በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ኢየሱስ ፈተናን ተቋቁሟል

ኢየሱስ ፈተናን ተቋቁሟል

ለወጣት አንባቢያን

ኢየሱስ ፈተናን ተቋቁሟል

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳልና ሌላው ቀርቶ ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማት ሞክር። እንዲሁም የባለ ታሪኮቹን ስሜት ለመረዳት ጥረት አድርግ።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ማቴዎስ 4:1-11ን አንብብ።

ኢየሱስ ለ40 ቀናት የቆየበት ምድረ በዳ ምን ዓይነት ይመስልሃል?

․․․․․

ፈታኙ ኢየሱስን ሲያናግረው ምን ዓይነት የድምፅ ቃና የተጠቀመ ይመስልሃል? ኢየሱስስ በምን ዓይነት የድምፅ ቃና ምላሽ የሰጠው ይመስልሃል?

․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

ሰይጣን አጋጣሚዎችን በመጠቀም ፈተና ሊያመጣ እንደሚችል የሚያሳየው ምንድን ነው? (ቁጥር 2⁠ን እንደገና አንብብ።)

․․․․․

ዲያብሎስ ሁሉንም የዓለም መንግሥታት ብቻ ሳይሆን “ክብራቸውን” ጭምር ለኢየሱስ እንደሚሰጠው የነገረው ለምንድን ነው? (ቁጥር 8⁠ን እንደገና አንብብ።)

․․․․․

ሰይጣን፣ ለኢየሱስ ዓለምን የመግዛትን አጋጣሚ በማቅረብ የፈተነው ለምን ሊሆን ይችላል?

․․․․․

(ሀ) ሰይጣን ያቀረባቸው ሦስቱም ፈተናዎች ሰይጣን ስለሚያስብበት መንገድ ምን ይጠቁማሉ? ․․․․․

(ለ) ኢየሱስ የሰጣቸው መልሶችስ ስለ ኢየሱስ አመለካከት ምን ይጠቁማሉ? ․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት በጥሩ መንገድ ተጠቀምበት። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ፈተና መቼ ሊያጋጥመን እንደሚችል።

․․․․․

ሰይጣን እኛን ለመፈተን ሊጠቀምባቸው ስለሚችላቸው የተለያዩ ዘዴዎች።

․․․․․

ፈተናዎችን በምን መንገድ መቋቋም እንደምንችል።

․․․․․

በዚህ ዘገባ ውስጥ ከተገለጹት ሁኔታዎች መካከል አንተን ይበልጥ የነካህ የትኛው ነው? ለምንስ?

․․․․․