በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ውዳሴ የሚገባው ፈጣሪ

ውዳሴ የሚገባው ፈጣሪ

ወደ አምላክ ቅረብ

ውዳሴ የሚገባው ፈጣሪ

ራእይ 4:11

‘የሕይወት ዓላማ ምንድን ነው’ ብለህ ጠይቀህ ታውቃለህ? ሕይወት የተገኘው በዝግመተ ለውጥ ነው ብለው የሚያምኑ ሰዎች ለዚህ ጥያቄ መልስ ማግኘት አይችሉም። የሕይወት ምንጭ ይሖዋ አምላክ እንደሆነ የሚገልጸውን ለዘመናት የኖረ እውነት ለሚቀበሉ ሰዎች ግን ሁኔታው ከዚህ የተለየ ነው። (መዝሙር 36:9) እነዚህ ሰዎች አምላክ የፈጠረን በዓላማ እንደሆነ ያውቃሉ። ይህ የአምላክ ዓላማ በራእይ 4:11 ላይ ተገልጿል። ሐዋርያው ዮሐንስ በዚህ ጥቅስ ላይ ያሰፈረው ሐሳብ የተፈጠርንበትን ምክንያት በተመለከተ ምን እንደሚል እንመልከት።

ዮሐንስ፣ በሰማይ የሚገኝ አንድ የመዘምራን ቡድን አምላክን እንደሚከተለው በማለት እንዳወደሰ ጽፏል፦ “ጌታችንና አምላካችን ሆይ፤ ክብርና ሞገስ፣ ኀይልም ልትቀበል ይገባሃል፤ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና፤ በፈቃድህም ተፈጥረዋልና፤ ሆነዋልምና።” እንዲህ ያለ ክብር የሚገባው ይሖዋ ብቻ ነው። ለምን? ምክንያቱም እሱ ‘ሁሉን ፈጥሯል።’ ታዲያ የማሰብ ችሎታ ያላቸው ፍጥረታቱ ይህን ማወቃቸው ምን እንዲያደርጉ ሊያነሳሳቸው ይገባል?

ይሖዋ ክብር፣ ሞገስና ኀይል ‘ሊቀበል’ የሚገባው አምላክ እንደሆነ ተገልጿል። በአጽናፈ ዓለም ውስጥ የይሖዋን ያህል ክብርና ሞገስ ያለው እንዲሁም ኃያል የሆነ አካል እንደሌለ ግልጽ ነው። ይሁንና አብዛኛው የሰው ዘር አምላክ የሁሉ ነገር ፈጣሪ መሆኑን አምኖ አይቀበልም። ያም ቢሆን የአምላክን ‘የማይታይ ባሕርይ’ ከፈጠራቸው ነገሮች በግልጽ የሚያስተውሉ ሰዎች አሉ። (ሮሜ 1:20) እነዚህ ሰዎች ልባቸው በአድናቆት ስለሚሞላ ለይሖዋ ክብርና ሞገስ ለመስጠት ይገፋፋሉ። ሁሉንም ነገሮች ድንቅ አድርጎ የሠራው ይሖዋ እንደሆነ የሚያሳዩትንና በዚህም ምክንያት ጥልቅ አክብሮት የሚገባው አምላክ መሆኑን የሚገልጹትን አስደናቂ ማስረጃዎች፣ ለመስማት ፈቃደኛ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ ያውጃሉ።—መዝሙር 19:1, 2፤ 139:14

ይሁን እንጂ ይሖዋ ከአምላኪዎቹ ኃይል ሊቀበል የሚችለው እንዴት ነው? እርግጥ ነው፣ ሁሉን ቻይ ለሆነው ፈጣሪ ኃይል ሊሰጠው የሚችል አንድም ፍጡር የለም። (ኢሳይያስ 40:25, 26) ሆኖም በአምላክ አምሳል የተፈጠርን እንደመሆናችን የእሱን ባሕርያት በተወሰነ መጠን የማንጸባረቅ ችሎታ አለን፤ ከእነዚህ ባሕርያት አንዱ ደግሞ ኃይል ነው። (ዘፍጥረት 1:27) ፈጣሪያችን ላደረገልን ነገር ልባዊ አድናቆት ካለን ኃይላችንንና ጉልበታችንን በመጠቀም እሱን ለማክበርና ከፍ ከፍ ለማድረግ መገፋፋታችን አይቀርም። ጉልበታችንን የራሳችንን ፍላጎት ለማሟላት ብቻ ከማዋል ይልቅ ይሖዋ አምላክን በማገልገል ሙሉ ኃይላችንን ለእሱ ልንሰጠው እንደሚገባ ይሰማናል።—ማርቆስ 12:30

ታዲያ የተፈጠርነው ለምንድን ነው? በራእይ 4:11 ላይ የሚገኘው የመጨረሻ ሐሳብ መልስ ሲሰጥ “በፈቃድህም [ሁሉም ነገሮች] ተፈጥረዋልና፤ ሆነዋልምና” ይላል። የተፈጠርነው በእኛ ፈቃድ ሳይሆን በአምላክ ፈቃድ ነው። በዚህም ምክንያት አንድ ሰው የራሱን ፍላጎት ለማሟላት ብቻ የሚኖር ከሆነ ሕይወቱ ባዶና ትርጉም የለሽ ይሆናል። ስለዚህ የአእምሮ ሰላም፣ ደስታና እርካታ ለማግኘት እንዲሁም ስኬታማ ለመሆን የአምላክን ፈቃድ መማርና ከተማርነው ነገር ጋር ተስማምተን መኖር ያስፈልገናል። የተፈጠርንበትንና የሕይወታችንን ዓላማ መረዳት የምንችለው እንዲህ ስናደርግ ብቻ ነው።—መዝሙር 40:8

[በገጽ 31 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

NASA, ESA, and A. Nota (STScI)