ስለ አምላክ መንግሥት
ከኢየሱስ ምን እንማራለን?
ስለ አምላክ መንግሥት
የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
የአምላክ መንግሥት መላውን ምድር የሚገዛ መስተዳድር ነው። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል:- “እናንተ ግን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤ . . . ‘መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች፣ እንዲሁ በምድር ትሁን።’”—ማቴዎስ 6:9, 10፤ ዳንኤል 2:44
የአምላክ መንግሥት ገዥዎች የሚሆኑት እነማን ናቸው?
ኢየሱስ የተወለደው የአምላክ መንግሥት ገዥ እንዲሆን ነው። አንድ መልአክ ለኢየሱስ እናት “ጌታ አምላክ የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ . . . ለዘላለም ይነግሣል” በማለት ነግሯት ነበር። (ሉቃስ 1:30-33) ከዚህ በተጨማሪም ኢየሱስ፣ ከተከታዮቹ መካከል የተወሰኑት ከእሱ ጋር እንዲገዙ መርጧል። ሐዋርያቱን እንዲህ ብሏቸዋል:- “እናንተም ሳትለዩኝ በመከራዬ ጊዜ በአጠገቤ የቆማችሁ ናችሁ፤ አባቴ እኔን እንደ ሾመኝ እኔም ደግሞ በመንግሥቴ እሾማችኋለሁ።” (ሉቃስ 22:28, 29፤ ዳንኤል 7:27) በአጠቃላይ 144,000 የሚሆኑ የኢየሱስ ተከታዮች አብረውት ይገዛሉ።—ራእይ 5:9, 10፤ 14:1
መንግሥቱ የሚገዛው የት ሆኖ ነው?
የአምላክ መንግሥት የሚገዛው ከሰማይ ሆኖ ነው። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ብሏቸዋል:- “[ወደ ሰማይ] የምሄደውም ስፍራ ላዘጋጅላችሁ ነው። ሄጄም ስፍራ ካዘጋጀሁላችሁ በኋላ፣ እኔ ባለሁበት እናንተም ከእኔ ጋር እንድትሆኑ ልወስዳችሁ ዳግመኛ እመጣለሁ። . . . ወደ አብ [እሄዳለሁ።]”—ዮሐንስ 14:2, 3, 12፤ ዳንኤል 7:13, 14
የአምላክ መንግሥት ክፋትን ምን ያደርጋል?
ኢየሱስ ክፉ ሰዎችን ከምድር ላይ የሚያጠፋ ሲሆን እንደሚከተለው ሲል ተናግሮ ነበር:- “የሰው ልጅ [ኢየሱስ] ከመላእክቱ ማቴዎስ 25:31-34, 46
ሁሉ ጋር በክብሩ ሲመጣ፣ በክብሩ ዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ . . . ሕዝቡን አንዱን ከሌላው ይለያል፤ . . . ‘[ክፉዎች] ወደ ዘላለም ፍርድ፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።’”—የመንግሥቱ ተገዥዎች በመሆን በምድር ላይ የሚኖሩት እነማን ናቸው?
ኢየሱስ “የዋሆች ብፁዓን ናቸው፤ ምድርን ይወርሳሉና” ብሏል። (ማቴዎስ 5:5፤ መዝሙር 37:29፤ 72:8) ወደፊት ምድር እርስ በርስ በሚዋደዱ ሰዎች ትሞላለች። ኢየሱስ ለተከታዮቹ እንዲህ ብሏቸዋል:- “አዲስ ትእዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ ይኸውም እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ነው፤ እንግዲህ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ። እርስ በርሳችሁ ብትዋደዱ፣ ሰዎች ሁሉ የእኔ ደቀ መዛሙርት እንደ ሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ።”—ዮሐንስ 13:34, 35
የአምላክ መንግሥት በምድር ላይ ላሉ የሰው ዘሮች ምን ያደርግላቸዋል?
ኢየሱስ የሰው ልጆችን ከማንኛውም በሽታ ይፈውሳል። ምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ለሕዝቡ ‘ስለ አምላክ መንግሥት የነገራቸው ሲሆን ፈውስ የሚያስፈልጋቸውንም ፈውሷቸው ነበር።’ (ሉቃስ 9:11) ሐዋርያው ዮሐንስ ከሞት የተነሳውን ኢየሱስን በራእይ ከተመለከተ በኋላ እንዲህ ብሏል:- “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ፤ . . . ደግሞም እንዲህ የሚል ታላቅ ድምፅ ከዙፋኑ ሲወጣ ሰማሁ፤ ‘እነሆ፤ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሰዎች መካከል ነው፤ . . . እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት [አይኖርም]።’”—ራእይ 21:1-4
የአምላክ መንግሥት ምድርን ገነት ያደርጋል። ከኢየሱስ ጋር ተሰቅሎ የነበረው ወንጀለኛ “ኢየሱስ ሆይ፤ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ” በማለት የጠየቀው ሲሆን ኢየሱስም “እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ” ብሎታል።—ሉቃስ 23:42, 43፤ ኢሳይያስ 11:4-9
ለተጨማሪ ማብራሪያ ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? * የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 8 ተመልከት።
[የግርጌ ማስታወሻ]
^ አን.16 በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ።