በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ዕለት

በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ዕለት

በታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ዕለት

ይህ ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተበት ዕለት ነው። የኢየሱስ ሞት ትልቅ ግምት የሚሰጠው ለምንድን ነው? ይህ የሆነው በበርካታ ምክንያቶች የተነሳ ነው።

ኢየሱስ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ መሆኑ ሰዎች ለአምላክ ታዛዥ በመሆን አቋማቸውን ጠብቀው መኖር እንደሚችሉ አረጋግጧል።

በተጨማሪም የክርስቶስ ሞት ከሰው ልጆች መካከል የተወሰኑት ከእሱ ጋር በሰማይ የመግዛት አጋጣሚ እንዲያገኙ አስችሏል። እንዲሁም ብዙዎች ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ለዘላለም መኖር የሚችሉበትን መንገድ ከፍቷል።

ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት ላይ፣ በፍቅር በመነሳሳት መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበውን ሥጋና ደሙን ለማመልከት ያልቦካ ቂጣና ቀይ የወይን ጠጅ ተጠቀመ። ደቀ መዛሙርቱንም “ይህን ሁልጊዜ ለመታሰቢያዬ አድርጉት” አላቸው። (ሉቃስ 22:19) አንተስ ይህን ታላቅ ክንውን ለማስታወስ በበዓሉ ላይ ትገኛለህ?

የይሖዋ ምሥክሮች የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ በዓል አብረሃቸው እንድታከብር በአክብሮት ይጋብዙሃል። በዚህ ዓመት በዓሉ የሚከበረው ሐሙስ፣ ሚያዝያ 9, 2009 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሚያዝያ 1, 2001) ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ይሆናል። ለቤትህ ቅርብ በሆነው የመንግሥት አዳራሽ ተገኝተህ በዓሉን ማክበር ትችላለህ። በዓሉ የሚከበርበትን ትክክለኛ ሰዓትና ቦታ ለማወቅ እባክህ በአቅራቢያህ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮችን አነጋግር።