በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አምላክ በገባው ቃል ላይ እምነት የነበረው ሰው

አምላክ በገባው ቃል ላይ እምነት የነበረው ሰው

ለወጣት አንባቢያን

አምላክ በገባው ቃል ላይ እምነት የነበረው ሰው

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳልና ሌላው ቀርቶ ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማት ሞክር። እንዲሁም የባለ ታሪኮቹን ስሜት ለመረዳት ጥረት አድርግ።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ዘፍጥረት 12:1-4፤ 18:1-15፤ 21:1-5፤ 22:15-18ን አንብብ።

አብርሃም፣ ለመላው ዓለም በረከት የሚያመጣው “ዘር” በእሱ የዘር ሐረግ እንደሚመጣ አምላክ ቃል ሲገባለት ምን ተሰምቶት ሊሆን እንደሚችል መገመት ትችላለህ?

․․․․․

በዘፍጥረት 18:2 ላይ የተጠቀሱት ሦስቱ እንግዶች ምን ሊመስሉ እንደሚችሉ መግለጽ ትችላለህ?

․․․․․

በዘፍጥረት 18:6-8 ላይ እንደተጠቀሰው አብርሃም ያደረገውን ነገር እንዴት ትገልጸዋለህ? (በወቅቱ የአብርሃም ዕድሜ ወደ 100 ዓመት ይጠጋ እንደነበር አትዘንጋ።)

․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

አብርሃም ይስሐቅን የወለደው፣ ወንድ ልጅ እንደሚወልድ ይሖዋ ቃል ከገባለት ከስንት ጊዜ በኋላ ነበር? (ዘፍጥረት 12:4⁠ን እና 21:5⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

አብርሃም አምላክ የሰጠው ተስፋ እስኪፈጸም እየጠበቀ በነበረበት ወቅት፣ ይሖዋ ለአብርሃም የገባውን ቃል እንደሚፈጽም በተለያዩ ጊዜያት ያረጋገጠለት እንዴት ነበር? (ዘፍጥረት 12:7፤ 13:14-17፤ 15:1-5, 12-21፤ 17:1, 2, 7, 8, 15, 16⁠ን አንብብ።)

․․․․․

አብርሃም ልጅ እንደሚወልድ በተጠራጠረበት ወቅት ይሖዋ ምን አደረገ? (ዘፍጥረት 15:3-5, 12-21⁠ን በድጋሚ አንብብ።)

․․․․․

ይሖዋ ተስፋ ከተሰጠበት “ዘር” ጋር የተያያዙ ዝርዝር መረጃዎችን ደረጃ በደረጃ የገለጠው እንዴት ነበር?

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት በጥሩ መንገድ ተጠቀምበት። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

አምላክ በገባው ቃል ላይ እምነት ማሳደር አስፈላጊ ስለመሆኑ።

․․․․․

ይሖዋ ፈቃዱን ደረጃ በደረጃ ስለሚገልጽበት መንገድ።

․․․․․

በዚህ ዘገባ ውስጥ ከተገለጹት ሁኔታዎች መካከል አንተን ይበልጥ የነካህ የትኛው ነው? ለምንስ?

․․․․․