሩን በስፋት ስለሚዘረጋ ግንዱ ቢደርቅም እንኳ ዛፉ ሊያንሠራራ ይችላል። ሥሮቹ እስካልሞቱ ድረስ ዛፉ እንደገና ያቆጠቁጣል።

ኢዮብ፣ ቢሞትም እንኳ ዳግመኛ በሕይወት ሊኖር እንደሚችል እርግጠኛ ነበር። (ኢዮብ 14:13-15) ኢዮብ፣ አምላክ ከሞት እንደሚያስነሳው ያለውን እምነት ለመግለጽ ዛፍ ምናልባትም የወይራ ዛፍ እንደ ምሳሌ ተጠቅሟል። “ዛፍ እንኳ ተስፋ አለውና። ቢቆረጥ መልሶ ያቆጠቁጣል” በማለት ተናግሯል። ከከባድ ድርቅ በኋላ ዝናብ ሲጥል፣ ደርቆ የነበረ የወይራ ዛፍ ጉቶ እንደገና ሊያንሰራራ ይችላል፤ ከዛፉ ሥሮች ላይ ቀንበጥ ማቆጥቆጥ ስለሚጀምር ዛፉ “እንደ አዲስ [ተክል] ቅርንጫፎች ያወጣል።”—ኢዮብ 14:7-9

አንድ ገበሬ፣ የተቆረጠ የወይራ ዛፍ ሥሮች እንደገና ሲያቆጠቁጡ ለማየት እንደሚጓጓ ሁሉ ይሖዋ አምላክም በሞት ላንቀላፉ አገልጋዮቹም ሆነ ለሌሎች ብዙዎች እንደገና ሕይወት ለመስጠት ይጓጓል። (ማቴ. 22:31, 32፤ ዮሐ. 5:28, 29፤ ሥራ 24:15) ሙታን ሲነሱ መቀበልና እንደ ቀድሟቸው ዓይነት ሕይወት ሲመሩ ማየት ምንኛ አስደሳች ይሆናል!