በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጋቢት 13, 2000—ሊታወስ የሚገባው ዕለት

መጋቢት 13, 2000—ሊታወስ የሚገባው ዕለት

መጋቢት 13, 2000—ሊታወስ የሚገባው ዕለት

ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ዋዜማ ምሽት ላይ ለሐዋርያቱ እርሾ ያልገባበት ቂጣና ቀይ የወይን ጠጅ ከሰጣቸው በኋላ እንዲበሉና እንዲጠጡ አዘዛቸው። ከዚያም “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አላቸው።—ሉቃስ 22:19

በዚህ ዓመት የዚህ ክንውን መታሰቢያ፣ ቅዳሜ መጋቢት 13, 2000 (March 22, 2008) ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይከበራል። በዚህ ልዩ ምሽት በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ እሱ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ለማክበር አንድ ላይ ይሰበሰባሉ። እርስዎም አብረውን ተገኝተው ዝግጅቱን እንዲከታተሉ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል። ስብሰባው የሚደረግበትን ቦታና ሰዓት ለማወቅ እባክዎ በአቅራቢያዎ የሚገኙትን የይሖዋ ምሥክሮች ይጠይቁ።