የሰውን ዘር ለመግዛት ብቃት ያለው ማን ነው?
ልዩ የሕዝብ ንግግር
የሰውን ዘር ለመግዛት ብቃት ያለው ማን ነው?
የትኛው መሪ ነው . . .
• የኢኮኖሚ ችግርን ማስወገድ እንዲሁም ለሰዎች ሁሉ በቂ ምግብና ጥሩ ቤት መስጠት የሚችለው?
• የሰው ልጆች እንደ ሱናሚ፣ አውሎ ነፋስና የመሬት መንቀጥቀጥ ባሉ አደጋዎች እንዳይጎዱ የተፈጥሮ አደጋዎችን ማስቀረት የሚችለው?
• በሽታን ፈጽሞ ማስወገድ እንዲሁም ሰዎችን ወደ ወጣትነት መመለስ የሚችለው?
• ሁሉንም ዓይነት ጦርነቶች ማስቀረትና ለተገዥዎቹ ሰላምና ደኅንነት ማምጣት የሚችለው?
• የምድር ሥነ ምህዳር ሚዛኑን የጠበቀ እንዲሆን ማድረግና ምድርን ወደ ገነትነት መለወጥ የሚችለው?
እነዚህን ሁሉ በረከቶች ማምጣት የሚችለው አንድ መሪ ብቻ ነው። ታዲያ ይህ መሪ ማን ነው? ይህ ጥያቄ “የሰውን ዘር ለመግዛት ብቃት ያለው ማን ነው?” በሚል ርዕስ በሚቀርበው የሕዝብ ንግግር ላይ መልስ ያገኛል። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተው ይህ ንግግር በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ከ230 በሚበልጡ አገሮች ውስጥ ይቀርባል። በበርካታ ቦታዎች ላይ ንግግሩ እሁድ ሚያዝያ 6, 2008፣ በይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ይቀርባል። በአካባቢዎ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ንግግሩ የሚቀርብበትን ቦታና ሰዓት ሊነግሩዎት ፈቃደኞች ናቸው። በዚህ ንግግር ላይ እንዲገኙ ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልዎታለን።