በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የምንኖረው በዓይነቱ ልዩ በሆነ ዘመን ውስጥ ነው

የምንኖረው በዓይነቱ ልዩ በሆነ ዘመን ውስጥ ነው

የምንኖረው በዓይነቱ ልዩ በሆነ ዘመን ውስጥ ነው

መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሰው ልጆች “ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን” እንደሚያጋጥማቸው አስቀድሞ ተናግሯል። ይህንን ጊዜ ‘የመጨረሻው ዘመን’ በማለት ይጠራዋል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5 NW፤ 2 ጴጥሮስ 3:3-7) ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ስለ ‘ዓለም መጨረሻ’ በጠየቁት ወቅት ስለዚህ ዘመን ተናግሯል። (ማቴዎስ 24:3) በእርግጥ የምንኖረው በመጨረሻው ዘመን ውስጥ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውንና ከታች ያሉትን በቅርብ ጊዜ የወጡ ሪፖርቶች በማነጻጸር ለዚህ ጥያቄ መልሱን ስጥ።

መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጦርነት እንደሚኖር ተንብዮአል—ሉቃስ 21:10፤ ራእይ 6:4

በቅርብ ጊዜ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚከተለው ይላሉ:- “በ20ኛው መቶ ዘመን ከጦርነት ጋር በተያያዘ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ከክርስቶስ ልደት ወዲህ ባሉት 1,900 ዓመታት ውስጥ በተደረጉት ጦርነቶች ሕይወታቸውን ካጡት ሰዎች ቁጥር ጋር ሲወዳደር በሦስት እጥፍ ይበልጣል።”—ዎርልድዎች ኢንስቲትዩት

መጽሐፍ ቅዱስ የምግብ እጥረትና በሽታ እንደሚኖር ተንብዮአል—ሉቃስ 21:11፤ ራእይ 6:5-8

በቅርብ ጊዜ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚከተለው ይላሉ:- በ2004 በምድር ዙሪያ 863 ሚሊዮን የሚያህሉ ሰዎች በምግብ እጥረትና በተመጣጠነ ምግብ እጦት እንደሚሠቃዩ ተዘግቧል። ይህ ቁጥር በ2003 ከነበረው በ7 ሚሊዮን ይበልጣል።—የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት

አንድ ቢሊዮን የሚያህሉ ሰዎች በደሳሳ መንደሮች፣ 2.6 ቢሊዮን የሚሆኑ ደግሞ መሠረታዊ የሆነ የፍሳሽና የቆሻሻ ማስወገጃ በሌላቸው ሰፈሮች ውስጥ ይኖራሉ፤ 1.1 ቢሊዮን የሚያህሉ ሰዎች ንጹሕ የመጠጥ ውኃ አያገኙም።—ዎርልድዎች ኢንስቲትዩት

የወባ በሽታ 500 ሚሊዮን ሰዎችን አጥቅቷል፤ 40 ሚሊዮን ሰዎች ደግሞ ከኤች አይ ቪ ኤድስ ጋር ይኖራሉ፤ በ2005 በሳንባ ነቀርሳ በሽታ 1.6 ሚሊዮን ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።—የዓለም የጤና ድርጅት

መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ምድርን እንደሚያበላሿት ተንብዮአል—ራእይ 11:18

በቅርብ ጊዜ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚከተለው ይላሉ:- “የሰው ልጅ በተፈጥሮ ላይ በሚያደርሰው ጉዳት ሳቢያ በርካታ የእንስሳትና የዕፅዋት ዝርያዎች በቅርቡ ከምድር ገጽ መጥፋታቸው አይቀርም።” “በተፈጥሮ ከምናገኛቸው ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች ውስጥ ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት እያሽቆለቆሉ ነው።”—ሚሊኒየም ኢኮሲስተም አሴስመንት

“የአካባቢን ሙቀት የሚጨምሩ ሰው ሠራሽ ጋዞች የምድርን የአየር ንብረት በእጅጉ ያዛቡት ሲሆን ፕላኔታችንንም ስጋት ላይ ጥለዋታል።”—ናሳ፣ ጎዳርድ ኢንስቲትዩት ፎር ስፔስ ስተዲስ

መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ መንግሥት ምሥራች በመላው ምድር እንደሚሰበክ ተንብዮአል—ማቴዎስ 24:14፤ ራእይ 14:6, 7

በቅርብ ጊዜ የወጡ ሪፖርቶች እንደሚከተለው ይላሉ:- በ236 አገሮች ውስጥ የሚኖሩ 6,957,854 የሚሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች በ2007 ስለ አምላክ መንግሥት ምሥራች ለሰዎች በመስበክ ከ1.4 ቢሊዮን በላይ ሰዓታትን አሳልፈዋል።—የ2008 የይሖዋ ምሥክሮች የዓመት መጽሐፍ

ቀደም ሲል እንደተመለከትነው የተለያዩ አሳዛኝ ሁኔታዎች ቢኖሩም መጽሐፍ ቅዱስ አዎንታዊ አመለካከት ለመያዝ የሚያስችል ምክንያት ይሰጠናል። ኢየሱስ ስለ አምላክ መንግሥት “ወንጌል” ወይም ምሥራች ተናግሯል። ይሁንና የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? የሰው ልጆች ወደፊት የተሻለ ሕይወት ከማግኘታቸው ጋር የተያያዘውስ እንዴት ነው? የአምላክ መንግሥት ለአንተ ምን ትርጉም አለው?

[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]

መጽሐፍ ቅዱስ በዛሬው ጊዜ በዓለም ላይ ስለምናያቸው ሁኔታዎች አስቀድሞ ተናግሯል