በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ኢየሱስ ተአምራዊ ፈውሶችን አከናውኗል

ኢየሱስ ተአምራዊ ፈውሶችን አከናውኗል

ለወጣት አንባቢያን

ኢየሱስ ተአምራዊ ፈውሶችን አከናውኗል

መመሪያ:- ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳልና በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማት ሞክር። ታሪኮቹ ሕያው እንዲሆኑልህ አድርግ።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።ማቴዎስ 15:21-28ን አንብብ።

እናትየው ምን ተሰምቷት እንደነበር መገመት ትችላለህ?

․․․․․

ከዚህ በታች ባሉት ቁጥሮች ላይ ኢየሱስ የተናገረው እንዴት ባለ የድምፅ ቃና ይመስልሃል?

24 ․․․․․ 26 ․․․․․ 28 ․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ኢየሱስ፣ የሴትየዋን ልጅ እንደማይፈውስላት በንግግሩም ሆነ በተግባሩ የገለጸው ምን ያህል ጊዜ ነበር?

․․․․․

ኢየሱስ መጀመሪያ ላይ ልጅቷን ያልፈወሳት ለምን ነበር?

․․․․․

ታዲያ ኢየሱስ ልጅቷን በኋላ ላይ የፈወሳት ለምንድን ነው?

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ:-

ኢየሱስ ምክንያታዊ ስለመሆኑ።

․․․․․

ከሌሎች ጋር ባለህ ግንኙነት ረገድ ይህን ባሕርይ ማንጸባረቅ ስለምትችልበት መንገድ።

․․․․․

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።ማርቆስ 8:22-25ን አንብብ።

በሰፈሩ ውስጥና ከሰፈሩ ውጭ ምን ይታይሃል? በአካባቢውስ ምን ድምፅ ይሰማሃል?

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

․․․․․

ኢየሱስ፣ ሰውየውን ከመፈወሱ በፊት ከሰፈሩ ውጭ ይዞት የወጣው ለምን ይመስልሃል?

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ:-

ኢየሱስ የአካል ጉዳተኛ ባይሆንም እንዲህ ላሉ ሰዎች ስለነበረው ርኅራኄ።

․․․․․

በእነዚህ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ውስጥ ከተገለጹት ሁኔታዎች መካከል አንተን ይበልጥ የነካህ የትኛው ነው? ለምንስ?

․․․․․